ጠቅላይ ሚንስትሩ እራሳቸው መጀመሪያ ስልጣን ይልቀቁ በቀጥታ ስልክ ውይይት ላይ ከሚሚ ስብሃቱ ጋር ሲከራከር ያዳምጡ።


<<ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ለዚች ሀገር ምን ሰሩ እና ነው እሳቸው እና ትላልቅ ባለስጣናት ቁጭ ብለው ሌሎችን ከስልጣን አንስተናል የሚሉት :: የችግሩ ምንጭ ዋናዎቹ
ከላይ ያሉት እነሱ ናቸው :: መጀመሪያ እራሳቸው ከስልጣን ይልቀቁ >> አንድ አድማጭ

ሊደመጥ የሚገባው እጅግ ወሳኝ የአማራ ተጋድሎ አረበኞች መልእክት ክፍል ፩። በዚህ መልእክት ውስጥ አማራው መደራጀቱ ዘረኝነት ነው ኢትዮጵያን ለማፍረስ ነው ለሚሉ አካላትም በቂ መለስ የተሰጠበት ድንቅ እና ግሩም መልእክት። እኛ የተደራጀነው አሉ ……

አንድ አባት ሦስት ልጆች እንደተገደለባቸው ገለፁ


8a5d3b29-a485-46e5-ad21-4f89d17fbab3_w987_r1_s

“እኔ ገጠር ተቀምጬ ልጆቼን ከተማ ነበር የማኖራቸው፡፡ በታጣቂዎች መገደላቸውን ሰምቼ ወደ ሚኖሩበት ከተማ ስሄድ የሦስቱንም ወንድ ልጆቼን አስከሬን ደጄ ላይ ወድቆ አገኘሁት” – አቶ ጀማል ሰኢድ ለአሜሪካ ድምፅ ከተናገሩት የተወሰደ ነው፡፡
ዋሺንግተን ዲሲ —
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምስራቅ አርሲ ዞን ውስጥ በሽርካ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ አቶ ጀማል ሁሴን የተባሉ ግለሰብ ሦስት ልጆቻቸው በታጣቂዎች እንደተገደሉባቸው ለአሜሪካ ድምጽ አፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍል ገለጹ።

“ምናልባት በህይወት ኖሬ ዐይምሮዬ ትክክል ከሆነ ‘ልጆቼ ምን አደረጉህ?’ ብዬ መንግስትን እጠይቀው ይሆናል” ብለዋል።

የወረዳው አስተዳዳሪ ሁኔታውን በስልክ ከመስማት ውጪ አካባቢው ላይ ስለሌሉ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።

በዚህ ዞን ሌላ ወረዳ ውስጥ ተጨማሪ ግድያ መፈፀሙን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ጃለኔ ገመዳ ያጠናቀረቸውን ሪፖርት ጽዮን ግርማ አሰናድታዋለች።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ነፃነት የሌለባት ሀገር ተብላለች


92c08975-f3fb-45a1-9108-09f8d6fa0aa7_w987_r1_s

 

መቀመጫውን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው ፍሪደም ሃውስ የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት የ2016 የዓለማት የኢንተርኔት ነፃነት ደረጃን ይፋ ባደረገበት ሪፖርቱ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት የኢንተርኔት ነጻነት በመገደብ አንደኛ ስትሆን ከ65 ሀገራት ደግሞ በአራተኛ ደረጃ ነፃነትን ገዳቢ ሀገር ተብላለች። ቻይና የኢንተርኔት ነጻነት በመገደብ 1ኛ ናት።

ፍሪደም ሀውስ Freedom on the Net 2016 (በኢንተርኔት ላይ ያለ ነፃነት) በሚል በትናንትናው ዕለት ባወጣው ሪፖርቱ በዓለም ላይ የኢንተርኔት አፈና እየጨመረ መምጣቱንና ጥናት ከተደረገባቸው 65 ሀገራት ውስት 35 በመቶ የሚሆኑት የኢንተርኔት ነፃነት የሌለባቸው መሆኑን ይፋ አድርጓል።

ፍሪደም ሀውስ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የጎግል መስሪያ ቤት ሪፖርቱን ይፋ ሲያደርግ የተገኘችው ጽዮን ግርማ ተከታዩን ዘግባለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምፅ ያድምጡ

የምንሄድበት መንገድ ያሳፍራል ያሳዝናል!!! የሕወሓት ቅልብ ዘረኞች ለለውጥ የሚደረገውን ትግል እያመሱ ነው::


14993508_1808663716071490_3802065714608474223_nሕወሓት የሚዘውረው የሚመራው አገዛዝ ይህን አደረገ ይህን አደረገ ዘረፈ ሰቀለ ገለፈ አሰረ ገደለ አሳደደ ወዘተ የሚሉ እኩይ ተግባራቱ ብንዘረዝረው አያልቅም ከዚህ ይልቅ አሁን የሚያስፈልገን ነገር ቢኖር ይህንን እኩይ አገዛዝ ለመጣል የምንሄድበት መንገድ የምንጓዝበት ስትራቴጂ አዋጪ ነው እቅዳችን አሳዛኝና አሳፋሪ ነው የምንለውን እንዴት ማስተካክል አለብን ኬዘመነ ትግል ጀምሮ ሲሰበክ የነበረው አንድ እንሁን በም አይነት መቻቻል እና ስልት ይሳካል ብሎም በዲያስፖራው ውስጥ ተቀምጠው ለሕዝብ ይተከራከሩ የሚመስሉ የሕወሓትን ራእይ የሚያሳኩ እና ተልእኮ ይዘው ለሚያናክሱ ፖለቲከኛ መሳዮች ባለመንታ ምላሶችን ከጨዋታ እጪ ማድርግ የመሳሰሉ ጉዳዮችን በተግባር የምንተረጉም ሆነ መገኘት ለጥያቄዎቻችንም መልስ ማግኘት አለብን ካልሆነ የምንሄድበት መንገድ ያሳፍራል ያሳዝናል::
ሕወሓት ኢትዮጵያን በታትኖ የራሱን አገዛዝ ለመመስረት እየተጣደፈ ይገኛል ለዚህ አላማ ስኬት ይሆነው ዘንድ በሃገር ቤትም ይሁን በውጪ ያሰማራቸው ዘረኝነትን የሚሰብኩ የሕወሓት ተቃዋሚ መስለው ኢትዮጵያን እንደ ቅኝ ገዢ ያስቀመጡ ቅልብ ዘረኞች ለለውጥ የሚደረገውን ትግል እያመሱ ነው::ሕዝቦች ለራሳቸው ነጽነት በሚታገሉበት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጫና አንገብግቧቸው አደባባይ በሚጮኹበት በዚህ ወቅት ላይ የሕዝብን ትግል ለጠባብነታቸው የሚጠቀሙበትን የእናት ጡት ነካሾች እቅተናል ብቻ ሳንል በተግባርም ልናስወግዳቸው ይገባል::ሕወሓት ከአነሳሱ ጀምሮ የመገንጠል ሱሱን ለማሳካት ደፋ ቀና እያለ ሲሆን የኢትዮጵያን ሉዋላዊነት ከመርህ እስከ ተግባር በመዳፈር ላይ ከመሆኑም ሌላ የበረሃ ስሙን እንኳን ሳይቀይር እስከዛሬ ሲዘልቅ ለዚሁ ግቡ ደግሞ አንዴ በኦሮሞ ሲለው በአማራ ስም የተፈለፈሉ ጠባብ ግለሰቦችን በማደራጀት የአገርና የሕዝብን ሕልውና በመጋፋት ላይ ይገኛል::ሕወሓት ክፋቱን ተንኮሉን እየቆፈረ ባለበት በዚህ ወት ክፍተት የሚፈጥሩ የቃላት ጦርነቶች ከማድረግ ይልቅ ሕወሓትን በቆፈረው ጉድጓድ ለመቅበር በጋራ መቆም ይጠይቃል ይህን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ የምሄድበት መንገድ ያሳዝናል ያሳፍራል::
የኦሮሞ ሕዝብን ትግል የኣማራን ሕዝብ ትግል ለማቀናጀት የተኬደበት መንገድ የኦጋዴን ሕዝብን ጥያቄ ለመተባበር የተኬደበት መንገድ የወልቃይት ጠገዴን እንዲሁም የጎንደር አከባቢን ጉዳይ ለመመለስ የተኬደበት መንገድ ሊመረመር ይገባዋል::እነማን ገብተው አደፈረሱ ከሚለው ጀምሮ በቃላት እና በወሬ እስከመቼ ይዘለቃል ብሎም የትግሉ እንቅስቃሴ እውን ዘልቆ ገብቶ የሕዝቡን የገነፈለ ቁጣ አቀናጅቶ ለግብ ይመራል ወይ ተደርጓል ወይ ካልተደረገስ.. ወዘተ የሚሉ ጉዳዮች ሊመረመሩ ይገባል::የትግሉን መንገድ ከግብ ለማድረስ የምሄድበት መንገድ በፖለቲካ ድርጅት ስር የታቀፉ አባላቶች እየታገሉበት ያለው መንገድ ሊመረመር ይገባል::አንድ ችግር በተነሳ ሰአት ወያኔ ስለ መልካም አስተዳደር እንደሚያላዝነው የለውጥ ሃይሉም ችግሩ እስኪቀዘቅዝ በአንድ እንሁን ሰበብ ከሚፋተግ ዘላጊ መፍትሄ እና በመከባበር በመቻቻል መንፈስ ላይ የተመረኮዘ መፍትሄ ሊያበጅ ይገባል::ካልሆነ አሁን የተያዘው መንገድ ያሳፍራል ያሳዝናል

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ዶከተር መረራ ጉዲናና የሪዮው ጀግና አትሌት ሌሊሳ ፈይሳ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ንግግር አደረጉ።


%e1%8d%95%e1%88%ae%e1%8d%8c-768x461

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ፕሬዝደንት ዶከተር መረራ ጉዲና እንዲሁም የሪዮው ጀግና አትሌት ሌሊሳ ፈይሳ በብራሰልስ 30 ጥቅምት 2009 ዓም ለአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸመ ያለውን አምባገነናዊና ኢሰብአዊ ወንጀሎችን በመጥቀስ ንግግር አድርገዋል። ከዚህም በተጨማሪ ወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታን ለተሰባሳቢዎቹ ለማስረዳት ሞክረዋል። ፕሮግራሙን በተሳካ ሁኔታ የመሩት ወይዘሮ አና ጎሜዝ እንደሆኑም ለመረዳት ተችሏል።
ከሶስቱ ተጋባዥ ተናጋሪዎች ውስጥ የሆነው አትሌት ሌሊሳ ፈይሳ የወያኔ መንግስት በንጹሃን ኢትዮጵያውያን ላይ የሚወስደውን ቅጥ ያጣ የሃይል እርምጃን ለፓርላማው ለመግለጽ ሞክሯል። የሩጫ ሙያዬ በተለያዩ አገራት እየተዘዋወርኩ ወያኔ በአንድ ብሄር ብቻ ሳይሆን በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈጽመውን እልቂትና ግድያ ለአለም ለማጋለጥ አስችሎኛል በማለት ለተሰብሳቢው ገልጿል። ይህ ጀግና የኢትዮጵያዊነት መንፈስ በውስጡ የሰረጸ አትሌት እንዲህ ባለ ትልቅ መድረክ የአንድን ብሄር ብቻ ሳይሆን የመላ ኢትዮጵያውያንን ሰቆቃ ለአለም ለማሳወቅ እየጣረ እንደሚገኝም አስረድቷል። በአለም እየተዘዋወረ የሚናገረውም አንድን ብሄር ወክሎ ሳይሆን ሁሉንም ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ገልጿል። አትሌቱም በማከል የአማራው መሬት ለትግራይ እየተሰጠ የአማራው ህዝብ እንደሚፈናቀል፤ የአዲስ አበባ መሬት እየተገፋ የኦሮሞ ተወላጅ እንደሚፈናቀል፤ በጋምቤላና በሌሎችም ቦታዎች በኢንቨስትመንት ስም ሰዎች እየተፈናቀሉ እንደሆነ ለማስረዳት ችሏል። በተጨማሪም ይህንን የሰዎችን መፈናቀል የሚቃወሙ በወያኔ መንግስት ግድያና እስራት እየተፈጸመባቸው መኖኑንም በንግግሩ ገልጿል። በማጠቃለያውም የአውሮፓ ህብረት ለወያኔ የሚያደርጉትን እርዳታ እንዲያቆሙና ለመብታቸው ከሚታገሉት የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በትብብር እንዲሰሩ ለፓርላማው ጥያቄውን አቅርቧል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና ዶክተር መራራ ጉዲናም የአውሮፓ ህብረት የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለሚፈጽመው ወንጀል ተባባሪ ሳይሆን የመፍትሄ አካል እንዲሆን አጽንኦት በመስጠት ንግግራቸውን አድርገዋል። እነዚህ ሁለቱ ተጋባዥ ተናጋሪዎች በበኩላቸው የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያን በአምባገነንነት እየገዛት ባለው የወያኔ መንግስት ላይ ጫና እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
በማጠቃለያም  ስለ ቀረበው  ገላጻ በፓርላማው በተገኙ አባላት ከፍተኛ ውይይት ከተደረገ በኋላ ወይዘሮ አና ጎሜዝ የሶስቱን ተጋባዦች ንግግር ለአውሮፓ የውጭ ጉዳይ ሃላፊ፣ ለአውሮፓ ካውንስል ፕሬዝዳንት እንዲሁም ለአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት በሪፖርት ተጠናክሮ እንደሚቀርብ ገልጸዋል።ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ዶከተር መረራ ጉዲናና የሪዮው ጀግና አትሌት ሌሊሳ ፈይሳ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ንግግር አደረጉ።ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ዶከተር መረራ ጉዲናና የሪዮው ጀግና አትሌት ሌሊሳ ፈይሳ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ንግግር አደረጉ።

የሕወሓት መንግስት ሃገር ውስጥ በሚኖሩ በዲያስፖራው ቤተሰቦች ላይ ታክቲካዊ ጥቃት ይፈጽማል:: #Ethiopia #HumanRights #


protest_2

የሕወሓት መንግስት ሃገር ውስጥ በሚኖሩ በዲያስፖራው ቤተሰቦች ላይ ታክቲካዊ ጥቃት ይፈጽማል:: ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ ዲያስፖራዎችንም ቤተሰቦች በዘፍቀደ ያፍናል ሲል አንድ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ገለጸ። ሂዩማን ራይት ስ ዎች የተባለው የሰብዓዊ መብት ድርጅት እንደጠቀሰው በሜልቦርን በስኔ ተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተሳተፉ በኣውስትራሊያ ነዋሪዎች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ዘመዶቻቸው በጅምላ ታፍሰው እስር ቤት መወርወራቸውን እና እስካሁን ኣለመፈታታቸውን ያብራራል። በምስልና በቪድዮ የተደገፈውን ዝርዝር እዚህ ሊንክ ላይ ያገኙታል ፦

http://mereja.com/network/post/320/australia-protests-prompt-ethiopia-reprisals-human-rights-wat

ህወሃት/ኢህአዴግ የራሱን ሪፖርት ይፋ ማድረግ ፈርቷል! “በጽሁፍ የታተመ ዘገባ በእርግጥ ካለ ይፋ አድርጉ!”


 

 

workneh-hrw-e1478300977613-620x310

ከሰብዓዊ መብቶች ጋር በምንም ዓይነት መልኩ የማይተዋወቀው፤ መተዋወቅና መግባባትም የማይችለው ህወሃት “የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን” ብሎ ባቋቋመው ጽ/ቤቱ አማካኝነት በሰኔ 2008ዓም “በኦሮምያ ክልል የተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት በፀጥታ ኃይሎች የተወሰደው እርምጃ አስፈላጊና ተመጣጣኝ ነበር” በማለት ዘገባ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ ይህ በቃል “ለፓርላማው” የቀረበው ሪፖርት እስካሁን ድረስ ይፋ አልተደረገም፡፡ የሂውማን ራይት ዎችም እስካሁን በተደጋጋሚ ኢህአዴግ ሪፖርቱን “እንዲያወጣ” ጥሪ ሲያስተላልፍ ቆይቷል፡፡ ጌታቸው ረዳ ከሂውማን ራይትስ ተመራማሪ ፊሊክስ ሆርን ጋር በአልጃዚራ ላይ በቀረበ ጊዜ ሰብዓዊ መብት ድርጅቱን በመወከል ሚ/ር ሆርን ኢህአዴግ ሪፖርቱን ይፋ እንዲደርግ በይፋ ጠይቀዋል፡፡ አሁን ደግሞ የመብት ድርጅቱ በወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” በኩል ለህወሃት/ኢህአዴግ በጻፈው ግልጽ ደብዳቤ “የራሱ ፓርላማ ሰዎች ያላነበቡትን ሪፖርት” ይፋ እንዲያደርግ ኢህአዴግን ተገዳድሯል፡፡

ለዓመታት በሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት – ሂውማን ራይትስ ዎች – ላይ የስድብ ናዳ ሲያወርድ የነበረው ህወሃት ከሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ግልጽ ደብዳቤ ደርሶታል፡፡ የመብት ተሟጋቹ ድርጅት ህወሃት/ኢህአዴግን ለምታደርሱት ወንጀል ያለንን ማስረጃ ይዘን ቤታችሁ ድረስ መምጣት እንችላለን ወይም ከተወካያችሁ ጋር ሌላ አገር ላይ መገናኘት እንችላለን ብሏል፡፡

felix-horne

ፊሊክስ ሆርን ስለኢትዮጵያ ጉዳይ በአውሮጳ ፓርላማ

የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ግልጽ ደብዳቤውን የላከው አሁን ለተሾመው ወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” ሲሆን የደብዳቤው ሃሳብ ትኩረት ያደረገው ቴድሮስ አድሃኖም ከቀድሞ ሥልጣኑ ከመነሳቱ በፊት ስለ መብት ተሟጋች ድርጅቱ በተለይም በኢትዮጵያ ላይ ምርምር ስለሚያደርጉት ፊሊክስ ሆርን ነው፡፡ በOctober 22, 2016 (ጥቅምት 12፤2009) ስለ ፊሊክስ ሆርን በተለቀቀው ረጅም ጽሁፍ ላይ ህወሃት በተመራማሪው የሚቀርቡትን የጽሁፍ፣ የቪዲዮ መረጃዎችና መግለጫዎችን በሙሉ ኮንኗል፤ማስረጃ ሳያቀርብም ሃሰት ናቸው ብሏቸዋል፡፡ ከዚህም አልፎ “ሂውማን ራይትስ ዎች በኢትዮጵያ የተውቃውሞ አመጽ እንዲነሳ ያደፋፍራል” በማለት ድርጅቱንም ዘልፏል፡፡

ለዚህ የህወሃት ዘለፋ ምላሽ ይሆን ዘንድ ዛሬ November 4, 2016 (ጥቅምት 25፤2009) ድርጅቱ በላከው ግልጽ ደብዳቤ በቴድሮስ አማካኝነት የተለቀቀውን የህወሃት ክስ ዕርቃኑን አስቀርቶታል፡፡ የመብት ድርጅቱ ሥራውን “በዓለም ዙሪያ በ90 አገራት ውስጥ” እንደሚያከናውን በመጥቀስ በሌሎች አገሮች እንደሚደርገው በኢትዮጵያ ላይ ማንኛውንም አቢይ ሪፖርት ለሕዝብ ይፋ ከማድረጉ በፊት የግኝቶቹን ማጠቃለያ፣ የተሰጡትን የእርምት ሃሳቦችን በተመለከተ አስተያየት በመጠየቅ ኢትዮጵያን በግፍ እየገዛ ላለው ህወሃት ሲያቀርብ እንደኖረ ገልጾዋል፡፡ ሆኖም እስካሁን ድረስ ይህ ነው የሚባል ቀጥተኛ የሆነ ይፋዊ ምላሽ ከህወሃት/ኢህአዴግ እንዳላገኘ በደብዳቤው አውስቷል፡፡

ድርጅቱ ባለው አሠራር መሠረት መረጃ የሚያቀብሉትን ግለሰቦች ማንነት ይፋ እንደማያደርግ የገለጸ ሲሆን ይህ ደግሞ የአሠራር ጉዳይ ብቻ ሳይሆን መረጃ ሰጪዎቹ በህይወታቸው ላይ አደጋ እንደሚደርስ በግልጽ በመናገራቸውና ህይወታቸው hrw-e1453960284186-300x148ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን አስረድቷል፡፡ የጥቃት
ሰለባዎችን ብቻ በማነጋገር ዘገባ እንደማያቀርብ የተናገረው ድርጅት ከእነርሱ ከሚገኘው መረጃ በተጨማሪ የራሱን የሆነ ምርመራ እንዴት እንደሚደርግና ዘገባ እንደሚያጠናቅር በየጊዜው በሚወጣው ሪፖርት ላይ በግልጽ እንደሚያሰፍል ተናግሯል፡፡ ሆኖም ግን ማስተካከያዎች ካሉ ዘገባው እንዲሻሻል ማረሚያ መቀበያ ገጽ ከቀድሞ ጀምሮ አዘጋጅቶ ማስቀመጡን አስታውቋል፡፡ ከዚህ ሌላ ግን ህወሃት ለስድስት ወር ባወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት ለማንኛውም ድርጅት መረጃ ማቀበል እንደ ወንጀል በመታየቱ የመረጃ አቀባዮቻችን ማንነት በምሥጢር እንድንይዝ ያስገድደናል በማለት የመብት ድርጅቱ ህወሃትን በራሱ ህግ አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል፡፡

ካለፈው ህዳር 2008ዓም ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ እየደረሰ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት አስመልክቶ ዓለምዓቀፋዊ ምርመራ እንዲደረግ የተጠየቀ መሆኑን ያስታወሰው ደብዳቤ በሰኔ 2008ዓም ህወሃት/ኢህአዴግ በራሱ “ፓርላማ” በቃል የተናገረውን ዘገባእስካሁን ይፋ አለማድረጉን በድጋሚ አስረድቷል፡፡ “በኦሮምያ ክልል የተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት በፀጥታ ኃይሎች የተወሰደው እርምጃ አስፈላጊና ተመጣጣኝ ነበር” በማለት በህወሃት ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የቀረበው ዘገባ ማንም የጽሁፍ ሪፖርቱ እንዳልደረሰው ሂውማን ራይትስ ዎች አስታውቋል፡፡ የመብት ተሟጋች ድርጅቱ ያነጋገራቸው “የፓርላማ” አባላት የጽሁፍ ሪፖርቱ ያላዩትና ያልደረሳቸው መሆኑን የጠቀሰው ደብዳቤ ሌሎች ተመሳሳይ የመብት ጥሰቶችን የሚዘግቡ ድርጅቶች ከሚያወጡበት የአዘጋገብ ስልት
በተለየ መልኩ በህወሃት/ኢህአዴግ “የተወሰደው እርምጃ አስፈላጊና ተመጣጣኝ” በሚል በዘገባው የተሰጠው የተዛባ ehrc-e1459118494443-300x148ድምዳሜ በዘገባ አቀራረብ ስልት ልዩ እንደሚያደርገው ጠቁሟል፡፡ ስለዚህ ይላል ደብዳቤው፤ “በጽሁፍ የታተመ ዘገባ በእርግጥ ካለ ለሕዝብ ይፋ እንድታደርጉት አጥብቀን እናስገነዝባችኋለን” በማለት ሂውማን ራይትስ ዎች በድጋሚ ህወሃት/ኢህአዴግን እጅግ የሚገዳደር ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ዓለምአቀፋዊ ምርመራ እንዲካሄድ አሁንም ጥያቄውን ያቀረበው ድርጅት እንዲህ ዓይነቱ ምርመራ በኤርትራ፣ በቡሩንዲና በደቡብ ሱዳን እንዲካሄድ ድርጅታችን ይፋ ሲያደርግ ህወሃት/ኢህአዴግ በፍጥነት ድጋፍ መስጠቱን በማስታወስ አሁንም የሺዎች ሰዎች ላይ የደረሰው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ፍትህና ተጠያቂነት እንደሚያስፈልገው በግልጽ አስረድቷል፡፡

በመጨረሻም ይህ በአውሮጳ ኅብረት የሂውማን ራይትስ ዎች ዳይሬክተር የተላከው ደብዳቤ እየተፈጸ ስላለው የመበት ረገጣ በሌላ አነጋገር ህወሃት እየፈጸመ ላለው ወንጀል ያለንን ማስረጃ ይዘን ቤታችሁ ድረስ መምጣት እንችላለን ወይም ከተወካያችሁ ጋር ሌላ አገር ላይ መገናኘት እንችላለን በማለት ደብዳቤው ተግዳሮቱን ይፋ አድርጓል፡፡

በጄኔራልነት ማዕረግ የፖሊስ ኃላፊ በመሆን ከዚያም በፊትም ሆነ በኋላ የሰብዓዊ መብቶችን ሲጨፈላልቅ ለመጣው ወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” ይህ ደብዳቤ “ሹመት ያዳብር” እጅ መንሻ አይደለም በማለት ቅድመ ግምት አስቀማጮች ለጎልጉል አስታውቀዋል፡፡ እንዲያውም ሂውማን ራይትስ ዎች በዚህ መልኩ ህወሃት/ኢህአዴግን በመገዳደር የላከው ደብዳቤ ግፍ በመፈጸም ለከፍተኛ ሹመት የበቃውን የወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ”ን “ዘንዶ” ቀን ጠብቆ የሚያወጣ “አሣ ጎርጓሪ” ደብዳቤ እንዳይሆን በማለት እነዚሁ አስተያየት ሰጪዎች ለጎልጉልአስረድተዋል፡፡

የሞተው ልጄ ሞቷል፤ ያሉትን መልሱልኝ” ወ/ሮ ሎሚ ዋቀዮ


e7147f60-9e5b-474b-b7c0-f278b715a969_w987_r1_s

የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው በምስራቅ ሸዋ ዘን ቦሰት ወረዳ የሚገኙ ወ/ሮ ሎሚ ዋቀዮ የተባሉ እናት አንድ ልጃቸው እንደተገደለ ሁለቱ እንደታሰሩና አንዱ በእጅጉ መደብደቡን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በኢትዮጵያ ለስድስት ወር አስቸኳይ ጊዜ ከታወጀ አንድ ወር ሊሞላው ጥቂት ቀናት ይቀሩታል። ይህ ዐዋጅ ይፋ ከተደረገ በኋላ ሰዎች ከየቦታው እየተለቀሙ እንደሚታሰሩ በተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና በሰባዊ መብት ተሟጋቾች ጭምር ሲነገር ቆይቷል።
ወ/ሮ ሎሚ ዋቀዮ በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ ቆምቤ ጉግሳ በተባለ መንደር ነዋሪ እንደሆኑ ይናገራሉ። የ65 ዓመት አዛውንት ናቸው። ባለቤታቸው ደግሞ የ74 ዓመት አዛውንት መሆናቸውን ገልጸውልናል።
እንደ ወ/ሮ ሎሚ ገለጻ አራት ልጆች ነበራቸው። አቢቲ ደጃሳ የተባለው ልጃቸው አርሶ አደር ነው። ደሜ የተባለው ልጃቸው ደግሞ አዳማ ሥራ ፍለጋ ሄዶ እንደነበር ይገልፃሉ። ንጉሴ እና አንድ ትንሽ ልጅ ነበራቸው። አሁን ደሜ እና ንጉሴ መታሰራቸውን ሰምተዋል ንጉሴ የታሰረው “ወለንጪቲ ነው” ብሎ ሰው እንደነገራቸው ይገልፃሉ።
የሰላሳ ዓመት ወጣት አቢቲ ደቻሳ ለስብሰባ ይፈለጋል ተብሎ ከተወሰደ ጥቅምት 12 ቀን 2009 ዓ.ም አስክሬን እንደመጣላቸው ይናገራሉ።
“አንዱን በሞት አጣሁ። አሁን አንድ ሰው አብሮኝ የለም። ቤቴ ባዶውን ቀርቷል። ደካማ ነኝ” የሚሉት ወ/ሮ ሎሚ ዋቀዮ “የሞተው ልጄ ሞቷል፤ ያሉትን መልሱልኝ” ሲሉ ይጠይቃሉ።
የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ይህን በተመለከተ የደረሰን ሪፖርት የለም ብለዋል።

የሳሞራ ታማኝ የአድዋው ተወላጅ ሜ/ጄኔራል መሃመድ ኢሻ የአማራ ምድር ኮማንድ ፖስቶች አዛዥ ሆኖ ተሾመ


mohamed-ishaአለበል አማረ እንደዘገበው
ጄኔራሉ የአድዋ ተወላጅ ሲሆን የጄ/ል ሳሞራ የቅርብ ታማኝና እስከ 2008 አጋማሽ የአግአዚ ክ/ጦር ዋና አዛዥ የነበረ ነው። ጄኔራሉ ምንም ፊደል ያልቆጠረ፣ ከህወኃትና ከሳሞራ ሌላ እምነት የለለው ድፍን ነው። ጀኔራሉ በ23/02/09 ከሌላው ከሜቴክ በለስ ስኩአር ፋብሪካ ስ/አስኪያጅ ከሆነው ኮ/ል ገ/ሚካኤል ሃጎስ ጋር በመሆን በአዊ ዞን ጃዊ ወረዳ ህዝባዊ ስብሰባ ጠርተው ነበር፤ በስብሰባው የአዊ ዞን አስተዳዳሪወች፣የጃዊ ወረዳ ካቢኔዎች፣በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት፣በብረታ ብረት ኮርፖሬሽን ሜቴክ አመራር ሰራተኞች እና ከግንባታ ድርጅቶችና የአካባቢው ነዋሪወች የተካተተበት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ ማብራሪያና ማስፈራሪያ ለመስጠት ያለመ ነበር።
በስብሰባው በጀኔራሉ በአዠንዳነት ከተገለፁ ነጥቦች፤
1. በሁሉም የአማራ ምድር በዞን እና በወረዳ ደረጃ ኮማንድ ፖስት ማቋቋምና በነውጥ(በነሱ አማርኛ) ተሳታፊ የነበሩ ግለሰቦችን በሚደረገው ጥቆማና ማጣራት ለፍርድ ማቅረብ፤ጥፋተኛ ነን ብለው አምነው ተጸጽተናል ብለው ራሳቸውን አጋልጠው ለሚቀርቡት ደግሞ እንደ ጥፋታቸው መጠን ታርመውና ታድሰው መኖር እንዲችሉ ማድረግና ይህንንም ህዝቡ እንዲያውቀው ለማድረግ፤
2. ማንኛውም አካል ነውጠኞችን በማጋለጥ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ ለህዝቡ ለማቅረብ፤
3. በህዝባዊ አመጹ ንብረታቸው የወደመባቸው ግለሰቦችን ካሳ ለመስጠትና ወደነበሩበት ለመመለስ ዞኑ እንቅስቃሴ መጀመር እንዳለበት ለመንገርና ይህም የህብረተሰቡን ተሳትፎ የሚሻ በመሆኑ ህዝቡን ለመቀስቀስና መዋጮም እንዲያዋጣ ለመንገር፤
4. በአዋጁ መሰረት እያንዳንዱ ከያዘው ሞባይል ጀምሮ በአዋጁ የተቀመጡትን እገዳዎች ማክበር እንዳለበትና እራሱንና አካባቢውን ከነውጠኞች እንዲጠብቅ ትዕዛዝ ማስተላለፍ ነበር፤
በዚህ መሃከል በነበሩ ዲስኩሮች ጄነራሉ ያለፋ ነግስታቶቻችን ለመተቸት ሲሞክር ተደምጧል። በተለይም ህዝቡን ቋቅ ያሰኘና እና ያስጠየፈ ነገር ቢኖር ጀኔራል ተብየው የሚያወሩትን የማያውቁና እና በርሳቸው አፍ እምዬ ምኒልክን ለመተቸት መሞከራቸው ነበር። የአሜሪካ የምርጫ ሂደትም በዚሁ ወደል ማህይም በጥቂት ቢልየነሮች የሚመራ መንግስት፣ለባለሃብት የቆመ መንግስት እያለ ለመተቸት ሲውተረተር ሲታይ ተሰብሳቢው በሳቅ እና በጩሀት አቁአረጠው ።
በመጨረሻም ተሰብሳቢው ለጀኔራል ተብየው በርካታ ጥያቄወች በማንሳት ጀኔራሉ መመለስ ተስኗቸው ሲቁለጨለጩ መዋላቸውና መጨረሻም ተሰብሳቢው ስብሰባውን በራሱ ኃይል በትኖት ወደ ቤቱ መሄድ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አረጋግጧል።

የቅማንትን ሕዝብ ከቀሪው የአማራ ህዝብ ጋር ለማጋጨት የትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት አዲስ ስልት ቀይሶ እየተንቀሳቀሰ ነው ተባለ


የአማራ ድምጽ ራድዮ እንደዘገበው የቅማንትን ሕዝብ ከቀሪው የአማራ ህዝብ ጋር ለማጋጨት የትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት አዲስ ስልት ቀይሶ እየተንቀሳቀሰ ነው ተባለ:: የዚህን ዜና ዝርዝር እና የተጨማሪ የራድዮውን የዛሬ ዜናዎች ያድምጡ::

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ መሪዎች በመጪው አርብ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ!!


ethiopian-national-movement-meeting2-324x160

ባሳለፍነው እሁድ ኦክቶበር 30 2016 ምስረታውን በመሪዎቹ የፊርማ ስነ-ስርአት ይፋ ያደረገውና በአራት ድርጅቶች የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ መሪዎች በመጪው አርብ ኖቨንበር 4 2016 በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ናሽናል ፕሬስ ክለብ በንቅናቄው አላማና ራእይ ዙርያ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ንቅናቄው ባዘጋጀው በዚህ ጋዜጣዊ ጉባኤ ላይ አቶ ሌንጮ ለታ፡ዶ/ር ዲማ ነገዎ፡ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ፡ አቶ ሙሉነህ እዩዔልና አቶ በቀለ ወያ እንደሚገኙና ማብራርያ እንደሚሰጡ ሲታወቅ በታዛቢነትም አቶ ሀ/ገብርኤል አያሌው እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ በተጨማሪ በሚደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተለያዩ አለም አቀፍ ሽልማት ተሸላሚ የሆነችው ጋዜጠኛና አክትቪስት እሪዮት አለሙ እንደምትገኝ ሲታወቅ ይህ በናሽናል ፕሬስ ክለብ የሚደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ አርብ ኖቨንበር 4 ከቀኑ 12፡15pm እስከ 2፡30pm ድረስ የሚቆይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የሀገር ሉአላዊነት ማስከበር፡ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት ማረጋገጥና እድገትና ብልፅግናን በማምጣት የፌደራል ስርአት መገንባት በሚሉ ሶስት ዋና ዋና አላማዎች የያዘውና በአራት ድርጅቶች የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ በወያኔ እየተፈፀመ ያለውን የጅምላ ግድያ፤ እሰርና ወከባ አጥብቆ ያወገዘ ሲሆን የታወጀውም ህገ-ወጥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለወራት ሀገሪቱን ሲንጥ የቆየውን ህዝባዊ እንቢተኝነት በሀይል ለመጨፍለቅ ታስቦ የታወጀ መሆኑንና ይህ አዋጅ በሀገሪቱ ላይ ዘላቂ መረጋጋትን ሊያመጣ እንደማይችል አስታውቆ  ለአሜሪካና የአውሮፓ መንግስታት በሀገራችን ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ለዚህ የወያኔ የሽብር አገዛዝ  ድጋፍ ከማድረግ ይልቅ  ከንቅናቄው ጋር በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ ማድረጉም ለማወቅ ተችሏል፡፡

2000 ብቻ ነበር የታሰሩት እነሱንም ፈትቻለሁ ይላል ሕዉሐት!


ethiopian-federal-police-attack-young-women-143526047284kng-e1478067757691-324x160አባይ ሚዲያ ዜና

በኦክቶምበር 8 2016 በታወጀዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጀ ከታወጀ ጀምሮ የታሰሩት 2000 ብቻ እንደሆነና እነሱንም ሕዉሐት እንደለቀቃቸዉ አገር ቤት ባሉት ሚዲያዎች መግለጫ መሰጠቱን ዋሽንግተን ፖስት  አስታወቀ።
በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አስከትሎ ከ40ሺ የበለጡ በኦሮሞ ማሕበረሰብ ብቻ መታሰሩ የተዘገበ ሲሆን አዲስ አበባንና ሌሎች የአማራዉን ማሕበረሰብ ጨምሮ ታፍሰዉ ወደ ማሰቃያ የተወሰዱት ኢትዮጵያዉያኖች ቁጥር ከ 50ሺ በላይ ሊደርስ እንደሚችል ይገመታል።
ባለፈዉ እሑድ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተክትሎ ታስረዉ የነበሩትን 2000 ወጣቶች መፈታታቸዉን ለሚዲያዎች ሲገልፁ ሌሎች ቁጥራቸዉን ለመናገር ፈቃደኛ ባይሆኑም በወታደራዊ ማሰቃያዉ ካምፕ ዉስጥ የሚሰቃዩ እስረኞች እንዳሉ የገለፁት የመከላከያ ሚኒስትሩ አያይዘዉም ከ አዲስ አበባ 1500 ሕጋዊ ያልሆኑ ጠብ መንጃዎችን መስብሰብ መቻላቸዉንም ገልፀዋል።
ከኢሬቻ እልቂት በኋላ በኦሮምያም ይሁን በአማራዉ አካባቢ መረጋጋት እንደሌለና በተቃራኒዉ በነዚህ ቦታዎች ችግሮች እየተበራከቱ መምጣታቸዉን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ሰሞኑን ብቃት የለህም ተብሎ ከስልጣኑ የተገለለዉ ጌታቸዉ ረዳ ስልጣኑን ከመልቀቁ በፊት ሰኞ ዕለት በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ አሁን በኢትዮጵያ ያለዉን ችግር መፍትሔ ለመስጠት የኃይለማርያም ካቢኔ አዳዲስ ሚኒስትሮችን እንደሚመድብ ቢገልፅም አብዛኛዉን በተቃዋሚ በኩል ያሉት የፖለቲካ ሰዎች ግን ይህ በምንም ዓይነት በኢትዮጵያ ላይ የተጋረጠዉን ፈተና ሊመልስ የማይችል መሆኑን ይስማሙበታል። ሕዉሐት እዉነተኛ መፍትሔ ካሰበ መፍትሔዉ ሊሆን የሚችለዉ ስልጣኑን መልቀቅ ብቻ ነዉ የሚለዉ ሁሉንም የሚያስማማ ነዉ ሲሉ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል።
የሕዉሐት ፕሬዚደንት የሆኑት አቶ ሙላቱ ተሾመ ችግሩን ለመፍታት የፖለቲካ ተሃድሶ እንደሚደረግ ቢገልፅም የተካሔደዉ አዳዲስ ባለስልጣናትን በመሾም የተጠናቀቀዉ ይኸዉ ተሃድሶ ከድጡ ወደ ማጡ የተሔደበት መሆኑን ብዙዎች የሚስማሙበት መሆኑም ታዉቋል። –
ናትናኤል ኃይለማርያም

አሁን የደረሰ ዜና…..ዳባት…ወያኔ ጋር ትንቅንቅ


ሰሜን ጎንደር ዳባት ከተማ ላይ የጅምላ እስርና ስቃይ እየተፈፀመ ነው። ከተማዋ በትግሬ አዛዥ በሚመራ አጋዚ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ውላለች።
*ወጣት ሽማግሌ ሳይሉ በጅምላ በየቤቱ እየገቡ እየደበደቡ እያሰሩ ነው። በጣም ብዙ ወጣት እያመለጠamhara ዱር ቤቴ እያለ ነው። ህዝቡ በጣም ተበሳጭቷል። ወያኔ የጎንደር አብዮት መነሻ በሆነችው በዳባት ላይ የበቀል ዱላውን እየሰነዘረ ነው። የአጋዚ ሰራዊት በአቅራቢያ ከተሞች የፍተሻ ኬላ ከፍቶ ወጣት እያሰሩ ስለሆነ ጥንቃቄ ይደረግ።
*ወያኔ በለስ ቀንቶት ስልጣን ላይ ከመውጣቱ በፊት ዳባት ታሪካዊ የወልቃይት ጠገዴ የወረዳ ዋና ከተማ ነበረች።
ከቦታው ያናገርናቸው ዳባቴዎች ይህ አፈና ቁርጠኝነታችንን ይጨምራል ወያኔን እስከሞት እንጋፈጣለን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በያለበት ጠላት ላይ በመረባረብ ወያኔን እንደምስስ ብለዋል። የጀግና ቃል። ይህን እየዘገብኩ እንኳን እኔኑ አይዟቹህ የሚሉ ጀግኖች! እባካቹህ ደጀን እንሁናቸው።
ስማቸው የደረሰኝን ታሳሪዎች እያጣራሁ እለጥፋለሁ… እስካሁን ባለኝ መረጃ የሚከተሉት ታስረዋል::

1. አዳሙ መኩሪያው
2. አመሀ ማሞ
3. መላኩ ፉንቱ
4. አቶ ምትኬ እንዳለ (ታዋቂ የሃገር ሽማግሌ)
5. ሚኪያስ ንጉሴ
6. እንዳልክ ተስፉ (ርእሰ መምህር)
( ሙሉነህ ዮሃንስ)

ሰበር ዜና   የአማራ ወጣቶች በባሕር ዳር እርምጃ ወሰዱ


የህዝብን ጥያቄ ወደ ጎን በማሸሽ መልስ የማይሰጠው ወያኔና ብአዴን ትምህርት የሚወስዱበት እርምጃ በባህር ዳር ወጣቶች ተወሰደባቸው። ከቀናቶች በፊት የተለያዩ የማህበር ክፍሎችና ነጋዴዎች ከእስር እንዲለቀቁ የጠየቁት ወጣቶች ለ5 ቀን የሰጡት ማስጠንቀቂያ ምላሽ ባለማግኘቱ እርምጃ መወሰዳቸውን አስታወቁ። እርምጃውም ቀበሌ 03 በሚገኘው የባለስልጣኖች መኖሪያ ኪቢአድ ግቢ እና የባህር ዳር መዘጋጃ ቤት( ከተማ አተዳደር)በተመሳሳይ ሰአት ከምሽቱ 2 ሰዓት የቦንብ ፍንዳታ ተፈጽሟል። ይሄንን ተከትሎ አካባቢው ላይ ከፍተኛ የሆነ ውጥረት ከመንገሱም በላይ አምቡላንሶች ሲሯሯጡ ይታያል።
አሁንም ወጣቶቹ ይናገራሉ የታሰሩ ወንድሞቻችንና ነጋዴዎች እስካልተፈቱ ድረስ ይሄ ጥቃት በሰፊው እና በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚካሄድ አስጠንቅቀዋል። ከዚህ በዃላ ሊደረግ የሚገባውን እርምጃና ማስጠንቀቂያ ከቀናቶች በዃላ ያስታውቃሉ።

ኢሳት ሰበር ዜና) — በባሕርዳር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ የነዋሪዎችን እና ነጋዴዎችን መታሰር በመቃወም የከተማዋ ወጣቶች የቦምብ ጥቃት ፈጸሙ።

Ethiopia: State of Emergency Risks New Abuses(Human rights wach)


(Nairobi) – An Ethiopian government directive under a state of emergency contains overly broad and vague provisions that risk photo_se_2triggering a human rights crisis, Human Rights Watch said today in a legal analysis. The government should promptly repeal or revise all elements of the directive that are contrary to international law.

Expand
A woman cries as she attends a prayer session at Biftu Bole Lutheran Church during a prayer and candle ceremony for those who died in the town of Bishoftu during Ireecha, the thanksgiving festival for the Oromo people, Addis Ababa, Ethiopia, October 9, 2016.
© REUTERS/Tiksa Negeri

On October 9, 2016, the government announced a six-month state of emergency following the destruction of some government buildings and private property by demonstrators. Over the past year, security forces have killed hundreds of protesters and detained tens of thousands in two regions where there have been numerous protests over government policies.
“Ethiopia’s state of emergency bans nearly all speech that the government disagrees with anywhere in the country for at least six months,” said Felix Horne, senior Africa researcher at Human Rights Watch. “The state of emergency hands the army new sweeping powers to crack down on demonstrators, further limiting the space for peaceful dissent.”
Related Content
Legal Analysis of Ethiopia’s State of Emergency
Under the new state of emergency, the army can be deployed country-wide for at least six months. The implementing directive prescribes draconian restrictions on freedom of expression, association, and assembly that go far beyond what is permissible under international law and signal an increased militarized response to the situation. The directive effectively codifies many of the security forces’ abusive tactics that Human Rights Watch has documented since the protests began.
The directive includes far-reaching restrictions on sharing information on social media, watching diaspora television stations, and closing businesses as a gesture of protest, as well as curtailing opposition parties’ ability to communicate with the media. It specifically bans writing or sharing material via any platform that “could create misunderstanding between people or unrest.”
It bans all protests without government permission and permits arrest without court order in “a place assigned by the command post until the end of the state of emergency.” It also permits “rehabilitation” – a euphemism for short-term detention often involving physical punishment. Many of these restrictions are country-wide and not limited to the two of Ethiopia’s nine regions where most of the unrest took place.
Under international law, during a state of emergency a government may only suspend certain rights to the extent permitted by the “exigencies of the situation.” Many of the measures, including the restrictions on freedom of expression, assembly, and association go far beyond what is permitted under international law.
The government reports that since the state of emergency began, 1,600 people have been arrested, including about 50 for closing their businesses. Human Rights Watch also has received unconfirmed reports of unlawful killings, mass arrests, and looting of houses and businesses by the security forces. There have been some armed clashes between security forces and unidentified groups. Mobile phone access to the internet has been blocked since October 5. Addis Standard, a monthly English language magazine and one of the few independent publications left in Ethiopia, announced on October 25 that it was halting publication of its print edition due to state-of-emergency restrictions.
Large-scale, and mainly peaceful anti-government protests have been sweeping through Oromia, Ethiopia’s largest region, since November 2015, and the Amhara region since July 2016. Ethiopian security forces have killed more than 500 people during protests over the last year. These protests occurred in a context of the near-total closure of political space.
Protesters have voiced a variety of concerns, including issues related to development, the lack of political space, the brutality of the security forces, and domination of economic and political affairs by people affiliated with the ruling party. The emergency measures send a strong and chilling message that rather than dealing with expressed grievances and ensuring accountability for violence by both government forces and protesters, the government will continue and probably escalate the militarized response.
On October 2, in Bishoftu, a town 40 kilometers southeast of the capital, Addis Ababa, tensions ignited at the annual Irreecha festival – an important Oromo cultural event that draws millions of people each year. Security forces confronted huge crowds with tear gas and fired shots and scores of people then died during a stampede. Since then, alleged demonstrators have damaged a number of government buildings and private businesses perceived to be close to the ruling party, setting some on fire.
The government has in part blamed human rights groups seeking to document violations of international law for the recent unrest. Human Rights Watch has repeatedly called for an independent and credible investigation into the security force response to the protests and to the deaths in Bishoftu.
“Many of the abuses committed by security forces since November 2015 have now been codified under the state of emergency,” Horne said. “Trying to use the legal cover of a state of emergency as a pretext for the widespread suspension of rights not only violates the government’s international legal obligations, but will exacerbate tensions and long-term grievances, and risks plunging Ethiopia into a greater crisis.”

ኮንትራታቸውን የጨረሱ የወያኔ ሰራዊት አባላት አዲስ ኮንትራት አንፈርምም አሉ!


አባይ ሚዲያ ዜና
አክሊሉ ታደሰ

የወያኔ ሰራዊት አባላት የሆኑና የሰባት አመት ኮንትራታቸውን የጨረሱ አዲስ የሰባት አመት ኮንትራት እንዲፈርሙ የቀረበላቸውን ጥያቄ በአባላቱ ተቀባይነት ያለማግኘቱ ሲታወቅ በመከላከያም በኩል በወቅቱ ከሚገኝበት ሁኔታ ሳቢያ ሰራዊቱን ማሰናበት ያለመፈለጉ ታውቋል፡፡

የደረሰን መረጃ እንደሚያስረዳው የወያኔ መከላከያ ሰራዊት አባላት የሆኑ በ1999 ዓ/ምና 2001 ዓ/ም የተቀጠሩ የፈረሙት የሰባት አመት የስራ ኮንትራት በመጠናቀቁ ምክንያት ሁለተኛ ዙር የሰባት አመት ኮንትራት እንዲፈርሙ ደብዳቤ ቢደርሳቸውም በአብዛኛው የሰራዊቱ አባላት እስካሁን ለመፈረም ፈቃደኛ ያለመሆናቸው ይልቁንም ወደ የቤተሰባቸው መመለስ እንደሚፈልጉ ለማወቅ ተችሏል፡፡

መረጃው አያይዞም የመከላከያ ሰራዊቱ አመራር አካላት የምንገኘው በፈታኝ ወቅት ላይ ነው በሚል ኮንትራት የጨረሱትን የሰራዊቱ አባላት አዲሱን ኮንትራት እንዲፈርሙ ለማግባባት ቢሞክሩም እስከአሁን ያልተሳካላቸው መሆኑን ሲያስረዳ በአንፃሩም ሰራዊቱም በዚህ ወቅት ማሰናበት እንደማይችሉ ለአባላቱ የገለጹ መሆኑን ያስረዳል፡፡

በተጨማሪ ኮንትራቱን አንፈርምም ያሉት የሰራዊቱ አባላት በቆይታቸው ሊያገኙት የሚችሏቸውን ማንኛውም ጥቅማ ጥቅም በመከልከል አስገድዶ ለማስፈረም የተለመደው ሙከራ መደረጉ የማይቀር መሆኑን መረጃው ሲያስረዳ በአሁኑ ሰአት የወያኔ ስርአት የገጠመውን ፈተና በሰ ራዊት ሀይል ለመቋቋም በመጣር ላይ መሆኑና ተጨማሪ ሰራዊት መመልመል ያለመቻሉ ተጨማሪ ፈተና በሆነበት በአሁኑ ወቅት ኮንትራታቸው ን በጨረሱ የሰራዊቱ አባላትን በግዳጅ በስራ ለማቆየት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ሊፈጥር የሚችለው ችግር ምልክቶች ከወዲሁ እየታዩ መሆኑንም ጨምሮ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ያደረጉት ጥሪ በመከላከያ ሰራዊቱ ዘንድ ከፍተኛ ተደማጭነትን እያገኘ መምጣቱ ታወቀ!


አባይ ሚዲያ ዜና
ናትናኤል ኃይለማርያም

14670781_1159797437461367_6771257405535668049_nየአርበኞች ግንቦት ሰባትሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሀኑ  ለመከላከያ ሰራዊት አባላት፣የፌደራለ እና የክልል ፖሊስ አባላት፤ለአጋዚ ልዩ ጦር አባላት እና ለሌሎች ስርአቱ ታጣቂዎች ያደረጉት  ጥሪ  በሰራዊቱ ዉስጥ ከፍተኛ መነጋገሪያ  ከመሆኑም በተጨማሪ ሰራዊቱ ከህዝብ ጋር ለመቆም የመጨረሻ ዉሳኔ ላይ እንዲደርስ ያደረገዉ ጥሪ ነዉ ሲሉ እነዚሁ ምንጮች ጠቅሰዋል።የተደረገዉን ጥሪ መቀበላቸዉን ለማመላከት ሀሳባቸዉን የገለጹት የሰራዊቱ አባላት እንዳሉት “ መከላከያዉ የህዝብ ሳይሆን የህዉሀት ቡድን አገልጋይ እየሆነ መምጣቱን ሙሉ በሙሉ ያወቁበት ደረጃ ላይ መድረሳቸዉን እና ሊቀመንበሩ እንዳሉት ሰራዊቱ የቁም እስረኛ ሲሆን በተለይ ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ከተጀመረ ጀምሮ ምን እንደሚያደርግ እና ወዴት እንደሚሄድ የጠራ አቅጣጫ ባለማግኘቱ እና ባለበት ከፍተኛ ጫና የተነሳ አማራጭ በማጣት በሰራዊቱ ዉስጥ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

አክለዉም በአሁኑ ሰአት አዛዦቻቸዉ ድንጋጤ ዉስጥ ከመሆናቸዉ የተነሳ በሰራዊቱ ላይ ያለዉ ቁጥጥር እና ማስጠንቀቂያ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን እንዲሁም ከአንድ ብሄር የሆኑ አባላት ባንድ ላይ ለግዳጅም ሆነ ለስምሪት እንደማይመደቡና በግል ህይወታቸዉ ዉስጥ ስለላን እያካሄዱ ነጻነታቸዉን ፍጹም እንደነጠቋቸዉም ገልጸዋል፡፤በዚህም ምክንያት ከሰራዊቱ መካከል ያሉ አንዳንድ አድር ባይ አባላትን ሳይቀር የሕዉሐት ገደብ ያለፈ ጥርጥር ወደተቃዋሚነት ስለለወጣቸዉ በአሁኑ ሰአት በጥቂት ቁጥር ከሚቆጠሩ የግል ሰዎቻቸዉ በቀር ሰራዊቱ ልቡ ከህዝብ ጎን ሆኗል ብለዋል፡፤  በየጊዜዉ ለግዳጅ ሲወጡ ወደነጻነት ታጋዮች ከነትጥቃቸዉ የሚቀላቀሉ እና በቡድን በመደራጀት በየጫካዉ የሚመሸጉ የሰራዊት አባላት ቁጥር ከቀን ወደቀን እየጨመረ መምጣቱንም አመልክተዋል።

ፕሮፈሰር  ብርሀኑ ነጋ ለሰራዊቱ ያደረጉትን  ጥሪ በርካታ ሰዎች ለዉጥ የሚያመጣ ጥሪ መሆኑን በመግለጽ እነሱን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ መከላከያ ሰራዊቱ ወገኑ ላይ መተኮስ እንዲያቆም እና የመሳሪያ ነጠቃን እና በ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሰበብ የሚደረግባቸዉን የጅምላ አፈሳ እንዲሁም ግድያ በመቃወም ወደጫካ ከገቡ ወጣቶች እና አርሶ አደሮች እንዲቀላቀል ጥሪ አቅርበዉ፤ ከሳምንታት በፊት በፍኖተ ሰላም ከተማ 18 የመከላከያ ሰራዊቶች እና አራት ያጋዚ አባላት ሰራዊቱን ከድተዉ መዉጣታቸዉን አስታዉሰዋል።በተለይ በአማራ ክልል አገዛዙ በስፋት ለማከናወን አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ያለበትን የመሳሪያ  ነጠቃ ሽሽት ወደየጫካዎች በመግባት ላይ ያለዉ ህብረተሰብ እየጨመረ መምጣቱን እና የኮማንድ ፖስት አባላት ወጣቶችን ያለምንም ምክንያት ስለሚያስሩዋቸዉ በፍኖተ ሰላም በከተማዋ ዉስጥ አዛዉንቶች፤ሴቶች እና ህጻናት ብቻ እየቀሩ እንደሆነ ገልጸዋል።

በተያያዘ ዜናም በባህር ዳር ከተማ  ከስድስት ሳምንት በፊት ወቶ የነበረዉና መመዘኛዉ ከ10ኛ ክፍል በላይ የነበረዉ የመከላከያ ምዝገባ ፤ተመዝጋቢ በማጣቱ ምክንያት ማስታወቂያዉ ከወጣ ከሁለት ሳምንት በሗላ መስፈርቱ ወደ 6ተኛ ክፍል ዝቅ ብሎም ባለመሳካቱ በአሁኑ ሰአት ወጣቶች ወደ መከላከያ ቢገቡ ጥቅማጥቅሞችን እንደሚያገኙ ዉስጥ ዉስጡን በቅስቀሳ መልክ እየተወራ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ይህ በእንዲ እንዳለ የክልሉ አየር መንገድ ለአዉሮፕላን አብራሪነት እና ለቴክኒሺያንነት የቅጥር ማስታወቂያ ማዉጣቱን ተከትሎ ምናልባት በስራ አጥነት ሲሰቃይ የከረመዉን ወጣት በዚ መልክ በመመዝገብ ወደመከላከያ ስለጠና ሊወስዱት ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳላቸዉም ጠቁመዋል። የህዋት መንግስት ለመከላከያ  እና ለፖሊስ አባላት መላቀቂያም ሆነ ፈቃድ መጠየቅ እንደማይቻል ቢያስተላልፍም እየከዱ እና እየጠፉ በሚለቁ አባላት ምክንያት አለመተማመን የመጣዉን የሰራዊቱን ቁጥር ለመጨመር በሰበብ አስባቡ በቁጥጥር ስር ያዋላቸዉን ወጣቶች በማባባል እና በማስገደድ ወደ ስልጠና ለማስገባት ሙከራ እያረገ ይገኛል ሲሉም ተደማጠዋል።

ከአመት በፊት ጀምሮ ሰራዊቱን እየለቀቁ የሚሄዱ አባላት ቁጥር  በተለይ ህዝባዊ ትግሉ ከተጀመረ በሁዋላ በመጨመሩ፤የህዋት መንግስት  በየክልሉ የመከላከያ  ሰራዊትነት ምዝገባን ለማካሄድ ከጥሩ የደሞዝ ክፍያ ጋር ጥሪ ቢያደርግም የሚመዘገብለት ማጣቱ በሌሎች አስገዳጅ መንገዶች ወጣቶችን በማታለል በግዳጅ ወደ መከላከያ ያስገባበት ሁኔታ መኖሩን ሲዘገብ መቆየቱ ይታወሳል።  –

ተሰብሳቢውን በእምባ ያራጨው የታማኝ በየነ ንግግር በሚኒሶታ – “ቢያንስ ለቅሷችንን እንኳ በጋራ እናልቅስ”


ጽናት የውውይት መድረክ በሚኒሶታ ባዘጋጀው ሁሉን ያካተተ የውይይት መድረክ ላይ ተወዳጁ አክቲቭስትና አርቲስት ታማኝ በየነ ተገኝቶ ተሰብሳቢውን እምባ ያራጨ ንግግር አድርጓል:: በዚህ ዝግጅት ላይ ከጋምቤላ; ከኦጋዴን; ከኦሮሞና ከአማራ የተወከሉ ተናጋሪዎች የነበሩ ሲሆን በሕዝባችን ዘንድ ያለውን አንድነት ለማጠናከር ወይም በአንድ ላይ ለመጓዝ ሁኔታዎችን ያመቻቹ ንግሮች ተደርገዋል:: ታማኝ በየነ “ቢያንስ ለቅሷችንን እንኳ በጋራ እናልቅስ” ሲል ስለአንድነትና መተባበር አስፈላጊነት ያደረገውን ንግግር ቢያድምጡት ይጠቀማሉ:: ሌሎች እንዲመለከቱትም ያካፍሉት::

ሰበር ዜና – የህወሃት ሰራዊት ባለ ቀይ መስመር የአርማጭሆ ወረዳዎችን ተቀማ!


በልኡል አለም
በጎንደር ሰሜን ምእራብ ኢትዮጵያ፣ በሱዳን ጠረፍ አዋሳኝ በደቡብ ተከዜ አቅጣጫ፣ ሰሜን ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ፣ የላይኛዉ አርማጭሆን ጨምሮ ተሰማርቶ የነበረዉ የህወሃት ጦር በደረሰበት ተደጋጋሚ ጥቃት ምክንያት የጥቃት ወረዳዎቹን ባጠቃላይ እየተነጠቀ ይገኛል።
ጀግናዉን የአማራ ገበሬን ትጥቅ ለማስፈታት ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ያደረገዉ ህወሃት በ14/02/2009 ማምሻዉን የተጠናከረ ኃይሉን ቢያሰማራም በለስ አልቀናዉም! ወደፊት ለማጥቃትpatriotic-ginbot7-fighters የማይመቸዉ የአማራዉ የነጻነት ምድር አርማጭሆ! ጀግናዉ ህዝብ ከነጻነት ሀይሎች ጋር በመተባበር ዙሪያ ገጠም እሳት በህወሃት ሰራዊት ላይ አርከፍክፏል።
ሄሊኮፍተሮች ቢያንባርቁ! ዝቅ ብለዉ ለመብረር እንዳይችሉ የነጻነት ሐይሎች ዙ23 እና ሞርተሮች ከተራራዎች ስርቻ እየተስፈነጠሩ የህወሃትን አየር ሐይል መድረሻ ያሳጡት ሲሆን የጦር መሳሪያ ድምጽ የሰሙ የአካባቢዉ ገበሬዎች ከየአቅጣጫዉ በማጥቃታቸዉ ምክንያት ወደ ሗላ ማፈግፈግ ያልቻለዉን የወያኔ ሐይል አኮላሽተዉታል።
ከፍተኛ መሰዋትነውት በመክፈል ትጥቅ በማቀበልና በመተባበር ድል የቀናቸዉ የነጻነት ሐይሎች ቆላ ድባትን ጨምሮ ዙሪያ ቁልፍ የጥቃት ወረዳዎችን በቁጥጥራቸዉ ስር ማድረጋቸዉን የህወሃት ወታደራዊ አስተዳደር መርዶዉን ዛሬ የተረዳ ሲሆን መልሶ ጥቃት ለመፈጸም የ 25ተኛ እና ሌሎች ተጨማሪ ክፍለ ጦሮች ተዉጣጪ ወታደሮችን እንዲሰማሩ መመሪያ ወጥቷል።
ህወሃት ወያኔ በአካባቢዉ ላይ በቀሰቀሰዉ ጦርነት የቆሰሉ ወታደሮችን በሄሊኮፍተር በማመላለስ ከመጠመዱ ባሻገር ቁጥራቸዉ 200 የሚጠጉ የጦር አባላቱ የነጻነቱን ትግል ከነሙሉ ትጥቃቸዉ ተቀላቅለዋል።
እጁን ለነጻነት ሐይሎች በፍቃዱ የሰጠ በቅጽል ስሙ ወዲ ሳንጃ የተባለ አንድ የ24ተኛ ክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራር እንድተናገረዉ
“የምንዋጋዉ አርሶ ካበላን ካሳደገንና ካጎለበተን አባት ገበሬ ጋር ነዉ፣ ጸጉሩ ሸበት ያለ ፊቱን ቅጭም አድርጎ በብርቱ አይኖቹ አሻግሮ የሚመለከት አዛዉንት አባት ላይ ከመተኮስ እጅ መስጠቱና ወደ ህወሃት መዞሩ አዋጪ ሆኖ አግኝቼዋለዉ ” በማለት የገበሬዉን ብቃት አረጋግጧል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

In Ethiopia, Posting About the Country’s Crisis on Facebook Could Land You in Jail


1_sn9il_8iubmx-tig6pbdbwby PETER DOERRIE

In Ethiopia, Posting About the Country’s Crisis on Facebook Could Land You in Jail Crackdown on social media follows a bloody campaign by the state by PETER DOERRIE
The Ethiopian government declared a nationwide state of emergency in October 2016 that severely restricts democratic rights. Rallies and public gatherings are now prohibited without prior permission, and the security forces declared a right to detain and search people without a court order.
Siraj Fegessa, Ethiopia’s defense minister and head of the ominously named “Command Post” tasked with dealing with country’s ongoing political crisis, declared that watching or listening to Voice of America and Deutsche Welle is illegal, in addition to banning any contact to groups labeled as terrorists.
The regime has placed a special emphasis on limiting the flow of information out of the country. Want to post an opinion about what is going on in Ethiopia on Facebook? If you do so within the country, you could face a three-to-five year jail sentence.
The Ethiopian government has also restricted all foreign diplomats to the capital and its immediate environs, limiting one of the most important ways to observe the development of the often violent crisis, which erupted one year ago as protesters demanded reform to the country’s one-party rule.

1_99j7i9ng1hkuhn5tmvbuwa

Foreign media has been restricted from covering the protests from the beginning, and the author’s visa request was recently denied by Ethiopia without comment, as were similar requests by a number of colleagues.
The government has also seemed to severely restrict access to the Internet. Statistics provided by Google show that traffic to YouTube (a Google property) fell off a cliff in early October. These harsh new laws are not a good sign for those who hoped that tensions and violence in Ethiopia would subside
The 40th anniversary rally ofEthiopia’sruling party in 2015. Rwandan government photo
The Ethiopian regime is facing its greatest challenge since it took power in 1991.
Twenty-five years ago, the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front swept into power — and was popular — as it replaced thoroughly brutal and corrupt Marxist regime that reduced Africa’s only uncolonized nation to famine and poverty.
The EPRDF implemented a federalist constitution and a parliamentary democracy. But while allowing a greater space to the political opposition and strengthening human rights, the ruling party never risked giving up its control over the state.
While the EPRDF is officially a coalition of several ethnic political parties, its Tigrayan members — who were instrumental to the insurgency that brought it power — have long dominated the party.
Over time, the Tigrayan People’s Liberation Front further strengthened its control over the coalition and the state’s political institutions. It further took control of the military — a key U.S. ally and one of the better equipped and trained forces on the continent.
The protests that erupted in November 2015 can be traced to the perceived dominance of Tigray politicians, businessmen and officers over Ethiopian affairs. Since those protests began, Ethiopia’s security forces have killed more than 500 people.
Originally the protests were staged largely by Oromo youths, but Amhara protesters have since joined them — uniting the country’s two largest ethnic groups. They share demands for greater participation in the political process, and the devolution of resources and rights to Ethiopia’s ethnic-based federal states.
The protests have been overwhelmingly peaceful, with no organized and violent anti-state movement being apparent. The regime could acquiesce to the protesters’ demands and open a dialogue about the future of Ethiopia’s political system. However, the state of emergency and its draconian rules make clear that this won’t be happening any time soon.
Instead, it is likely that the new legal instruments, and reduced scrutiny from abroad, will give the regime license to increase the level of violence against its opponents.
The opposition, meanwhile, has little hope of resisting such a coordinated effort from the state. The regime has successfully undermined opposition groups in recent years, leaving the protesters without a national platform or individuals to organize around.
U.S. Secretary of State John Kerry shakes hands with Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn at the 2014 U.S.-Africa Summit. State Department photo
A continuation of the crisis will severely harm Ethiopia’s economy. Some investors are already pulling out, throwing one of Africa’s few economic success stories into jeopardy. But the regime might decide that the risk is worth it, hoping to come out of the conflict with even stronger control over the country.
Currently, there is only one strategy that would almost certainly force the government to change course — a coordinated withdrawal of international development assistance.
Ethiopia received more than $3.5 billion in development assistance in 2014. In 2011, official development assistance amounted to more than 100 percent of central government spending.

But international donors are exceedingly unlikely to pull the plug. German chancellor Angela Merkel visited Ethiopia in October 2016 to — yes, you’re reading this correctly — inaugurate the African Union’s new headquarters for peace and security operations.
While she criticized Ethiopia’s democratic deficits, she made no threat to withdraw resources. On the contrary, Merkel proposed to support the training of Ethiopian security forces “so that protests won’t result in so many deaths.”
Merkel, at least, took the time to meet with some representatives of the opposition. U.S. president Barack Obama refused to do so last year, instead calling the Ethiopian government “democratically elected.”
This statement came to the consternation of human rights organizations, which pointed out that the ruling party currently holds 100 percent of the seats in Ethiopia’s parliament.
The reason for this blatant refusal to take action is simple — faced with the threat of terrorism in Ethiopia’s neighbor Somalia, and several civil wars in the region, Western powers are betting on the Ethiopian regime to pull through this crisis and provide the region with an “anchor of stability,” in Merkel’s words.

countries, this primarily means holding back refugees who would otherwise make their way across the Mediterranean, potentially further destabilizing the political landscape in the European Union — already battered by the Brexit and a surge of right-wing populist movements.
It’s a risky gamble. While the Ethiopian regime is unlikely to falter in the short term, further entrenching its control over the Ethiopian state and military will be practically impossible to reverse at a later point.
No regime lasts forever, and if the events of the Arab Spring are any guide, the most “stable” regimes also create the biggest messes.
source  tps://warisboring.com

በባህርዳር ዙሪያ ጢስ አባይ ሁለት የአጋዚ ወታደሮች መገደላቸውን ዕማኞች ለኢሳት ገለጹ


ኢሳት (october 21 ፥ 2016)

agaziበአማራ ክልል የባህር ዳር ዙሪያ ከተማ በሆነችው ጢስ አባይ በአንድ ጊዜያዊ ካምፕ ላይ ራሳቸውን ያደራጁ ሃይሎች በፈጸሙት ጥቃት ሁለት የአጋዚ ወታደሮች መገደላቸውን ዕማኞች ለኢሳት ገለጹ።Ethiopia’s killing squad
ሃሙስ ምሽት በወታደራዊ ጣቢያው ላይ የተቃጣውን ጥቃት ተከትሎ ወደ ጢስ አባይ ከተማ ተጨማሪ የመንግስት ታጣቂ ሃይል በመሰማራት ላይ መሆኑን ከኢሳት ዜና ጋር ቃለምልልስን ያደረጉ ምንጮች አስረድተዋል።
ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት ወደ 30 የሚደርሱ ወታደሮች በስፍራው እንደነበሩ የተናገሩት ምንጮች ጥቃቱን ከፈጸሙት አካላት በኩል አንድ ታጣቂ ጉዳት እንደደረሰበት ተመልክቷል።
ራሳቸውን አደራጅተዋል የተባሉ ሃይሎች በፈጸሙት ጥቃት የተገደሉት ሁለት የአጋዚ ወታደሮች በጊዜያዊ ወታደራዊ ካምፑ ቅጥር ግቢ መቀበራቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አስረድተዋል።
ሃሙስ ምሽት ለአንድ ሰዓት ያህል ጊዜ የተካሄደውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ በባህር ዳር ከተማና ሌሎች አጎራባች አካባቢዎች ያሉ የገዥው ስርዓት ሃይሎች ወደ ጢስ አባይ እንዲሰማሩ መደረጉም ታውቋል።
መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ ገለሰቦች በእጃቸው የሚገኝ የጦር መሳሪያን እንዲያስረክቡ ጥሪ ማቅረቡ የሚታወስ ነው።
ይሁንና በርካታ አርሶ አደሮችና ነዋሪዎች መንግስት ትጥቅ ለማስፈታት የያዘውን እቅድ በመቃወም መሳሪያቸውን አናስረክብም ሲሉ ቆይተዋል።
ከሃምሌ ወር ጀምሮ በአማራ ክልል የተጀመረውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በተለያዩ ስፍራዎች በመንግስት ታጣቂ ሃይሎችና በታጠቁ ሃይሎች መካከል ግጭቶችን ሲካሄዱ መቆየታቸው ይታወሳል።
በተያዘው ሳምንት የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘውን የአስቸኳይ ጊዜ ዋጅ በመቃወም ለሶስት ቀን የሚቆይ የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ነዋሪዎች ለኢሳት ሲገልጹ ቆይተዋል።
ድርጊቱን ሲያስተባብሉ የቆዩ የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው በአድማው ተሳታፊ ነበሩ የተባሉ ወደ 30 አካባቢ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውን ከቀናት በፊት ይፋ አድርገዋል።

At least 1,500 arrests in Ethiopian state of emergency, claims news agency


State-run media says since declaring the six-month state of emergency, authorities have made vast numbers of arrests to quell protests

the

Ethiopian authorities have arrested more than 1,500 people since declaring a state of emergency less than two weeks ago, according to a statement published by state-controlled news agency Fana.

The command post, a body set up by authorities to oversee the state of emergency, said 1,120 people had been arrested in the towns of Shashemene and West Arsi – south of the capital, Addis Ababa – for “violence and property damage”.

The towns are in the region of the Oromo ethnic group, who along with the Amhara have waged a nearly year-long protest against a government largely made up of minority Tigrayans.

Another 302 people were arrested in the western town of Guji and 110 in the area of Kelem Wolega. According to the statement on Fana’s website, authorities seized hundreds of weapons.

Specially crafted for Windows 10, this app gives you full access to the Guardian’s award-winning content. With automatic caching, you can keep reading even when you’re offline.
Click here
About 50 people were arrested for “trying to deny service” by closing their businesses or calling for strikes in the Amhara region, and three teachers were detained for “abandoning school”.

The six-month state of emergency comes with a raft of stringent rules. Foreign diplomats are banned from travelling more than 25 miles outside Addis Ababa, and it is illegal to watch television stations set up by the diaspora. Posting links from these organisations’ websites on social media has been declared a “criminal activity”.

The state of emergency was imposed after a surge in violence following a stampede at an Oromo religious festival that killed more than 50 people on 2 October, which was blamed on police firing tear gas at anti-government protesters.

 https://www.theguardian.com

Ethiopians face five years in jail for posting on Facebook as ‘state of emergency’ rules set in


The flow of opposition reports about unrest has already started to dwindle

By Adam Withnall Africa Correspondent

 

(The Independent) — Ethiopians who post statuses on Facebook about the country’s growing political unrest could face up to five years in jail, as part of a series of measures under a “state of emergency” that grow more stringent by the day.

Ethiopians who post statuses on Facebook about the country’s growing political unrest could face up to five years in jail, as part of a series of measures under a “state of emergency” that grow more stringent by the day.

The government has imposed the longest blanket ban on mobile internet services in the capital Addis Ababa since protests began a year ago, and access to messaging platforms like WhatsApp has been heavily restricted.

The measures are designed to stifle people’s ability to organise protests, amid calls for greater political freedoms and recognition from the ethnic Oromo and Amharic groups.

Access to foreign-based media has also been restricted, including Deutsche Welle and Voice of America, which both have popular Amharic stations. Two TV stations run from the US for the Ethiopian diaspora, ESAT and the Oromia Media Network, have been banned.

facebook_300x214_270x193

And the new rules even seek to ban people from carrying out certain gestures “without permission”. They include crossing arms above the head to form an “X”, a political symbol that has become synonymous with the Oromo struggle and featured at the Rio Olympics and Paralympics.

UK rights charities are particularly concerns that under the emergency rules, which are expected to be in place for the next six months, foreign diplomats will have their movements heavily restricted.

Protesters chant slogans against the government during a march in Bishoftu, in the Oromia region of Ethiopia (AP)
The government says diplomats are not allowed to travel more than 40km (25 miles) from the capital, Addis Ababa, without permission, and say it is for their own safety.

But the rights group Reprieve told The Independent there are serious concerns this could limit the access Britons have to consular services. They raised the case of one UK citizen, father-of-three Andy Tsege, who is on Ethiopia’s death row and held at a jail some way outside the capital.

“Andy’s family in London, who cannot contact him, are sick with worry,” said Maya Foa, a director at Reprieve. “Amid this crisis, it’s shocking that the UK continues to rely on Ethiopia’s vague, broken promises of regular consular access and a lawyer for Andy. Boris Johnson must urgently call for Andy to be returned home to his partner and kids in Britain.”

Ethiopia is a key strategic ally for the US and European countries in the fight against Somalia’s Islamist insurgency, al-Shabaab, and Addis Ababa is the home of the African Union.

The global importance of the country’s stability has meant Western governments turning a blind eye to its authoritarian leadership. In June, the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front cut off nationwide access to social media – on the grounds of preventing exam result leaks.

The new ban on internet services has already made a noticeable impact on the flow of reports of unrest coming out of the country via on-the-ground activists.

Ethiopian state media reported that 1,000 protesters had been arrested in the central Oromia town of Sebeta since the state of emergency was declared on 8 October, and ahead of an investment conference in the town which began on Monday.

Festival goers flee during a deadly stampede in Bishoftu, on October 2, 2016 (AFP/Getty Images)
FBC said those detained were suspected of damaging property, but there was little in the way of opposition reports to give the other side of the story.

The emergency rules include a ban on using social media to contact “outside forces”, and Ethiopians risk jail if they communicate with any “anti-peace groups designated as terrorist”.

Finally, the rules stipulate a curfew of 6pm to 6am in which members of the public may not visit factories, farms and government institutions, which have come under attack in recent weeks.

The UN Secretary-General Ban Ki-moon has urged the Ethiopian government to ensure “the protection of fundamental human rights” during the state of emergency, and the president has announced some electoral reforms in order to try and reach out to protesters.

A Western diplomat told the AFP news agency those changes had not yet materialised, however. “This is a state of emergency and we expect repressive measures,” the diplomat said.

“But we also expect an opening of the political space for the opposition as stated by the president in front of the parliament. This is not what seems to be happening.

የአርበኞች ግንቦት7 መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል። ከመግለጫው የተወሰደ


14670781_1159797437461367_6771257405535668049_nከዚህ በኋላ የፍትህና የነፃነት ኃይሎች ዋና ተግባር ያላቸውን አቅም ሁሉ አስተባብረውና ነፃነት የራበውንና የጠማውን ሕዝባቸውን ከጎናቸው አሰልፈው፤ ጊዜውና ሁኔታው የሚፈቅደውን ተለዋዋጭና ተለማጭ የትግል ስልት እየተጠቀሙ ይህ አዋጅ በፍጹም ተግባራዊ እንዳይሆንና እንዳይሳካ ማድረግ ነው። ይህን የባርነት አዋጅ ለማስፈጸም በመሪነትና በዋና አስፈጻሚነት የሚንቀሳቀሱት ኃይሎች፤ ይህ የባርነት አዋጅ በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ እንዲተገበርና እንዲሳካ ለማድረግ የሚሞክሩ ወይንም ከዚህ ዘራፊ ሥርዓት ጋር በጥቅም ተሳስረው ከዚህ የባርነት አዋጅ ጋር የሚተባበሩ ማናቸውም ኃይሎች ሁሉ ከአሁን ጀምሮ የሕዝባዊ ትግሉ ቀንደኛ ዒላማዎች መሆናቸውን ግልጽ አድርጎ መንቀሳቀስ ይገባል። በዚህ ሕዝባዊ ትግል ላይ የሚሳተፉ የሕዝብ ወገኖችም ሆነ ይህንን ዘራፊ ሥርዓት የሚያግዙ ኃይሎች በደንብ እንዲረዱት የሚያስፈልገው ይህን አዋጅ አከሸፍነው ማለት የወያኔ ሥርዓት አከተመለት ማለት እንደሆነ ነው። ይህ አዋጅ ተሳካ ማለት ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ላልተወሰነ ጊዜ በባርነት መቀመቅ ውስጥ ሊኖር ተፈረደበት ማለት ነው። ለዚህ ነው አሁን የገባንበት ትግል የመጨረሻው የሞት ሽረት ትግል ነው የምንለው።”
“በዚህ የመጨረሻ የፍልሚያ ወቅት ጥቂቶቻችን ልናልፍ እንችላለን። ለነፃነታችን ስንል ሕይወታችንን ብንሰጥ ፈጣሪያችን በአምሳሉ ሲፈጥረን የሰጠንን የሰውነት ማንነት እውን ለማድረግ በምናደርገው ትግል ነውና የምናልፈው፤ የፈጣሪያችንን ፈቃድ ለማስፈጸም የገበርነው ሕይወታችን ነውና በደስታ የምንጠጣው ጽዋችን ነው። ይልቅስ ፈጣሪያችን ለምንግዜውም ይቅር የማይለን ከሌላው እንሰሳ ለይቶ የሰጠንን ይህን በነፃነት የታጀበ የሰው ልጅነት፤ እንደ እንሰሳ ለሚበላና ለሚጠጣ ቁሳዊ ጥቅም ሸጠን፤ ሰው መሆንን በእንሰሳዊ የባርነት ሕይወት ቀይረን እኛ ባርነትን ተቀብለን ከራሳችን አልፎ ባርነትን ለልጆቻችን ያስተላለፍን እንደሆነ ነው። የዛሬ ትውልድ ኢትዮጵያውያን የባርነትን ኑሮ ከኛ እንዳያልፍና ወደ ልጆቻችን እንዳይጋባ ማስቆም ታሪክ የጣለብንና በእርግጠኛነት የምንፈጽመው ተግባራችን እንደሆነ ከቶውንም አልጠራጠርም።”

በሃገር ቤት እየተቀጣጠለ ያለውን የኦሮሞ ሕዝብ ትግል እየመራ ያለው ማን ነው? ጀዋር ወይስ ዳዑድ? | ይህ የድምጽ ዘገባ ምላሽ አለው


አንደኛ ዓመቱን ሊደፍን ያለውን የኦሮሞ ሕዝብን ትግል በሃገር ቤት ወጣቶችን (ቄሮዎችን) በማደራጀት እየመራነው ያለነው እኛ ነን ሲሉ አቶ ዳዑድ ኢብሳ ለሰይፈነበልባል ራድዮ የሰጡትን ቃለምልልስ ዘ-ሐበሻ ጠቅሳ ዘግባ ነበር:: የአሜሪካ ድምጽ ራድዮ ጋዜጠኛዋ ጽዮን ግርማም ይህን ተከትላ ለኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ዳይሬክተርን አክቲቭስት ጀዋር መሐመድ “የኦሮሞን ሕዝብ እንቅስቃሴ እየመራው ያለው ማን ነው?” ስትል ጠይቃው ነበር:: በዚህ ቃለምልልስ የዳዑድ ኢብሳውን ኦነግ ሌላ አመራርም አካታለች:: ተከታዩ ዘገባ አሁን በሃገር ቤት እየተቀጣጠለ ያለውን የኦሮሞ ሕዝብ ትግል እየመራ ያለው ማን ነው? ለሚለው ምላሽ ይሰጣችኋል – ያድምጡት::

ከአማራ ክልል የሕዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫና አዲስ የትግል ጥሪ!


አዲስ የትግል ጥሪ !!

amhara-satenaw-2-300x2412ቀጣዩ እቅድ አንባገነኑ መንግስት በአማራና በኦሮሚያ እንዲሁም በጋንቤላና በኮንሶ በሰላም ባዶ እጁን ለተቃውሞ በወጣ ህዝብ ላይ በአልሞ ተኳሽ ህዝብን መጨፍጨፍ ሥራ ብሎ ይዞታል። ዛሬም ወጣትነት እስኪጠላ ድረስ በጅምላ ይጨፈጭፋል ፤በጅምላ ያፍናል፤ በጅምላ ያስራል፤ አስሮም አድራሻ አጥፍቶ ይገላል፤ ወላጆችም በሞቱት ልጆቻቸው አንጀታቸው ተቆርጧል። ልጆቻቸው የታሰሩባቸውም በህይወት ይኑሩ አይኑሩ ለማወቅ ተቸግረው ሌት ተቀን እያለቀሱ ይገኛሉ።

በቁስል ላይ እንጨት እንዲሉ ሰሞኑን በቢሾፍቱ የተፈጠረው ሁኔታ ሁላችንንም የማይታረቅ ቅራኔ ውስጥ አስገብቶናል። ጠንከር ያለ እርምጃ እንድንወስድም አስገድዶናል። በመሆኑም ባለን ውክልና በአማራ ክልል የወሎ፣ የጎንደርና የጎጃም የህዝብ ትግል አስተባባዎች የሆንነው አካላት አዲስ የትግል ጥሪዎችን አውጥተናል።
የኦሮሚያ ክልል የህዝብ ትግል አስተባባሪዎችም እንዲህ አይነት የትግል ስልቶችን በመጠቀም ከወገኖቻቸው ጋር በመተባበር በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ በማሰቃያ ቤቶች የሚገኙ ወንድሞቻቸውን እና 40 ሚሊዮን የሚገመተውን የኦሮሚያን ክልል ህዝብ ከሌላው ወንድሙ ጋር በማስተባበር ፤ህዝባችንን ነፃ ለማውጣት እንድንተባበር ይህን የትግል ጥሪ ስናቀርብ፤ሌሎችም በህወሀት አገዛዝ ታፍነው የሚገኙት የደቡብ ፣የጋምቤላ፣ የሶማሌ፣ የሀረሪ፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ የአፋር እና የትግራይ ክልል ሕዝብ ከሌላው ወገናቸው ጋር በትግሉ በመተባበር ሁላችንም ነፃ ልንወጣ ይገባል የሚል እምነት አለን።
እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚኖሩ ነጋዴዎችና አጠቃላይ የመዲናዋ ነዋሪዎች፤ የንፁሀን ወገኖቻቸውን ያልተቋረጠ ስቃይ ለማስቆም የሌሎች ወንድሞቻቸውን ጥሪ ሊተገብሩ ግድ ይላቸዋል።
በመሆኑም እኛ የአማራ ህዝብ ትግል አስተባባሪዎች፣ አፋኙን አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ህዝብን በማይጎዳ መልኩ ከዚህ በፊት ካካሄድነው የስራ ማቆም አድማ በበለጠ ጠንካራና ገዥውን ቡድን የሚያሽመደምድ ትግል የቀረጽን ሲሆን ህዝብም ይህን አንድ ሀሙስ የቀረው ቡድን አሽቀንጥሮ ለመጣል ይህን የትግል ስልት ያለፍርሀትና ያለመለያየት በጋራ ተግባራዊ ሊያደርገው ይገባል።

የትግል አይነቶች፦

የትግል ስልት1ኛ

-ለግል ድርጅቶች የ2008 ዓ/ም ግብር እስከ ተህሳስ 30 ታክስ አለመክፈል።
ከላይ እንደተመለከተው የወርሃዊ ቫት አለመክፈል ጥሪ ያስተላለፍን ሲሆን፤ አንድ ነጋዴ አገዛዙን ፈርቶ ታክስ እከፍላለው ካለ እስከ ታህስስ 30 ድርጅቱን የመዝጋት አማራጭ ቀርቦለታል። ምክንያቱም ህዝብ አንድ ከሆነ፤ አሸባሪው ቡድን ምንም ማድረግ አይችልምና።ይህን ጥሪ ጥሶ ለገዳዩ መንግስት ታክስ እየከፈለ ሌላውን የሚያሳጣውንና ለወንድሞቹ መግደያ ጥይት የሚገዛውን ድርጅትም ለመፋረድ ዝግጅት አድርገናል።
ምክንያቱም እኛ ወጣቶች ለነፃነት የህይወት መስዋትነት እየከፈልን ባለበት ሁኔታ አንዳንድ ነጋዴዎች ለንብረት ሣስተው ለገዳዩ መንግስት የጥይት መግዣ የሚሆን ግብር ከከፈሉ እኛም ለነሱ ዋጋቸውን እንከፍላለን። ከሌላው ወገኑ ጋር ያልተባበረ ነጋዴንና ከህዝብ ያልወገነ የታክስ መስሪያ ቤት ሰራተኛንም ከገዳዩ የህወሀት ቡድን በምንም አይነት ለይተን የማናያቸው መሆኑን ሊያውቁት ይገባል።

በተጨማሪም ነጋዴው ታክስ እንዳይከፍል የሂሳብ ባለሙያዎች ነጋዴውን በነፃ እንዲያማክሩት እናሣስባለን። ከምክሮቹም ውስጥ 1ኛ የወርሃዊ ቫት ሪፓርትና አመታዊ ታክስ ክፍያን ለወራት በማቋርጥ በወር በ2000 ብር ቅጣት ሳይከፍል እንደሚቆይ ማስገንዘብ፣ 2ኛ የአመታዊ የትርፍ ግብር የኪሳራ ሪፓርት ማቅረብ እና 3ኛ ተመላሽ ክፍያወችን መጠየቅ የሚሉት ይገኙበታል። ይህን በተመለከተ ለበጠ መረጃ የሂሳብ ባለሙያወችን ያማክሩ ።

እኛ የአማራ ክልል የህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪዎች ከሌሎች ወንድሞቻችን እና ከሕዝባችን ጋር በመሆን በነዚህ ወራት ይህን ዘረኛና ገዳይ ቡድን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ እየጣርን ባለበት ሁኔታ የገዳዩን ቡድን እድሜ ለማራዘም ይህን ግብር ያለመክፈል ጥሪ የሚጥሱ ነጋዴዎችን ስምና አድራሻ የታክስ መስሪያቤት ሰራተኞች እንዲተባበሩን ጠይቀናል፣ አሁንም እንጠይቃለን።
በተጓዳኝ ከህዝብ ያልወገኑ የታክስ መ/ቤትና የንግድና ትራንስፖርት መ/ቤት ሰራተኞችን ስም ፣ የሥራ ቦታና እድራሻቸውን ነጋዴው ሊያደርሰን ይገባል።

የትግል ስልት 2ኛ

በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ተባባሪ ድርጅቶች ፦
ሀ- የጥረት ድርጅቶች ፣ለ- የሸህ ማህመድ አል አሙዲ ድርጅቶች፣ ሐ- በክልላችን የሚተላለፉ የህወሀት ተሽከርካሪዎችና ንግድ ድርጅቶች ስራችውን እንዲያቆሙ ጥሪ እያስተላለፍን፤ ይህን ጥሪ ከተላለፉ እርምጃ እንደምንወስድባቸው እናሳውቃለን!!!
የህወሀት ተሽከርካሪዎችን የሚያሽከረክሩ ሾፌሮች ወንድሞቻችንም በክላችን እንዳትንቀሳቀሱ በውንድሞቻችን ደም እንጠይቃለን!!!

የትግል ስልት 3ኛ

ንግድ ባንክ፣ ዳሽን ባንክ፣ አንበሳ ባንክ፣ አባይ ባንክ፣ ወጋገን ባንክ፣ አማራ ብድር እና ቁጠባ ባንክ ተጠቃሚ የሆናችሁ የአማራ ክልል ነዋሪዎች በ15 ቀን ውስጥ ገንዘባችሁን እንድታወጡ እንጠይቃለን። ከ15 ቀን በሗላ ማንም የአማራ ክልል ህዝብ ገንዘብም በነዚህ ባንኮች እንዳይገባና እንዳይወጣ፤ እንዲሁም ከነዚህ ባንኮች የወሰደውን ብድር እንዳይከፍል፤ በነዚህ ባንኮች በእዳ የተያዙና ለጨረታ የቀረቡ የግለሰብ ቤቶችን እና ተሽከርካሪዎችንም ማንም እንዳይገዛ እናሣስባለን። ይህን ጥሪ ጥሶ በእዳ የተያዙ ንብረቶችን የሚገዛ፤ ነገ ጧት ሀብቱ የህዝብ እንደሚሆን ከወዲሁ እናሳውቃለን!!!
በትጓዳኝ ሌሎች ባንኮችም ቅርንጫፎቻቸውን እንዲያሰፉ ባልተቋቋሙባቸው የአማራ ክልል ከተሞች ቅርንጫፎችን እንዲከፍቱ እንጠይቃለን!
የንግድ ባንክ፣ የአንበሳ ባንክ፣ የዳሽን ባንክ፣ የአባይ ባንክ፣ የአበቁተ ባንክ ስራ አስኪያጆች፤ ገንዘቡን ወጭ የሚያደርገውን ህዝብ ያለምንም ችግር እንዲያስተናግዱ በሞቱት ወንድሞቻችን ስም እንጠይቃለን!ከዚህ በሗላ በነዚህ ባንኮች እየተጠቀመ ለወንድሙ መግደያ ጥይት የሚገዛውን ግን እንፉረደዋለን!!!
ህዝብ ከከፈለው ግብር በአመታዊ በጀት ተመልሶ ለልማት ሊደርሰው ይገባ ነበር። የእኛ የአማራ ህዝብ ግን፦ “ሰነፍ ነው፤ አይሰራም” ተብሎ ግብር ከፍሎ ከተመደበለት 4.5 ቢሊዮን ብር (ልብ በሉ ሚሊዮን እይደለም)የአማራ ክልል ልማት ባንክ በጀት ገንዘብ፤ ወደ ትግራይ ተወስዶ ሕዝብን ለመጨፍጨፍ ለህወሀት ወታደሮች ስልጠና እየተሰጠ ባለበት ወቅት እኛ በህወሀት በሚሽከረከሩ ባንኮች ገንዘባችንን ማስቀመጥ ፈጽሞ የለብንም!!!

የትግል ስልት 4ኛ

በመድን ኢንሹራንስ፣ ኒያላ ኢንሹራንስ ፣አንበሳ ኢንሹራንስ፣ አባይ ኢንሹራንስ ፣አፍሪካ ኢንሹራንስ ፣ተጠቃሚ የአማራ ህዝብ ከነዚህ ድርጅቶች ገንዘቡን ተመላሽ በማድረግ ሌሎች ኢንሹራንሶች እንዲገባ ጥሪ እናስተላልፉለን!!ሌሎች ኢንሹራንሶችም ለህብረተሰቡ የተመጣጠነ ዋጋ እንድታቀርቡ እንጠይቃለን።

የትግል ስልት 5ኛ

በውጭ የሚኖረው ማህበረሰብ በወገኑ ላይ እየደረሰ ያለውን አይን ያወጣ ስቃይ እያየ ወደ ሀገር ቤት በባንክ ገንዝብ መላክ፤ ሕዝብን በተጋድሎው በማገዝ ፋንታ ወገንን ለማስገደል መንግስትን እንደማገዝ ይቆጠራልና ቢችሉ 3 ወር ላልበለጠ ጊዜ ገንዘብ እንዳይልኩ እንጠይቃለን!!
ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ግዴታ መላክ ካለበዎት በጥቁር ገበያ እንዲልኩ አለዚያም ዘመድዎ ሀገር ውስጥ ካለ ዘመድ ወይም ወዳጅ ተበዳድረው እንዲቆዩ ያደርጉ ዘንድ እንጠይቃለን። ይህ ውጪ ላለው ወገናችን ለራሱ ህሊና የሚተው ጥሪ ሲሆን፤ ይህን ጥሪ ጥሶ በባንክ ገንዘብ የላከን ከአጋዚ ለይተን አናየውም።

የትግል ስልት 6ኛ

ማንኛውም ህዝብ ከዛሬ ጀምሮ የመሬት ሊዝ ማንኛውንም አይነት ክፍያ ለአማራ ክልል ለከተማ አስተዳደር መ/ቤቶች እንዳይከፍል!!

የትግል ስልት 7ኛ

ትራፊኮች፣ አደጋዎችን ከመቆጣጠር ውጭ ተሽከርካሪዎችን በገንዘብ እንዳትቀጡ!

የትግል ጥሪ 8ኛ

የመንግስት ተላላኪዎች በሙሉ ከዛሬ ጀምሮ ከህዝብ ጎን የማትቆሙ ከሆነ በናንተና በንብረቶቻችሁ ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን!!

የትግል ስልት 9ኛ

የመንግስት ባለስልጣን እና ካድሬ ንብረቶችን ባልተጣሩበት ሁኔታ ከዛሬ ጀምሮ በእዳ መያዣም ይሁን በግዥ ማንም እንዳይገዛ ጥሪ እናቀርባለን! እነዚህን ንብረቶች ገዝቶ የተገኘ ፤ነገ ጧት ወደ ህዝብ ንብረትነት መመለሳቸው እንደማይቀር ከወዲሁ እናሳውቃለን!!!

ከላይ የተዘረዘሩት ከዛሬ ጀምሮ የሚተገቡሩ የትግል ስልቶች ሲሆኑ ፤አሸባሪው ቡድን የህዝብን ጥያቄ የማይቀበል ከሆነ፤ አስተባባሪ ኮሚቴው በየደረጃው ከዚህ የተሻሉ ሌሎች እርምጃዎችን ለመውሰድ ዝግጁ መኾኑን እናሳውቃለን።
የአማራ ክልል ሕዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ

ኢንጂነር ይልቃል ታሰሩ


የሰማያዊ ፓርቲን እስከባለፈው ሳምንት ድረስ ሲመሩ የቆዩት ኢንጂነር ይልቃል መታሰራቸው ተሰማ:: ከርሳቸው ጋር አብረው ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች መታሰራቸው ተሰምቷል::

መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አውጥቻለሁ; እየታደስኩኝም ነው ባለ ማግስት ተቃዋሚዎችን እየጠራረገ ማሰሩን ተያይዞታል::

hiber-radio-interview-with-eng-yilkal-getnet.jpg

ከኢንጂነር ይልቃል በተጨማሪ አቶ ወረታው ዋሴ; ወይንሸት ሞላ እና ብሌን መስፍን እንዲሁም እያስጴድ ተስፋዬ በተለያዩ ቦታዎች በደህንነቶች ተይዘው መታሰራቸውን   አስታውቀዋል::

ሰማያዊ ፓርቲ ባለፈው ሳምንት ባደረገው ጉባኤ ኢንጂነር ይልቃልን ከሊቀመንበርነት ማንሳቱ ይታወሳል:

የመጨረሻው ሰዓት ነው። ወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኣውጇል።


3d6025f0በኢትዮጵያውያ ያለው የሕዝብ ተቃውሞ በመበርታቱ ኣላላውስ ያለው ኣጣብቂኝ ውስጥ የገባው ወያኔ ትላንትና ከሰዓት በኋላ ከሕወሓት ኣስቸኳይ ስብሰባ በኋላ ለሃይለማርያም በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት የኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ እንዲነገር መደረጉ ወያኔ የደረሰበትን ውድቀት በገሃድ ያሳይል፤ ባለፉት ሃያ ኣምስት ኣመታት ውስጥ ኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ ሲታወጅ ይህ የመጀመሪያው ሲሆን ሃገሪቱ ከባድ ኣደጋ ውስጥ መሆኗንና ወያኔ መምራት ኣለመቻሉን የሚመሰክር ኣዋጅ መሆኑ ታውቋል።ሕዝባዊው ትግሉ ካለበት ደረጃ ከፍ ብሎና ጠንክሮ በመሄድ ላይ በመሆኑ ለነጻነት ፈላጊ ሕዝቦች ታላቅ የድል ብስራት ነው።

ሕወሓት የማይወድቅባቸው የትግል ሥልቶች (ነፃነት ዘለቀ)


ፃነት ዘለቀ

Ethiopia-armyባሳለፍነው እሁድ በደብረ ዘይት የእሬቻ በዓል አከባበር ላይ በአጋዚ የወያኔ ቅልብ ጦር ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችንን ነፍስ እግዚአብሔር ይማርልን፤ ከዚህች ዘግናኝ ቀን በፊትም ሆነ በኋላ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በዚሁ የወያኔ ጦር ያለቁና ወደፊትም የሚያልቁ ወንድም እህቶቻችንንና ልጆቻችንን መንግሥተ ሰማይን ያውርስልን፡፡ ፈጣሪ የነሱን መስዋዕትነት እንደአቤል ንጹሕ ደም ቆጥሮልን የነፃነታችንን ቀን ያፋጥንልን፡፡ የቤተሰባቸውንም ሆነ የሁላችንን የተሰበረ ልብ ይጠግን፡፡ አሁንስ እጅግ በጣም እየተጎዳን ነው፡፡

ወያኔ በምን እንደማይወድቅ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለይ ቁልጭ ብሎ እየታየ ነው፡፡

  1. በምንም ዓይነት መንገድ ወያኔ በጩኸት አይወድቅም፡፡ እርግጥ ነው ሰሚ ከተገኘ ጩኸት ብሶትንና ግፍን ለመግለጽ ይጠቅማል፡፡ በኛ የእስካሁኑ ሁኔታ ግን ሰሚ የለንምና ጩኸታችን አልጠቀመንም፡፡ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተሰማራው ኃይል ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው በመሆኑ “ዐውቆ የተደበቀ ቢጠሩት አይሰማም” እንዲሉ ሆኖ ለማንም ብንጮኽ ሰሚ አናገኝምና ትርፉ ድካምና ጩኸትን በከንቱ ማባከን ነው፡፡ የኛ ደም ውኃ ይመስል በየቀኑ እንደጎርፍ እየፈሰሰ በዋና ዋና የሚዲያ አካላት በስፋትና በጥልቀት የማይዘገብበት ምክንያት ሌላ ሣይሆን ጥፋትና ውድመታችን የታዘዘው ዓለምን ከተቆጣጠረው ዋናው የአጋንንት ኃይል በመሆኑ ነው፡፡ እንጂ አንድ የስዊድን ወይም የእንግሊዝ ዜጋ የወያኔ ወንድሞች ማለትም አይሲሶች ቢገድሉት ኖሮ የሣምንታት የዜና መክፈቻቸው በሆነ ነበር፡፡ እነዚህ ጉደኞች ከአምስት መቶ ሕዝብ በላይ በጠራራ ፀሐይ የታጨደበትን አሳዛኝ ዕልቂት በመኪና ተገጭቶ የሞተ አንድ የአውሮፓ ውሻ ያህል እንኳን አልቆጠሩትም፡፡ ለይስሙላ ግን “In God we trust.” እያሉ በፈጣሪ ኅልውና ሲያላግጡ አያፍሩም፤ የሥራቸውን ይስጣቸው እንጂ ምን ይባላል፡፡ ለነገሩ ከሞላ ጎደል ሁሉም የዘሩትን እያጨዱ ነው፤ ወደፊትም ይህ የፈጣሪ ፍርድ በነሱም ላይ አይቀርም፡፡ ማንም የሥራውን ያገኛል፡፡
  2. በምንም መንገድ በሰላማዊ ሰልፍ ወያኔ አይወድቅም፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ጊዜ ማባከኛ ነው፡፡ 25 ዓመት ተሰልፈን ያመጣነው ለውጥ የለም፡፡ “ደግሞ ጀመራቸው!” ከማስባልና እንደክፉ ዐመል የተተከለን ጠባይ ከማሳየት ውጪ ምንም አልፈየደም፡፡ ሰልፍ የሚሠራበት ሀገር አለ፤ ለኛ ግን አይሠራም፡፡
  3. በምንም መንገድ ሕወሓት በድርድር አይወድቅም፡፡ ወያኔ ዘንድ ሰጥቶ መቀበል ብሎ ነገር የለም፡፡ የወያኔ ጠባይ ጨርሶ ማጣት ወይም ጠቅልሎ መውሰድ እንጂ የቁጥ ቁጥ ነገር አይዋጥላቸውም፡፡ አንድም የሕዝብ ጥያቄ በአወንታ መልሰው የማያውቁት ጥያቄን በአግባብ መመለስን እንደመሸነፍ ስለሚቆጥሩት ነው፡፡ ለምሣሌ ሁለትና ሁለት ሲደመር ስንት እንደሚሆን ወያኔዎችን ብትጠይቋቸው ሦስት ወይም አምስት ይሉ ይሆናል እንጂ እቅጩን “አራት ነው” አይሉም፡፡ ምክንያቱም በትክክል መመለስ ጠያቂን እንደሚያስደስት ስለሚያምኑና ያንንም ለነሱ እንደሽንፈት ስለሚቆጥሩት ነገረ ሥራቸው ሁሉ ጠማማ ነው፡፡ ይህ ጠባያቸው የሚያሳየን አእምሯቸው ያልሠለጠነና በዕድገቱ ከእንስሳትም በታች መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም ከወያኔ ጋር ተደራድሬ ሀገሬን ነፃ አወጣለሁ የሚል አካል ቢኖር ራሱም ያበደ ነው፡፡ ወይም ወያኔ ጊዜ ገዝቶ ከጭንቀቱ እስኪገላገልና አንዳች ዘዴ ፈልጎ እስኪያጠፋው በመሣሪያነት ሊያገለግል የወደደ ጊዜያዊ የሥልጣን ፍርፋሪ የሚፈልግ መሆን አለበት፡፡ እርግጥ ነው ወያኔ በጣም ሲጨነቅ ከነልደቱ አያሌውና ከነ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ዓይነቶቹ የሥልጣን ጥመኞች ጋር ሊደራደር ይችል ይሆናል፡፡ እነዚህ ወገኖች በሥልጣን አራራ የሚታሙና የሚወቀሱም በመሆናቸው ለወያኔ የተወሰነ እፎይታ ለመስጠት በመናጆነት ሊያገለግሉ ቢሞክሩ አይገርምም – ጊዜና ዕድል ከገጠማቸው ሊያውም፡፡
  4. በምንም መንገድ ወያኔ በምርጫ አይወድቅም፡፡ ይህ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ምርጫን በግልጽና በማንአለብኝነት በማጭበርበርና ኮረጆን በመገልበጥ የሚታወቁትን ወያኔዎችን በምርጫ አሸንፌ ሥልጣን እረከባለሁ ማለት ከጅብ መንጋጋ ሥጋ ለመቀማት እንደመሞከር ያለ ቂልነት ነው፡፡ በፍጹም አይታሰብም፡፡
  5. በምንም መንገድ በምዕራባውያን ተፅዕኖ አይወድቅም፡፡ ሞልቃቃ ልጃቸው ስለሆነ በጠራራ ፀሐይ ሚሊዮኖችን ቢጨፈጭፍና የዘር ማጥፋት ወንጀል ቢፈጽምም በሞራል ከማበረታታትና የገንዘብ ድጋፍ ከመለገስ በስተቀር ፊቱን የሚያዞርበት አንድም ምዕራባዊ ሀገር የለም፡፡ ምክንያቱም ከፍ ሲል ለመጥቀስ እንደተሞከረው የኢትዮጵያ ጥፋትና ውድመት የተቀነባበረው በነዚህ ልዝብ ሰይጣናት የምዕራቡ ዓለም የደኅንነት ተቋማትና በዐረቦችም ጭምር የወልና የተናጠል ድጋፍ ነውና፡፡
  6. በምንም መንገድ እዚያና እዚህ በሚደረግ ያልተቀናጀ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ወያኔ አይወድቅም፡፡ በዘርና በጎሣ እንዲሁም በሃይማኖት በተከፋፈለ ሕዝባዊ ዐመፅ ወይም የእምቢተኝነት ንቅናቄ ወያኔ ይወድቃል ማለት ዘበት ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ነገር ለወያኔ ሥራ ያበዛበት እንደሆነ እንጂ፣ የመቆያ ሥልቶችን እንዲያሰላስል ዕድል ይሰጠው እንደሆነ እንጂ፣ ትንሽ እንዲጨነቅ ያስገድደው እንደሆነ እንጂ ከአራት ኪሎ አያስወጣውም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የተነጣጠለ ትግል ለአደጋና ዕልቂት የሚጋብዝ እንጂ ውጤት የለውም፡፡
  7. በምንም መንገድ በጋዜጣዊ መግለጫና በፉከራ አይወድቅም፡፡ ወያኔዎች ምሥጥ ናቸው፡፡ ዕድሜ ለላኪዎቻቸው የትም ሆነህ ብትቃወማቸው ክንዳቸው ረጂም ነው፤ ባለህበት ይመጡልሃል፡፡ አንተን የመሰለ ሰው አስርገው ይልኩብሃል፡፡ እናም እንኳንስ በጋዜጣዊ መግለጫና በፖለቲካዊ ጫጫታ ይቅርና በተደራጀ ጦርም እነሱን ማሸነፍ አስቸጋሪ ነው፤ ጨርሶ አይቻልም እያልኩ ግን አይደለም፡፡ ገንዘባቸው፣ ስለላቸው፣በአባቶቻቸው የሚደረግላቸው የመረጃና የበጀት ድጋፍ፣ በጥቅም በዘርና በቋንቋ ሰውን መከፋፈላቸው፣ እኛን የሚመስለው የሰውነትና የቋንቋ እንዲሁም ሌላው ቅርጻቸው የኛን ትግል እጅግ ከባድና ውስብስብ ያደርገዋል፡፡ በዚያ ላይ ብዙ ተቃዋሚዎቻቸው ወያኔዎችን ይንቃሉ፡፡ እንደውነቱ ከሆነ በዋናነት ወያኔን የጠቀመው የነሱ ሸረኝነትና የኛ እነሱን መናቅ ነው፡፡ እነሱ እያደቡ ዕቅዳችንን ሁሉ ሲያከሽፉ እኛ ደግሞ ስንፎክርና በመግለጫ “ድባቅ ስንመታቸው” ይሄውና ሩብ ምዕተ ዓመት ዘለቅን – ሁነኛ የማስወገጃ ሥልቱን በቶሎ ካልነቃንበት ደግሞ ምዕተ ዓመቱን ይደፍናሉ፡፡ አሁን አሁን ግን ሕዝቡ ቀደመና መቆሚያ መቀመጫ እያሳጣቸው ይገኛል፡፡ የነሱ ተንኮል ማርከሻ ይህ ዓይነቱ መነሻው እንጂ መድረሻው በውል የማይታወቅ ሕዝባዊ ቁጣ ነው፡፡ ብልህ ሰው ታዲያ ያስፈልገናል፡፡ ይህን ሕዝባዊ እምቢተኝነት ወያኔዎች ብቻ ሣይሆኑ አለቆቻቸውም ይፈሩታል፡፡ ለምን ቢባል የሕዝብ ዐመፅ የት ጀምሮ የት እንደሚያልቅ አይታወቅም፡፡ የወያኔ ጌቶች ወያኔንና መሰል አሸባሪ ድርጅቶችን ጠፍጥፈው ሲሰሩ በርቀት መቆጣጠሪያ ሳይቀር እየተከታተሉ የሚያሸክሟቸውን ተልእኮ ተፈጻሚነት ያረጋግጣሉ፡፡ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ግን ከነሱ ዓላማና ፍላጎት ሊወጣ የሚችልበት አጋጣሚ ብዙ ስለሆነ ይፈሩታል፤ ፊት ለፊት ሊጋፈጡትም ብዙውን ጊዜ አይደፍሩም፡፡ ስለዚህ ይህን የትል ዓይነት ገፋ አድርጎ መቀጠል ተገቢ ነው፡፡
  8. በምንም መንገድ በስደተኞች ብዛትና ሀገርን ለወያኔ ለቅ በመሄድ ወያኔ አይወድቅም፡፡ ይህ ዓይነቱ ነገር ሳይዋጉ እጅን እንደመስጠት ነውና በሀገር ውስጥ ሆኖ መታገል አማራጭ የለውም፡፡
  9. በምንም መንገድ በማዕቀብና ዕቃና አገልግሎት ከሕወሓት ባለመግዛት ወያኔ አይወድቅም፡፡ ምክንያቱም በቂ የሀብት ክምችት አላቸው፤ ሁሉ በጃቸው ሁሉ በደጃቸው – ምን ሲጎድልባቸው፡፡ ሕወሓት ሀገሪቱን ላለፉት 25 ዓመታትና ከዚያም በላይ ለሚቆጠር ጊዜ በብቸኝነት ሲበዘብዝ በመክረሙ የገንዘብም ሆነ የማቴሪያል ችግር ሳይኖርበት ብዙ ዓመታትን መዋጋት የሚስችለው አቅም አጎልብቷል፡፡ ስለዚህ ከነሱ ዕቃ ባለመግዛት የምንጎዳቸው ነገር የለም፡፡
  10. በምንም መንገድ በፈቃዱ አይለቅም፡፡ ብሔራዊ ስሜት ቀርቶ የሰውነት ደረጃም የሌላቸው የለየላቸው ዕብዶችና ሰካራሞች በመሆናቸው የሀገሪቱና የሕዝቧ ችግር ገብቷቸው ሥልጣናቸውን ለሽግግርም ይሁን ለቋሚ የሕዝብ ተመራጭ መንግሥት ሊያስረክቡ አይችሉም፡፡ ትግራይንና የትግራይን ሕዝብ በሆነ ኮሮጆ ውስጥ ይዘህ “ይህን ኮሮጆ እሳት ውስጥ ከምጨምረውና ሥልጣናችሁን ከምትለቁ የትኛውን ትመርጣላችሁ?” ብለህ ብትጠይቃቸው ወያኔዎች ሥልጣናቸውን እንደሚያስቀድሙ ግልጽ ነው፡፡ ትግራይንና ተጋሩን ይቅርና በሚስትና በልጆቻቸው ሳይቀር ቁማር የሚጫወቱ የብዔል ዘቡል ደቀ መዛሙርት ናቸው፡፡ የሚገርም ተፈጥሮ እኮ ነው ያላቸው!

ስለዚህ መፍትሔው ምንድን ነው ቢባል መልሱ በበኩሌ እንዲህ ይመስለኛል፡፡

ሁሉም ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎች በአንድ ወቅት ተባብረው በመነሣት በየአካባቢያቸው የሚመጣውን የወያኔ ጦር ቢቻል መማረክና ማስተማር፣ ያ ባይቻል አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ በቁጥጥር ሥር ማዋልና ለፍርድ ማቅረብ፡፡ ዕቃና ንብረት እየዘረፉ የሚያሸሹባቸውን መንገዶች ሁሉ መዝጋት፤ የጎበዝ አለቃ እየመረጡ ትግሉን በአንድ ጊዜ በሁሉም ሥፍራ ማጧጧፍ፡፡ የወያኔ ወታደራዊ ክንድ ከተመታ፣ በተለይም አጋዚ የሚባለው የሰይጣን መንጋ ከተበተነ ሕወሓት ምንም አቅም አይኖረውምና በፍጥነት ይፍረከረካል፡፡ ያኔ ከያካባቢው የሕዝብ ተወካዮች ተመርጠው ትልቅ ሀገራዊ ስብሰባ በማካሄድ ከታዋቂ ጤናማ ፖለቲከኞችና ታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም የሕዝብ እምነት ከሚጣልባቸው ተቃዋሚዎች የሚውጣጡ የአደራ መንግሥት ማቋቋም፡፡ ያ የዐደራ መንግሥት ለሁለት ዓመታት ያህል ሀገሪቱን ካረጋጋ በኋላ በእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አዲስና ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል የሚያለግል ዴሞክራሲያዊ መንግሥት መመሥረት፡፡ ስንታገል ደግሞ በአንድነት እንጂ ዘርና ጎሣ፣ ሃይማኖትና ክልል ለይተን መሆን የለበትም፡፡ እንደዚያ ካደረግን የወያኔን ፈለግ እንደመከተል ያለ ከንቱነት ነው፡፡ አሮጌው ወይን በአዲስ አቅማዳ ከተገለበጠ ጥፋትን በጥፋት መተካት ነውና ካለፈ ጠመዝማዛ ሕይወታችን መማር አለብን፡፡ ስለዚህ ትግሬን ከዐማራ፣ ኦሮሞን ከሶማሌ፣ ከምባታን ከአፋር … አንዱ ከሌላው ሳይለያይ የአንዲት ሉዓላዊት ሀገር ሕዝብ ባንድ ልብና ባንድ መንፈስ መታገል ይኖርበታል፡፡ ወያኔዎች በተለይ ትግሬን ከሌላው ለመለየትና በሌሎች እንዲጎዳ በማድረግ ከነሱ ጋር ለመለጠፍ የሚያካሂዱትን የቀቢፀ ተስፋ ሸርና ተንኮል ነቅተን መጠበቅ አለብን፡፡ የወያኔን ሤራ በንቃት መከታተልና የእሳት ቃጠሏቸውን ሁሉ ሳይቀር እየተከታተልን ማጋለጥ አለብን፤ ሆን ብለው የሚጭሯቸውን ግጭቶች እየተከታተልን እውነቱን በወቅቱና አደጋ ሳያስከትሉ ይፋ ማድረግ አለብን፡፡ ሟች ይዞ ይሞታልና እነሱ ሥልጣናቸውንና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የማያደርጉት ነገር አይኖርም፡፡ እኛን ለመለያየትም የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡ መለያየትን ደግሞ እስኪያንገሸግሸን አየነው፤ ክፉኛ ጎዳን እንጂ አልጠቀመንም፡፡ መኖር ከፈልግን እንግዲህ ማድረግ ያለብን እንደዚህ ነው፡፡ ሁሌ መሞኘት የለብንም፡፡ በመሠረቱ ብልጥ ከአንዴ በላይ መብለጥ አልነበረበትም፡፡ እኛ ግን የሆንነውን ሳናውቀው ዕድሜ ልካችንን በነዚህ ሰይጣኖች ስንታለልና ስንበለጥ ኖርን፡፡

እንጂ እንዳሁኑ አካሄዳችን ከሆነ ሶማሊያና ሦርያ በስንት ጣማቸው የሚያስብል አስቀያሚ ሁኔታ እንደሚፈጠር በጣም ግልጽ ነው፤ የሚደርስልን ደግሞ እንደሌለ መረዳት ይገባል፡፡ ወያኔዎች አያያዛቸው “የምፅዓት ቀን ለምን ዘገዬ?” እያሉ ለአባታቸው ለዲያቢሎስ ከፍተኛ ተማፅኖ በማቅረብ ላይ የሚገኙ ይመስሉኛል፡፡ የታወከን ሀገር በብልሃትና በዘዴ እንደማረጋጋት ቦሃ ላይ ቆረቆር እንዲሉ በሰላም በዓልን በሚያከብር በሚሊኖች የሚቆጠር ሕዝብ ላይ ከመሬትና ከሰማይ ጥይት ማዝነብ በየትኛውም ሥሌት ትርጉም የለውም፡፡ እነዚህ ድፍን ቅሎች የጥጋብ ሞራ ሁለመናቸውን ስለጋረደው የሚያደርጉት ነገር ምን ሊያስከትል እንደሚችል ማሰብ አልቻሉም፤ ተፈጥሯቸው ሁሌም በተቃርኖ የተሞላ ነው – “እንብላ” ሲሏቸው “እንተኛ” ዓይነት፡፡ ገና ለገና የላኳቸው የጥፋት ኃይሎች በሁሉም ረገድ አይዟችሁ ስላሏቸው ብቻ ምድራችን ዐይታውም ሆነ ሰምታው የማታውቀውን የክፋት ሥራ በኢትዮጵያውያን ላይ ይፈጽማሉ፡፡ በመጨረሻው የሚያስደስተው ነገር ግና የሠሯትን ሁሉ አንድ ባንድና በዕጥፍ ድርብ ያወራርዷታል፤ ያም ቀን ደርሷል፡፡

እንደማሣረጊያ – ያገሬ ባላገር ምን አለ?

የማን ቤት ፈርሶ የማን ሊበጅ፤
ያወሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ፡፡

እባክሽ እናቴ ውለጅ መንታ መንታ፤
ቀኝ እጄ ሲመክት ግራ’ጄ ተመታ፡፡

እዚያ ማዶ ሆኖ አንድ ሰው ተጣራ፤
እዚህ ማዶ ሆኖ አንድ ሰው ወይ አለው፤
ጎበዝ ተጠራጠር ይህ ነገር ለኛ ነው፡፡

ኃይለማርያም ደሳለኝ ሲዋሹ ምንም ጥይት አልተተኮሰም ይላሉ – ፎቶው ግን ይናገራል


 

ተላላኪው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ትናንት ከ500 በላይ ወገኖቻንን ከሕወሓት መንግስት ጋር በመተባበር ካስፈጁ በኋላ “አንድም ጥይት ሳይሰማ” በሚል እንጀት በሚያቃጥል መግለጫ በመስጠት ሕዝብ ላይ ተጨማሪ ሃዘን ጨምረውበታል:: እንግዲህ እርሳቸው ወደ ሕዝብ አልተኮስንም የሞቱት ገደል ገብተው ነው ብለውናል በአደባባይ:: ፎቶው ግን የሚያሳየው በተቃራኒው ነው:: ይህ ማስረጃ ይመዝገብ:: ይናገራል ፎቶው

hailemariam-593x1024

ሕዝባዊው አመጽ በአምቦ፣ በጊንጪ፣ በሸኖ፣ በመቂ፣ በባሌ ሮቤ፣ በደንቢ ዶሎ፣ በቄለም ወለጋ፣ በም ዕራብ ሸዋና በሌሎችም ከተሞች ተቀጣጠለ


cars

meki-768x432cars

ትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ትናንት በቢሾፍቱ የ እሬቻን በዓል ለማክበር በወጡ ንጹሃን ላይ በሂሊኮፕተር እና በመትረየስ የታጀበ የዘር ማጥፋት ከፈጸመ በኋላ በተለያዩ ከተሞች ሕዝባዊ አመጹ እንደገና ተቀጣጠለ::

መረጃዎች እንደጠቆሙት በአምቦ፣ በጊንጪ፣ በሸኖ፣ በመቂ፣ በባሌ ሮቤ፣ በደንቢ ዶሎ፣ በቄለም ወለጋ፣ በም ዕራብ ሸዋና በሌሎችም ከተሞች ተቃውሞው ተቀጣጥሏል::

በተለያዩ ከተሞች በተነሱት በነዚሁ ሕዝባዊ አመጾች የመንግስት መኪኖች ሲነዱ ታይተዋል::
በአምቦ፣ በጊንጪ፣ በሸኖ፣ በመቂ፣ በባሌ ሮቤ፣ በደንቢ ዶሎ፣ በቄለም ወለጋ፣ በም ዕራብ ሸዋ ሕዝብ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን እያሰማ ሲሆን በመንግስት ንብረቶች ላይ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይም ይገኛል::

በተለይ የሕወሃት ንብረት የሆነው ሰላም ባስ በሃረርጌ ጥቃት እንደተፈጸመበት የደረሰን መረጃ ያመልከታል::

በቄለ ወለጋ ጂማ ሆሮ ወረዳ ኑኑ ከተማ ከፍተኛ የሕዝብ ተቃውሞ ተቅስቅሶ ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ እንደሆኑ ሲታወቅ በባሌ ሮቤ ደግሞ ሁሉ ነገር መዘጋጋቱ ተሰምቷል::

በደምቢ ቦሎ ኢንተርኔት በጠቅላላ መቆረጡ ሲታወቅ ተቃውሞውም እንደበረታ ምንጮች ገልጸዋል:: በአምቦም እንዲሁ ተመሳሳይ ተቃውሞዎች ዳግም እንደተቀሰቀሰ የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ::

እስካሁን ባለዉ መረጃ,,,,, ዛሬ በዓል ላይ በኢሬቻ የተገደሉ ወገኖቻችን ቁጥር 115 ደረሰ:: የቆሰሉ 75 ናቸዉ –


በኢሬቻ የተገደሉ ወገኖቻችን ቁጥር 115 ደረሰ:: የቆሰሉ 75 ናቸዉ:: እስካሁን ባለዉ መረጃ:: በተያያዘ ዜናም ከሞትት መካከሎም ባህሉን ከኦሮሞ ወንድሞቻቸዉ ጋር ለማክበር የተገኙ የአማራ ልጆች እንዳሉ ታዉቋል:: በዚህ ሰአት ኔትወርክ የተዘጋ ሲሆን ተቃዉሟዉ ወደሌሎች አካባቢዎችና አዲስ አበባ ሻሸመኔም ይዛመታል ተብሎ ተሰግቷል:: ከወደመከላከያ ፌደራል ፖሊስ አካባቢም አለመግባባት ተፈጥሯል:: ደብረዘይት አየር ሀይል ዉስጥ የተኩስ ድምፅ ተሰምቷል:: we will see what to happen next! ህሊና ዘቀበሮ #OromoProtest –
j8

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ሀይለማሪያም ደሳለኝ፣ “አንዳንድ ሰዉ እንደራሱ ነዉ ሰዉን የሚያስበዉ እሱ በራሱ ወስኖ ስለማይሰራ ፈይሳ እንደዛ ያስባል ብሎ ነው ሚገምተዉ፤ ራሴ ነኝ ራሴን የምመራው፤ ሰው አይደለም ሚመራኝ ሰዉ ጽፎ የሰጠኝን እኔ አላነብም።”

ስትሮክ


13872636_10208572113394776_4322058600249668540_nይህንን መረጃ ሳነብ ያገኘሁት ነው። ለሁላችንም እንዲጠቅም ወደአማርኛ መልሼዋለሁ። ስትሮክ የዕለት ከዕለት ችግራችን እየሆነና የሁላችንንም ጓዳ እያንኳኳ በመሆኑ መረጃው ይጠቅመናል ብዬ አስባለሁ። እባካችሁ ሼር በማድረግ እውቀት አሸጋግሩ። ምናልባት በዚህ መረጃ የአንድ ሰው ህይወት ታተርፉ ይሆናል።

እኔ በበኩሌ ከ8 አመት በፊት ይህ መረጃ ቢኖረኝ ኖሮ ምናልባት ወንድሜን ከሞት የማትረፍ እድል ይኖረኝ ነበር። እሁድ ቀን ጠዋት ነው። ወደጓደኛዬ ኒካ ስነስርአት ለመሄድ ስነሳ ወንድሜ ቀድሞኝ ከቤት ወጥቶ ስለነበር ከቤታችን ደጃፍ የሚገኝ አስፋልት መንገድ ዳር ላይ ተቀምጦ አይቼው ነበር። ከአይኑ እስክጠፋ ቁጭ ባለበት ቦታ ሆኖ ያየኝ እንደነበር ያወቅኩት ርቄ ሄጄ ዘወር ስል ወደኔ አቅጣጫ ያይ እንደነበር በመታዘቤ ነው።

ከሁለት ሰአታት በኋላ ፑል በመጫወት ላይ እንዳለ ተዝለፍልፎ ወደቀ ተብሎ ተደወለልኝ። ስደርስ ቤተዛታ ሆስፒታል ገብቶ ስትሬቸር ላይ ተኝቶ አገኘሁት። ሃኪሞች ከሻይ እስኪመለሱ እርዳታ አላገኘም። ቀስ በቀስ ራሱን ሙሉ በሙሉ ሳተ። ችግሩ ምን እንደሆነ አላወቅንም የነገረንም ሃኪም የለም። በመጨረሻ ቤተዛታ ከአቅሜ በላይ ነው አልችልም አለ ……ጥቁር አንበሳ በበኩሉ አልጋ የለኝም ሲል…እኛም ለጭንቅላት ምርመራ የታዘዘልንን ኤምአርአይ ፍለጋ ስንንከራተት ሰአቱ ገፋ። መጨረሻ ላይ ሀያት ሆስፒታል አልጋ ተገኝቶ የፅኑ ህሙማን ጥብቅ ክትትል ክፍል (ICU) ገባ። በዚያው ሁኔታ ሳለ በሶስተኛው ቀን ህይወቱ አለፈ።ገና በ22 አመቱ። ለቤታችን ታላቅ ሃዘን ሆነ። ዛሬ ድረስ ሁኔታውን ሳስበው እንባዬን ማቆም አልችልም። እጅግ የምወደውን ወንድሜን የነጠቀኝ ስትሮክ ነው።

ከዚያ ጊዜ በኋላ የቅርብ ዘመዶቼን ጨምሮ የማውቃቸው ብዙ ሰዎች በስትሮክ ተጠቅተው አይቻለሁ። ብዙዎቹ ሞተዋል።ብዙዎቹ ፓራላይዝ ሆነዋል። በዚህ ሁለት ወር ብቻ የማውቃቸው ሶስት ሰዎች በስትሮክ ሞተዋል።

በስእሉ ላይ እንደምትመለከቱት ስትሮክ ወደአንጎል የሚሄደው ደምስር በረጋ ደም በሚዘጋበት ጊዜ የደም ዝውውር ሲቋረጥ የሚከሰት የደም ወደአንጎል መፍሰስ የሚያስከትለው ከባድ የጤና አደጋ ነው። ከባድ የደም ግፊት፣ የልብና ኩላሊት በሽታ ለስትሮክ መከሰት ዋና ምክንያቶች መሆናቸውን ሃኪሞች ይናገራሉ።

ብዙዎቻችን ስለማናስተውለው እንጂ የምንሰማው የዘመድ ወዳጆቻችን ድንገተኛ ሞትና ራስ መሳት ከስትሮክ ጋር ቁርኝት አለው። ይህ አደጋ ድንገት ባልታሰበ ሰአት ይከሰታል። ተኝተን፣ እየሰራን፣ እየበላን፣ እየተጫወትን፣ መንገድ ላይ ሆነን ሊከሰትብን ይችላል።

በስትሮክ የተመታ ሰው ለብዙ ጉዳቶች ሊዳረግ ይችላል። አንዳንዶችን በሙሉ ወይም በከፊል ፓራላይዝ ያደርጋል። አንዳንዶቹን የአእምሮ ማስታወስ ችሎታቸውን በሙሉ ወይም በከፊል ይነጥቃቸውና ሚስትና ልጆቻቸውን ጭምር እንዲረሱ ያደርጋቸዋል። የከፋ ጊዜ ልክ ኮምፒውተር ፎርማት እንደሚደረገው ሁሉ ስትሮክ ያጠቃቸውን ሰዎችም አዕምሯቸው ምንም ሳያስቀር ሙሉ በሙሉ የመርሳት ችግር ይጋርጥባቸዋል። አንዳንዶቹ ላይ ደሞ ራስን ስቶ ሽንትና ሰገራ ለመቆጣጠር እስካለመቻል ምግብ እስካለመቀበልና በመጨረሻም እስከሞት ያደርሳቸዋል።

የስትሮክ የከፋው ጠባይ የያዘውን ሰው አንዳንዴ ከሞቱት በላይ ከቆሙት በታች አድርጎ ማስቀረቱ ነው። እናት ለታመመ ልጇ ሞትን እስክትመኝ የታመመ ሰው በጠያቂ “አሁንስ በገላገለው ” እስከሚባል ድረስ ተስፋ ያስቆርጣል።

የጭንቅላት ቀዶ ሃኪሞች አንዳንዴ ከተሳካላቸው በአንጎል ውስጥ የፈሰሰ ደምን በመጥረግ ህይወት ያተርፋሉ ወይም ጉዳት ይቀንሳሉ። በኛ አገር ደረጃ በከባድ ስትሮክ ተመትቶ ሙሉ በሙሉ የመዳን ብቻ ሳይሆን ከሞት የመትረፍ እድል ራሱ አናሳ ነው። እግዚአብሄር ተጨማሪ የመኖር እድል የሰጠው ሰው ከሳምንታት ወይም ወራት ራስን መሳት በኋላ ሙሉ በሙሉ ተርፎ በተአምር ከሞት ወደህይወት ይመለሳል። የአንዳንዱን ህይወት ደግሞ እስከእድሜ መጨረሻው ድረስ አበላሽቶ ያስቀረዋል። በአጠቃላይ ስትሮክ መቼና እንዴት እንደሚከሰት ስለማይታወቅ ሰይጣን በሽታ በሉት። ሹክክ ብሎ መጥቶ ውድ ህይወታችንን ይነጥቀናል።ወይም ከነበርንበት ሙሉነት ወደከባድ ጎዶሎነት ይቀይረናል።

ስትሮክን በተመለከተ ያለው መልካም ዜና አንድ ብቻ ነው። ምልክቱን አውቀን ከቀደምነው የሞት በትሩን የማስጣል እድል አለን ። በጣም ቀላል በሆኑ ዘዴዎች አንድ ሰው በስትሮክ ስለመመታቱ ማረጋገጥና በፍጥነት ወደሀኪም ወስደን ህይወቱን ማትረፍ እንችላለን። በርግጥ እግዜር ይጠብቅ ነው እንጂ በኛ ሃገር ሃኪሞችና ሆስፒታል ሁኔታ ብዙ ተስፋ ማድረግ አይቻል ይሆናል። ( በወንድሜ ሞት ያረጋገጥኩት ይህንኑ ነው)። ነገር ግን ባለሙያዎች እንደሚያረጋግጡት የስትሮክ ምልክት የታየበት ሰው በ3ሰአታት ጊዜ ውስጥ ሃኪም ጋር ከደረሰ ሙሉ በሙሉ ለመዳን እድል አለው። ዋናው ጥያቄ አንድ ሰው በስትሮክ ሲመታ የሚያሳያቸው ምልክቶች ምንድናቸው? እንዴትስ ማወቅ ይቻላል? የሚለው ነው።

አንዳንድ ጊዜ ምልክቶቹን ለመለየት ከባድ ቢሆንም STROKE አንድን ሰው እንዳጠቃው ለማወቅ የምንረዳባቸውን ቀላል ዘዴዎች አሉ። ቀዳሚው ዘዴ የ STROKE ን የመጀመሪያዎቹን ሶስት ፊደላት በቃል ይዞ በአዕምሮ መመዝገብ ነው። STR

S= smile. በትሮክ የተመታ ሰው ፈገግ ማለት ያዳግተዋል። ፊቱ ስሜት አልባ ይሆናል። አንድ ጊዜ ፈገግ እንዲል መጠየቅና ውጤቱን ማየት

T =talk ስትሮክ አንደበት ስለሚይዝ የሚወጡ ቃላት እንዲንተባተቡና ትርጉመቢስ እንዲሆኑ ያደርጋል። ቀላል አረፍተነገርን ሳያቆራርጥ እንዲናገር መጠየቅ (ምሳሌ ቴሌቪዥኑን ስንት ትሸጠዋለህ? እንዲል )
ውጤቱንም ማጤን

R=raise hands ስትሮክ እጅና እግር እንዳይታዘዝ ያደርጋል። ሁለት እጆቹን ወደላይ እንዲያነሳ መጠየቅና ውጤቱን ማየት

ከነዚህ አንዱን በትክክል መወጣት ከተሳነው የስትሮክ ምልክት ነውና ሃኪም ጋር በፍጥነት መውሰድ ጠቃሚ ይሆናል። በተጨማሪም ምላሱን ቀጥ አድርጎ እንዲያወጣ መጠየቅ ማውጣት ከተሳነው ወይም አጥፎና አጣሞ ካወጣው በስትሮክ የመመታት ምልክት ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል ።

በቃ ይኸው ነው። ለሁሉም ሼር አድርገን ህይወት እናድን

አባሎቻችንና ሌሎች ዜጎች ከሕግ ውጭ እየታሰሩ ነው ሲል ሰማያዊ ፓርቲ ከሰሰ


12439199_1011550062219585_4312483131257534071_nበመላው ሀገሪቱ የሰማያዊ ፓርቲ አባሎችና ሌሎችም ዜጎች ከሕግ ውጭ በሆነ አያያዝ በገፍ እየታሰሩ መሆናቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ተናገሩ።

በተመሳሳይ ሁኔታ ከ20 የማያንሱ ዜጎች ከሕግ ውጭ በምዕራብ ኦሮምያ በጅማ ገነት ወረዳ መታሰራቸውን አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ ወኪል ገለጹ።

ከመንግሥት በጉዳዩ ላይ ለጊዜው ማብራርያ ለማግኘት አልተቻለም።

በኦሮምያና በአማራ ክልሎች የተቃውሞ ሰልፎች መካየድ ከጀመሩ በኃላ በአጠቃላይ በሀገሪቱ ውስጥ በዜጎች ላይ እየተካሄዱ ነው ያሉት የአፈና እርምጃዎች እየተባባሰ መሆኑን በመግለጽ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ ይልቃል ጌትነት መንግሥትን ከሰዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድም