በደብረታቦር፣ በወረታ እና በአዲሥ ዘመን ከተሞች ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ቀን የስራ ማቆም አድማው የተጀመረ ሲሆን ደብረታቦር ከተማ ፀጥ ረጭ ብላለች።


በደብረታቦር፣ በወረታ እና በአዲሥ ዘመን ከተሞች ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ቀን የስራ ማቆም አድማው የተጀመረ ሲሆን ደብረታቦር ከተማ ፀጥ ረጭ ብላለች። #MinilikSalsawi ከጎንደር ወልድያና ባሃርዳር መንገዶች ተዘግተዋል።

አዊ ዞን ከፍተኛ ተካውሞ እየተካሄደ ነው ፤በጣም ከልክ ያለፈ ተኩስ አለ። ምን ያህል ሰው እንደሞተ እና እንደቆሰለ ኣልታወቀም። በምዕራብ ጎጃም ሰከላ በምትባል አካባቢ ህዝቡ በነቂስ በመውጣት የብአዴን ፅህፈት ቤትን ሙሉ ለሙሉ እንዳወደመና በመንግስት ተቋማት የተሰቀሉ ባንዲራዎችን በማውረድ በምትኩ አርማ የሌለበትን ባንዲራ ሰቅሏል በአካባቢው የተኩስ ድምፅ በየአቅጣጫው ይሰማል ።የደቡብ ጎንደሯ እሥቴ(መካነ እየሡሥ) ከተማ የአማራ ተጋድሎውን በሥራ ማቆም አድማ ተቀላቀለች። በመካነ እየሡን ከተማ አገልግሎት ሠጭ ተቋማት በሙሉ ተዘግተዋል። በነገራችን ላይ መካነ እየሡሥ ከተማ ከዚህ በፊት የአማራ ተጋድሎን በመቀላቀል ግንባር ቀደሟ ነበረች። ከዚህ በፊት በሠላማዊ ሠልፍ የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬ ከቤት ባለመውጣት ተቃውሞ ተደግሟል!በደቡብ ጎንደር ወረታ ከተማ የሥራ ማቆም አድማውን ተከትሎ ሱቆችንና ሆቴሎችን ለማሥከፈት የተደረገው ሙከራ ወደ ግጭት ማደጉን ከቦታው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በአሁኑ ሠዓት የከተማው ህዝብ ወደ አደባባዮች የወጣ ሲሆን በአጸፋው የመንግሥት ታማኞች በየአቅጣጫው እየተኮሡ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል ወረታ፤ ሃሙሲትና አመድበር ቀውጢ ተፈጥሯል!የጉማራና ርብ ድልድዮች በተጋድሎ ወጣቶች ቁጥጥር ስር ወድቀዋል። ከጎንደር ወልድያና ባሃርዳር መንገዶች ተዘግተዋል። የገጠሩ ህዝብ ከነትጥቁና ፈረሱ እየፎከረና እየሸለለ ወደ ከተሞቹ ገብቷል፤ ከከተማው ወጣቶች ጋር በመሆንም አካባቤውን ተቆጣጥሯል። ሁኔታው ሁሉ በቃ ተቀይሯል።ደብረታቦር አሁንም ፀጥ ብላለች። ምንም አይነት እንቅስቃሴ የለም።ፎገራ ወረታ ከተማ ታሪክ ተቀየረ፡፡ ጦርነቱ ተጀምሯል፡፡ ተደራጅተው የቆዩ ወጣቶች የገጠሩም የከተማውም ዝናሩን እያገማሸረ ታጥቆ ወጥቷል፡፡ጉጅሌና ፖሊስ ድራሹ ጠፍቷል፡፡ እየተቧደነ መደበቂያ ፍለጋ ላይ ነው፡፡ ሀሙሲቶችና የጉማራ ገበሬ ታጥቆ እየገባ ነው፡፡ ከደብረታቦር የታጠቁ ወጣቶች ወረታ ገብተዋል፡፡