ጠቅላይ ሚንስትሩ እራሳቸው መጀመሪያ ስልጣን ይልቀቁ በቀጥታ ስልክ ውይይት ላይ ከሚሚ ስብሃቱ ጋር ሲከራከር ያዳምጡ።


<<ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ለዚች ሀገር ምን ሰሩ እና ነው እሳቸው እና ትላልቅ ባለስጣናት ቁጭ ብለው ሌሎችን ከስልጣን አንስተናል የሚሉት :: የችግሩ ምንጭ ዋናዎቹ
ከላይ ያሉት እነሱ ናቸው :: መጀመሪያ እራሳቸው ከስልጣን ይልቀቁ >> አንድ አድማጭ

Advertisements

ሊደመጥ የሚገባው እጅግ ወሳኝ የአማራ ተጋድሎ አረበኞች መልእክት ክፍል ፩። በዚህ መልእክት ውስጥ አማራው መደራጀቱ ዘረኝነት ነው ኢትዮጵያን ለማፍረስ ነው ለሚሉ አካላትም በቂ መለስ የተሰጠበት ድንቅ እና ግሩም መልእክት። እኛ የተደራጀነው አሉ ……


አንድ አባት ሦስት ልጆች እንደተገደለባቸው ገለፁ


8a5d3b29-a485-46e5-ad21-4f89d17fbab3_w987_r1_s

“እኔ ገጠር ተቀምጬ ልጆቼን ከተማ ነበር የማኖራቸው፡፡ በታጣቂዎች መገደላቸውን ሰምቼ ወደ ሚኖሩበት ከተማ ስሄድ የሦስቱንም ወንድ ልጆቼን አስከሬን ደጄ ላይ ወድቆ አገኘሁት” – አቶ ጀማል ሰኢድ ለአሜሪካ ድምፅ ከተናገሩት የተወሰደ ነው፡፡
ዋሺንግተን ዲሲ —
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምስራቅ አርሲ ዞን ውስጥ በሽርካ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ አቶ ጀማል ሁሴን የተባሉ ግለሰብ ሦስት ልጆቻቸው በታጣቂዎች እንደተገደሉባቸው ለአሜሪካ ድምጽ አፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍል ገለጹ።

“ምናልባት በህይወት ኖሬ ዐይምሮዬ ትክክል ከሆነ ‘ልጆቼ ምን አደረጉህ?’ ብዬ መንግስትን እጠይቀው ይሆናል” ብለዋል።

የወረዳው አስተዳዳሪ ሁኔታውን በስልክ ከመስማት ውጪ አካባቢው ላይ ስለሌሉ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።

በዚህ ዞን ሌላ ወረዳ ውስጥ ተጨማሪ ግድያ መፈፀሙን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ጃለኔ ገመዳ ያጠናቀረቸውን ሪፖርት ጽዮን ግርማ አሰናድታዋለች።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ነፃነት የሌለባት ሀገር ተብላለች


92c08975-f3fb-45a1-9108-09f8d6fa0aa7_w987_r1_s

 

መቀመጫውን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው ፍሪደም ሃውስ የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት የ2016 የዓለማት የኢንተርኔት ነፃነት ደረጃን ይፋ ባደረገበት ሪፖርቱ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት የኢንተርኔት ነጻነት በመገደብ አንደኛ ስትሆን ከ65 ሀገራት ደግሞ በአራተኛ ደረጃ ነፃነትን ገዳቢ ሀገር ተብላለች። ቻይና የኢንተርኔት ነጻነት በመገደብ 1ኛ ናት።

ፍሪደም ሀውስ Freedom on the Net 2016 (በኢንተርኔት ላይ ያለ ነፃነት) በሚል በትናንትናው ዕለት ባወጣው ሪፖርቱ በዓለም ላይ የኢንተርኔት አፈና እየጨመረ መምጣቱንና ጥናት ከተደረገባቸው 65 ሀገራት ውስት 35 በመቶ የሚሆኑት የኢንተርኔት ነፃነት የሌለባቸው መሆኑን ይፋ አድርጓል።

ፍሪደም ሀውስ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የጎግል መስሪያ ቤት ሪፖርቱን ይፋ ሲያደርግ የተገኘችው ጽዮን ግርማ ተከታዩን ዘግባለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምፅ ያድምጡ

የምንሄድበት መንገድ ያሳፍራል ያሳዝናል!!! የሕወሓት ቅልብ ዘረኞች ለለውጥ የሚደረገውን ትግል እያመሱ ነው::


14993508_1808663716071490_3802065714608474223_nሕወሓት የሚዘውረው የሚመራው አገዛዝ ይህን አደረገ ይህን አደረገ ዘረፈ ሰቀለ ገለፈ አሰረ ገደለ አሳደደ ወዘተ የሚሉ እኩይ ተግባራቱ ብንዘረዝረው አያልቅም ከዚህ ይልቅ አሁን የሚያስፈልገን ነገር ቢኖር ይህንን እኩይ አገዛዝ ለመጣል የምንሄድበት መንገድ የምንጓዝበት ስትራቴጂ አዋጪ ነው እቅዳችን አሳዛኝና አሳፋሪ ነው የምንለውን እንዴት ማስተካክል አለብን ኬዘመነ ትግል ጀምሮ ሲሰበክ የነበረው አንድ እንሁን በም አይነት መቻቻል እና ስልት ይሳካል ብሎም በዲያስፖራው ውስጥ ተቀምጠው ለሕዝብ ይተከራከሩ የሚመስሉ የሕወሓትን ራእይ የሚያሳኩ እና ተልእኮ ይዘው ለሚያናክሱ ፖለቲከኛ መሳዮች ባለመንታ ምላሶችን ከጨዋታ እጪ ማድርግ የመሳሰሉ ጉዳዮችን በተግባር የምንተረጉም ሆነ መገኘት ለጥያቄዎቻችንም መልስ ማግኘት አለብን ካልሆነ የምንሄድበት መንገድ ያሳፍራል ያሳዝናል::
ሕወሓት ኢትዮጵያን በታትኖ የራሱን አገዛዝ ለመመስረት እየተጣደፈ ይገኛል ለዚህ አላማ ስኬት ይሆነው ዘንድ በሃገር ቤትም ይሁን በውጪ ያሰማራቸው ዘረኝነትን የሚሰብኩ የሕወሓት ተቃዋሚ መስለው ኢትዮጵያን እንደ ቅኝ ገዢ ያስቀመጡ ቅልብ ዘረኞች ለለውጥ የሚደረገውን ትግል እያመሱ ነው::ሕዝቦች ለራሳቸው ነጽነት በሚታገሉበት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጫና አንገብግቧቸው አደባባይ በሚጮኹበት በዚህ ወቅት ላይ የሕዝብን ትግል ለጠባብነታቸው የሚጠቀሙበትን የእናት ጡት ነካሾች እቅተናል ብቻ ሳንል በተግባርም ልናስወግዳቸው ይገባል::ሕወሓት ከአነሳሱ ጀምሮ የመገንጠል ሱሱን ለማሳካት ደፋ ቀና እያለ ሲሆን የኢትዮጵያን ሉዋላዊነት ከመርህ እስከ ተግባር በመዳፈር ላይ ከመሆኑም ሌላ የበረሃ ስሙን እንኳን ሳይቀይር እስከዛሬ ሲዘልቅ ለዚሁ ግቡ ደግሞ አንዴ በኦሮሞ ሲለው በአማራ ስም የተፈለፈሉ ጠባብ ግለሰቦችን በማደራጀት የአገርና የሕዝብን ሕልውና በመጋፋት ላይ ይገኛል::ሕወሓት ክፋቱን ተንኮሉን እየቆፈረ ባለበት በዚህ ወት ክፍተት የሚፈጥሩ የቃላት ጦርነቶች ከማድረግ ይልቅ ሕወሓትን በቆፈረው ጉድጓድ ለመቅበር በጋራ መቆም ይጠይቃል ይህን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ የምሄድበት መንገድ ያሳዝናል ያሳፍራል::
የኦሮሞ ሕዝብን ትግል የኣማራን ሕዝብ ትግል ለማቀናጀት የተኬደበት መንገድ የኦጋዴን ሕዝብን ጥያቄ ለመተባበር የተኬደበት መንገድ የወልቃይት ጠገዴን እንዲሁም የጎንደር አከባቢን ጉዳይ ለመመለስ የተኬደበት መንገድ ሊመረመር ይገባዋል::እነማን ገብተው አደፈረሱ ከሚለው ጀምሮ በቃላት እና በወሬ እስከመቼ ይዘለቃል ብሎም የትግሉ እንቅስቃሴ እውን ዘልቆ ገብቶ የሕዝቡን የገነፈለ ቁጣ አቀናጅቶ ለግብ ይመራል ወይ ተደርጓል ወይ ካልተደረገስ.. ወዘተ የሚሉ ጉዳዮች ሊመረመሩ ይገባል::የትግሉን መንገድ ከግብ ለማድረስ የምሄድበት መንገድ በፖለቲካ ድርጅት ስር የታቀፉ አባላቶች እየታገሉበት ያለው መንገድ ሊመረመር ይገባል::አንድ ችግር በተነሳ ሰአት ወያኔ ስለ መልካም አስተዳደር እንደሚያላዝነው የለውጥ ሃይሉም ችግሩ እስኪቀዘቅዝ በአንድ እንሁን ሰበብ ከሚፋተግ ዘላጊ መፍትሄ እና በመከባበር በመቻቻል መንፈስ ላይ የተመረኮዘ መፍትሄ ሊያበጅ ይገባል::ካልሆነ አሁን የተያዘው መንገድ ያሳፍራል ያሳዝናል

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ዶከተር መረራ ጉዲናና የሪዮው ጀግና አትሌት ሌሊሳ ፈይሳ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ንግግር አደረጉ።


%e1%8d%95%e1%88%ae%e1%8d%8c-768x461

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ፕሬዝደንት ዶከተር መረራ ጉዲና እንዲሁም የሪዮው ጀግና አትሌት ሌሊሳ ፈይሳ በብራሰልስ 30 ጥቅምት 2009 ዓም ለአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸመ ያለውን አምባገነናዊና ኢሰብአዊ ወንጀሎችን በመጥቀስ ንግግር አድርገዋል። ከዚህም በተጨማሪ ወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታን ለተሰባሳቢዎቹ ለማስረዳት ሞክረዋል። ፕሮግራሙን በተሳካ ሁኔታ የመሩት ወይዘሮ አና ጎሜዝ እንደሆኑም ለመረዳት ተችሏል።
ከሶስቱ ተጋባዥ ተናጋሪዎች ውስጥ የሆነው አትሌት ሌሊሳ ፈይሳ የወያኔ መንግስት በንጹሃን ኢትዮጵያውያን ላይ የሚወስደውን ቅጥ ያጣ የሃይል እርምጃን ለፓርላማው ለመግለጽ ሞክሯል። የሩጫ ሙያዬ በተለያዩ አገራት እየተዘዋወርኩ ወያኔ በአንድ ብሄር ብቻ ሳይሆን በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈጽመውን እልቂትና ግድያ ለአለም ለማጋለጥ አስችሎኛል በማለት ለተሰብሳቢው ገልጿል። ይህ ጀግና የኢትዮጵያዊነት መንፈስ በውስጡ የሰረጸ አትሌት እንዲህ ባለ ትልቅ መድረክ የአንድን ብሄር ብቻ ሳይሆን የመላ ኢትዮጵያውያንን ሰቆቃ ለአለም ለማሳወቅ እየጣረ እንደሚገኝም አስረድቷል። በአለም እየተዘዋወረ የሚናገረውም አንድን ብሄር ወክሎ ሳይሆን ሁሉንም ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ገልጿል። አትሌቱም በማከል የአማራው መሬት ለትግራይ እየተሰጠ የአማራው ህዝብ እንደሚፈናቀል፤ የአዲስ አበባ መሬት እየተገፋ የኦሮሞ ተወላጅ እንደሚፈናቀል፤ በጋምቤላና በሌሎችም ቦታዎች በኢንቨስትመንት ስም ሰዎች እየተፈናቀሉ እንደሆነ ለማስረዳት ችሏል። በተጨማሪም ይህንን የሰዎችን መፈናቀል የሚቃወሙ በወያኔ መንግስት ግድያና እስራት እየተፈጸመባቸው መኖኑንም በንግግሩ ገልጿል። በማጠቃለያውም የአውሮፓ ህብረት ለወያኔ የሚያደርጉትን እርዳታ እንዲያቆሙና ለመብታቸው ከሚታገሉት የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በትብብር እንዲሰሩ ለፓርላማው ጥያቄውን አቅርቧል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና ዶክተር መራራ ጉዲናም የአውሮፓ ህብረት የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለሚፈጽመው ወንጀል ተባባሪ ሳይሆን የመፍትሄ አካል እንዲሆን አጽንኦት በመስጠት ንግግራቸውን አድርገዋል። እነዚህ ሁለቱ ተጋባዥ ተናጋሪዎች በበኩላቸው የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያን በአምባገነንነት እየገዛት ባለው የወያኔ መንግስት ላይ ጫና እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
በማጠቃለያም  ስለ ቀረበው  ገላጻ በፓርላማው በተገኙ አባላት ከፍተኛ ውይይት ከተደረገ በኋላ ወይዘሮ አና ጎሜዝ የሶስቱን ተጋባዦች ንግግር ለአውሮፓ የውጭ ጉዳይ ሃላፊ፣ ለአውሮፓ ካውንስል ፕሬዝዳንት እንዲሁም ለአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት በሪፖርት ተጠናክሮ እንደሚቀርብ ገልጸዋል።ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ዶከተር መረራ ጉዲናና የሪዮው ጀግና አትሌት ሌሊሳ ፈይሳ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ንግግር አደረጉ።ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ዶከተር መረራ ጉዲናና የሪዮው ጀግና አትሌት ሌሊሳ ፈይሳ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ንግግር አደረጉ።