ከቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዓለም አቀፍ ህብረት የተሰጠ መግለጫ – “አገር ህዝብ እንጂ መንግስት አይደለም”


ethiopian-airforce
የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት የተጫነበትን የጭቆና ቀንበር ሲታገልና እራሱን ነፃ እያወጣ የኖረ ህዝብ ነው ። በፊውዳሉ የዘውድ ስርዓትም ሆነ በማርክሲሳዊው ወታደራዊ አገዛዝ ለዴሞክራሲና ለህግ የበላይነት በብዙ ታግሏል ። የሚገጥሙትን የአስተዳደር በደሎች ጐዳና ላይ በመውጣት ብሶቱን ሲያሰማ የኖረ ቢሆንም እንደዚህ ዘመን ግን የመከላከያ ሰራዊቱ በአልታጠቀ ሰላማዊ ህዝብ ላይ አልሞ ሲተኩስና የጅምላ ፍጅት ሲፈፅም ታይቶ አይታወቅም ።
በመሰረቱ የአገር መከላከያ ሰራዊት ከህዝቡ አብራክ ውስጥ የተገኘ እንደ መሆኑ መጠን የህዝቡ ብሶትና በደል የእራሱም በደል ሊሆን ይገባዋል ። የተመሰረተበት ዋና ዓላማም የአገርን ዳር ድንበር ማስከበርና የህዝብን ሰላምና ደህንነት መጠበቅ ነው ። ይሁን እንጂ አሁን በስልጣን ላይ ያለው የህውሃት/ኢህአዴግ ስርዓት ህዝቡን በዘር በመከፋፈል አገራችንን ወደ አደገኛ ብጥብጥና ፍጅት እየወሰደ ሲሆን ሰራዊቱም ብሶቱን ለማሰማት ወደ ጐዳና በወጣ ያልታጠቀ ሰላማዊ ህዝብና ገና አድገው ያልጨረሱ ወጣት ተማሪዎች ላይ ዓልሞ በመተኰስ አሰቃቂ ፍጅት እየፈፀመ ነው ።
የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዓለም ዓቀፍ ህብረት የህውሃት/ኢህአዴግ ስርዓት ከህዝብ ፈቃድ ውጪ ከሱዳን ጋር የሚያደርገውን የድንበር መካለል ፣ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ በህዝባችን ላይ እየፈፀሙ ያሉትን የጐዳና ላይ አሰቃቂ የጅምላ ፍጅት አጥብቆ ያወግዛል ።
በመሆኑም የመከላከያ ሰራዊቱም ሆነ የፌደራል ፖሊስ መንግስት አላፊ ፣ አገርና ህዝብ ግን ሁልጊዜም ቋሚ መሆናቸውን በማስታወስ በገዛ ወገናቸው ላይ የሚያደርሱትን የጅምላ ፍጅት በማቆም ከህዝቡ የነፃነት ትግል ጐን በመሰለፍ ህዝባቸውን ከማንኛውም ጥቃትና አደጋ እንዲታደጉ ጥሪ ያቀርባል ።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !

ከፍተኛ የወያኔ ባለስልጣናት በቋራ ህዝብ ውርደት ተከናንበው ተመለሱ


tplf-in-gondar

አባይ ፀሐዬ፣ ደመቀ መኮንን፣ ገዱ አንዳርጋቸውና ሌሎች በዛሬው ዕለት ወደ ቋራ አምርተው ህዝቡን ለመሰብሰብ ሲሞክሩ ህዝቡ በአንድነት አምፆ ከእነሱ ጋር ፈፅሞ መነጋገር እንደማይፈልግ ገልፆ የውርደትና ሀፍረት ጉንጉን አበባ አንገት አንገታቸው ላይ አስሮ መልሷቸዋል፡፡tplf-in-gondar
የጀግናው አፄ ቴዎድሮስ አጥንት ፍላጭ የሆነው ጀግናው የቋራ ህዝብ አሳፍሮ የመለሳቸው እነ አባይ ፀሐዬ በጎንደር ከተማ ሲኒማ አዳራሽ የፀጥታ ኃይሎችን፣ የዞኑን አመራሮች፣ ወሬ ለማዳመጥና እግር ጥሎት የገባውን ህዝብ ለማወያየት ሞክረው ነበር፡፡ ባለስልጣናቱ ፀረ ሰላም ኃይሎችና አሸባሪዎች ያሏቸውን ጠብመንጃ ያነሱ የነፃነት ድርጅቶች ህዝቡ እንዳይደግፍ ሲያሳስቡ ህዝቡ “ቢመጣ ቢመጣ ከእናንተ የባሰ አይመጣ…” ሲል ምላሽ ሰጥቷቸዋል፡፡ በጎንደር ከተማ የሚኖሩ የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በስማቸው እየነገደ ከሌሎች ቋንቋዎች ተናጋሪዎች ጋር እንዳቆራረጣቸው በመግለፅ ህወሓትን ከሰውታል፡፡ ከዚህ በኋላ የህወሓት ደጋፊም እንዳልሆኑ የአቋም ለውጣቸውን በይፋ አስታውቀዋል፡፡
የጎንደር ከተማ የፀጥታ ኃይሎች ደግሞ በበኩላቸው ከእንግዲህ ወዲህ ወደ ወጡበት ህዝብ አፈሙዝ አዙረው ምላጭ መስበር እንደማይሹና አገዛዙ ወደ ወገናቸው ተኩሱ የሚላቸው ከሆነ አስቀድሞ የጦር መሳሪያቸውን እንዲረከባቸው ጠይቀዋል፡፡

የወልቃይት ወደ ትግራይ መካለል የተቃወሙ ወጣቶች ላይ የደረሠውን ግፍ አንድ ወታደር እንደሚከተለው ተናግሮ ነበር


gonder-before-and-after-1991_121623

በመጀመሪያ ወጣቶቹ ከወልቃይት ተጭነው ወደ ትግራይ ተወሠዱ። ከዚያም እጅና እግራቸው ታጥፎ ተሠበረ። በዚህ ሁኔታ ለሀምሣ ቀናት እራቁታቸውን አንድ ቤት ውሥጥ ተዘግቶባቸው በቀን አንድ ዳቦ ከብዙ ዱላ ጋር እየተሠጣቸው እንዲቆዩ ተደረገ።
ሀምሣ ቀን ሙሉ ከዚያ ቤት አልወጡም። በሀምሣኛው ቀን አንድ የጭነት መኪና መጣና ወጣቶቹ ተዘግተውበት የነበረው ቤት ተከፈተ። በወቅቱ በአካባቢው የነበረውን ሽታ በቃላት ለመግለጽ አዳጋች ነው። ወጣቶቹ በጣም ከመክሣታቸው የተነሣ ወታደሮቹ በአንድ እጃቸው ጸጉራቸውን አንጠልጥለው ወደ መኪናው ይወረውሯቸው ነበር። አንደኛውን ወጣት ጸጉሩን ይዞ ሢወረውረው ጸጉሩ ተነቅሎ ወደቀ። ያንን ሥመለከት ሠው ሆኘ መፈጠሬር ጠላሁት።
ወጣቶቹን ጭኖ የሄደው መኪና ማታ አካባቢ ባዶውን ተመለሠ። ወጣቶቹን እንደገደሏቸው ባውቅም ከዚያ ሁሉ ሥቃይ መሞት እንደሚሻላቸው በመረዳቴ ደሥ አለኝ። ቢሄንም ግን ይህ ድርጊት በአእምሮየ እየተመላለሠ ሥለረበሸኝ ከሥራየ ልለቅ ችያለሁ። በወቅቱ ይህ ሁሉ የሚፈጸመው በትግራይ ክልል ፕሬዘዳንት በገብሩ አሥራት ቀጥተኛ ትእዛዝ ነበር።”

የቀድሞው ጠ/ሚ/ር ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን የሰሞኑ ሕዝባዊ ቁጣ ለቤተሰቧና ለንብረቷ እንድታስብ እንዳደረጋት ገለጸች


Screen-Shot-2015-12-16-at-3.54.28-AM
ወ/ሮዋ በፌስቡክ ገጿ እንዳለችው “በሰሞኑ በሚሆነው ነገር በጣም በጣም የሚያሳዝን ነው። እኛ እንግዲህ አስራ ሰባት አመት ትግል ቦኅላ ለዚህ ድል በቅተን ደርግን ገርስሰን ለመላው ኢትዮጵያዊ ዲሞክራሲ ያለባት አገር መስርተናል። እና መለስ ልጅነቱን በሙሉ የለፋበትን አላማ ዛሬ በዚህ ብጥብጥ ባነሱ አደገኛ ቦዘኔዎች ከልማት ታቅበን መቀመጥ በጣም ያሳዝናል በእውነቱ። ስራ አቁሞ ሰልፍ ሲሰለፉ መዋል ምን ይባላል? ብንሰራ አይሻልም? እንደ የድሮ ስርአት ነፍጠኞች ያሁኑ አገር ባይበጠብጡ ይሻላል።”
ወ/ሮዋ አክላም ” ትልልቅ አዋቂ ሰዎች የመለስ አይምሮ ያፈለቀውን ራእይ የሚያስፈፅሙ አሉ ተመርጠው በህዝብ መቶ ድምፅ ተሰጥቷቸ እያሉ አሁን ለምን አገር ይረበሻል? እኔ በእውነቱ ከሆነ ለቤተሰብ ለንብረቴ ማሰብ ጀምሬያለሁ። እርግጠኛ ነኝ ብዙዎች እንደኔው ማሰብ መስጋት ጀምረዋል። ጥሩ አይደለም ሰላም እና መረጋጋት ያስፈልጋል በመጀመሪያ።” ብላለች::
ስለ ባሏ ራዕይ ከሞተ በኋላም እንዲነገር የምትፈልገው ወይዘሮ አዜብ ሕዝብ የመለስን ፓርክ በማቃጠሉ የተሰማትን ስሜት ስትገልጽም “የመለስ እሚያህል ትልቅ ሰው በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ እማይታወቅ ሰው፣ ከዚህ በፊትም እንዳልኩት በፔሮል የሚተዳደር ፕሬዚደንት በሶስት ሺህ ብር ደሞዝ የትም አለም የለም። እና ዛሬ ለመታሰቢያ አንድ ፓርክ ቢሰራ እነዚ ሰልፍ ወጡ የተባሉ አደገኛ ቦዘኔዎች አቃጠሉ አሉ። ሀዘኔ መሪር ነው በእውንት ከሆነ። መለስ ቢያየን ያፍርብናል። ራእይ ሰጥቶን ያ ሁሉ አይምሮ ጨምቆ አውጥቶ እኛ እንዲ ወደ ድንቁርና ስንሄድ ያሳዝነዋል። በቶሎ መንግስ ፀጥታ ሊያስከብር ይገባዋል። እነዚ ቦዘኔዎችም ለፍርድ መቅረብ አለባቸው።” ብላለች::
የቀድሞው ጠ/ሚ/ር ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን የሰሞኑ ሕዝባዊ ቁጣ ለቤተሰቧና ለንብረቷ እንድታስብ ካደረጋት ቀጣይ እቅዷ ገንዘቧን አሽሽታ ወደ ሌላ ሃገር መፈርጠጥ? ይህ የሕዝብ ጥያቄ ነው::

እርግዝና እና ወሲብ


pregnancy-sex1pregnancy-sexበዚህ ወቅት በፊት የነበራችሁ ጥሩ የወሲብ ህይወት በጣም እንዳይቀየር ዋናው መፍትሄ ስለምትፈልጉት እና ስለሚሰማችሁ ነገር በግልፅ መወያየት ነው። ሁለታችሁንም የሚያረካ መፍትሄ ፈልጉ። ከዚህ በታች ብዙ ጥንዶች ስለ ወሲብ የሚያሳስቧቸው ነገሮች ተዘርዝረዋል። በሃገራችን ባህል ስለነዚህ ጉዳዮች በግልጽ ማውራት ሊከብድ ይችላል። ይህ ከሆነ ከባለቤትሽ/ባለቤትህ ጋር በመሆን ይህንን ፅሁፍ ማንበብ ነገሮችን ሊያቀል ይችላል።
የግብረ ሥጋ ግንኙነት በእርግዝና ወቅት በእናቲቱ ወይም በልጁ ላይ ችግር ይፈጥር ይሆን?

ይህ ጥያቄ ብዙዎችን የሚያሳስብ ነው። በአጠቃላይ መልሱም በፍፁም ነው። ሴቷ በወሲብ ወቅት በምትረካበት ጊዜ በማህፀን ላይ የመኮማተር (የመጫን) ስሜት ሊፈጥር ይችላል። የእምስ ግርግዳ ስለሚሳሳ በግንኙነት ወቅት በትንሹ ሊደማ ይችላል። እኚህ ሁኔታዎች ባይመቹም በብዛት አደጋ የላቸውም። ለመጀመሪያ ጊዜ የደማሽ እንደሆነ ወይም አደማምሽ ካሳሰበሽ ሃኪምሽን አማክሪ። የደማሽው መጠኑ ብዙ ከሆነ ግን በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ሂጂ። በባለቤትሽ ብልትና በልጅሽ መካከል ብዙ ርቀት ስላለ በተጨማሪም ልጅሽ በማህፀን ግርግዳ፣ እንዲሁም የማህፀን በሩን ዘግቶ ባክቴሪያና የውንዱ የዘር ህዋስ እንዳይገባ በያዘው ዝልግልግ መድፈኛ ከዚያም አልፎ በክርታሱና ውስጡ ባለው የሽርት ውኃ ተከልሎ ስለሚገኝ ወሲብ ልጅሽ ላይ የሚፈጥርበት ችግር አይኖርም።

ጥሩ ግንኙነት ስለመፈፀም

ብዙ እናቶች በእርግዝና ምክንያት በሰውናታቸው ውስጥ ባሉ ሆርሞኖች አማካኝነት እና የብልት ግርግዳዎች ስለሚለሰልሱ በወሲብ ወቅት በቀላሉ ለመራስ ይችላሉ። ስለዚህም በዚህ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ይመቻቸዋል። በጣም ጥሩው ጊዜ በተለይ የመጀመሪያው ሶስት ወር (ብዙ ማቅለሽለሽ የሚሰማበት) ካለፈ በኋላ ፅንሱ ትልቅ ሆኖ ሆድ በጣም እስከሚገፋ በመኃል ያለው ነው።

ሆድሽ ወደፊት ሲገፋስ?

ሆድሽ በሚገፋበት ጊዜ ለወሲብ የሚመች አኳኋን ማግኘት ከባድ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ዋናው ነገር የሚመቻችሁን አይነት መንገድ እስክታገኙ መሞከር ነው። ሴቷ በጎኗ ብትተኛ ወይም በጉልበቷ ብትንበረከክ የበለጠ ሊመቻችሁ ይችላል።

ወደ እርግዝና መጨረሻ

በዚህ ጊዜ የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል። ጉልብት የበዛው ግንኙነት ማድረግ አይመከርም። ቢሆንም አንደኛው ወገን ወሲብ ማድረግ ፈልጎ ሊላኛው ወገን ባይፈልግ ሌሎች ፍቅርን ለመግለፅ ሊደረጉ የሚችሉ ነገሮች አሉና መረሳት የለባቸውም።

ከወሊድ በኋላ

ወሊድ በእያንዳንዷ እናት ላይ የሚፈጥረው ስሜት ይለያያል። ቀላል ወሊድ ከነበረ በቶሎ ወደነበረው ሁኔታ ለመመለስ ይቀላታል። ከባድ ወሊድ ያሳለፈች እናት ደግም አእሮዋም ሆነ ሰውነቷ ዝግጁ እስኪሆን ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድባት ይችላል። በወሊድ ወቅት የማህፀን መውጫ እና አካባቢው ሊቆስልና ህመም ሊሰማ ይችላል። ሆኖም ይሄ የሚድን ሁኔታ ነውና ሊያሳስብሽ አይገባም። በሰውነትሽ ውስጥ ያለው የኤስትሮጅን መጠንም ይቀንሳል። በዚህ ምክንያትም እንደበፊቱ እርጥበት ላይሰማሽ ይችላል፤ ነገር ግን ይሄ የተለመደ ነው። ሊረዳሽ የሚችል ቅባት በፋርማሲዎች ስለሚገኝ ሐኪምሽን ማማከር ትችያለሽ።

ከወሊድ በኋላ ግንኙነት ማድረግ የሚቻለው መቼ ነው?

ከአራት እስከ ስድስት ሳምንት በኋላ ሁኔታዎች በፊት እንደነበሩት ለመመለስ ቢችሉም ብዙ ጥንዶች የበለጠ ጊዜ ይወስድባቸዋል።፡አዲስ ወላጆች እንደመሆናቸው በቤታቸው ለመጣው እንግዳ ህይወት ብዙ ትኩረት ስለሚሰጡ ላያስባቸውም ይችላል። አብሮ በመተኛት እና በመጨዋወት ቀስ በቀስ ድሮ ወደነበረው ፍቅራቸው በሂደት መመለስ ይችላሉ። ይህ እንደገና ለመላመድ እድል ይሰጣቸዋል። ስለስሜታቸው በግልፅ መወያየት በጣም ጥሩ ነው። በተጨማሪ ስለዚህ ጉዳይ ሐኪምን ማማከር ይቻላል።

አዲሱ የታንዛኒያ ፕሬዘዳንት ስልጣን በያዙ በጥቂት ቀናት ውስጥ እነዚህ አስገራሚ ነገሮች አድርገዋል።


12308730_1071309952902256_4593188065234626811_nጆን ማጉፉሊ ይባላሉ የዛሬ ወር ነበር ስልጣን የተረከቡት ታዲያ በአንድ ወር ውስጥ ያረጉትን ይመልከቱ…
1. የመጀመሪያ እርምጃቸው የታንዛኒያ የነፃነት ቀን በዓል እንዳይከበር ማድረግ ነው፣ ለምን? በርካቶች በኮሌራ በሽታ እየሞቱ የነፃነት ቀን ማክበር ነውር ስለሆነ ለበዓሉ የሚወጣውን ወጪ ብሄራዊ የፅዳት ቀን ተብሎ ሁሉም አካባቢውን በማፅዳት እንዲጀምር አዘዋል። በዚህም መሰረት ከትላንት በስቲያ December 9 በታንዛኒያዊያን የነፃነት ቀን ታንዛኒያዊያን ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ አካባቢያቸውን ሲያጸዱ ውለዋል
2. ሙሂምቢሊ የተባለ ሆስፒታልን ከጎበኙ በኋላ ባዩት አስቸጋሪ ሁኔታ ለፓርላማ አባላት የሚወጣውን የመዝናኛ ዝግጅት ገነዘብ ለዚህ ሆስፒታል እንዲውል አዘዋል፣ ታዲያ በጥቂት ቀናት ውስጥ ሆስፒታሉ 300 አዳዲስ አልጋዎች ተገዝተዋል እንዲሁ የማይሰሩ የሆስፒታሉ መሳሪያዎች በታዘዘው 200Million Shilling ተጠግነዋል።
3. ስልጣን በያዙ በሶስተኛው ቀን የመንግስት ባለስልጣናት ወደ ውጭ ሀገር የሚያረጉትን ጉዞ ሰርዞ በምትኩ ወደ ገጠር ከተሞች ተጉዘው የህዝቡን ችግሮችን እንዲከታተሉና መፍትሄ እንዲያመጡ አዘዋል። ውጪ ሀገር የሚያስኬዱ ጉዳዩች ሀገሪቱዋን ወክለው ውጪ ባሉ አምባሳደሮች እንዲፈጸሙ አዘዋል።
4.ከፕሬዝዳንቱ፤ ከምክትል ፕሬዝዳንቱ እና ከጠቅላይ ሚንስተሩ ውጪ ያሉ ባለስልጣናት የአውሮፕላን ጉዞ ሲያደርጉ ከፍተኛ ማዕረግን እንዳይጠቀሙና አብዛኛው ህዝብ በሚጠቀመው በመደበኛ ማዕረግ እንዲጠቀሙ አዘዋል
5.የመንግስት መስሪያ ቤቶች ስብሰባዎችን እና ወርክ ሾፖችን ውድ በሆኑ ሆቴሎች ካሁን በኋላ እንዳያደርጉ አስታውቀዋል በየሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ያሉት ክፍሎች በቂ እንደሆኑ አስታውቀዋል
6. እቃ የጫኑ 350ኮንቴኖሮች በዳሬሰላም ወደብ መጥፋታቸውን ተከትሎ የታንዛኒያን የገቢዎች ሀላፊ ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሀላፊዎች አባረዋል
7.አዲሱን ፓርላማ ለመክፈት ወደ ዶዶማ 600ኪሜ በመኪና ነው የሄዱት፤ በፓርላማው መክፈቻም ላይ ባለስልጣናት ነገሮች እንደድሮ ይሆናሉ ብለው እንዳይጠብቁ እና ህዝቡ የመረጣቸው ንግግር እንድናደርግ ሳይሆን ችግሮቻቸውን እንድንፈታላቸው ነው ብለዋል
8. ለበአለ ሹመታቸው ይወጣ የነበረውን $100,000(2 ሚሊዮን ብር) ብር ወደ $7000(140,000) በመቀነስ የቀረውን ለሆስፒታል ሰጥተውታል
ለሌሎች ሀገሮችም መሪዎች ምሳሌ ለሚሆኑት ለታንዛኒያው አዲሱ ፕሬዝዳንት ላይክ በማድረግ አድናቆቶን ይግለጹ

«Al-Shamiyya Front የተባለ የሶሪያ አማፂ/ተቃዋሚ ታጣቂዎች ግንባር ለፅንፈኛው አሸባሪ ISIS ምርኮኞች እጅግ ልብ የሚነካ ይቅር ባይነት፣ ፅንፍ የሌለው ምህረት አደረጉ»


2015-12-09 at 09-36-41
ነገሩ እንዲህ ነው። የሶሪያ ተቃዋሚ ታጣቂዎች የፅንፈኛው አሸባሪ ቡድን ታጣቂ የሆኑ ምርኮኞችን አሸባሪ ቡድኑ ብዙሃኑን በሚቀላበት/በሚገድልበት መልኩ ብርቱካናማ ቱታ አስለብሰው በጉልበታቸው እንዲንበረከኩ ከተደረጉ በኋላ ሽጉጥ ጭንቅላታቸው ላይ ይደግኑባቸዋል። በዚህ ሰአት የአሸባሪ ቡድኑ ምርኮኞች በደቂቃዎች ውስጥ ሞታቸውን እየጠበቁ ነበር። ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ እዚች ሰአት ላይ የሶሪያ ተቃዋሚዎች ቪዲዮ ላይ ከመቅፅበት “ሙስሊሞች ወንጀለኛ አይደሉም” የሚል መልእክት ተነበበ።
እጅግ እጅግ እጅግ በሚገርም ሁኔታ የአረመኔው አሸባሪ ቡድን አባላት የሆኑትን ምርኮኞች በሽጉጥ ጭንቅላታቸውን ለማፍረስ ተዘጋጅተው የነበሩት የሶሪያ አማፂያን ታጣቂዎች ሽጉጣቸውን ከሽብር ቡድኑ ምርኮኞች ጭንቅላት ላይ በማንሳት በኩራት እና በአሸናፊነት ፊታቸውን አዙረው ሲሄዱ ያሳያል።
‪#‎ከዚያም_ቀጥሎ_በሙስሊም‬ የአለባበስ ስርዓት ነጭ ልብስ የለበሰ እና የሐይማኖቱ መገለጫ የሆነ ነጭ ቆብ ያደረገ አንድ የእስልምና እምነት ሰባኪ ድንገት ከፊታቸው ድቅን አለ፣ ምርኮኞቹም አንገታቸውን ካስደፋቸው ስራቸው ካቀረቀሩበት በግድ ቀና አሉ። ነጭ ለባሹ ሰውም ስለ ፍትህ/Justice በዝርዝር አስተማራቸው/አስረዳቸው፣ ሰው በላው አሸባሪ ቡድን እስከዛሬ በግፍ ለጨፈጨፋቸውና እንደ እንስሳ ላረዳቸው ንጹሃን የነፈገው ርህራሄ/ምህረት/ይቅርታ በውስጡ ምን ያህል ጉልበት/ሃይል እንደነበረ አሳያቸው።
አል- ሻይማ የተባለው የሶሪያ ተቃዋሚ ግምባር ፕሬዝዳንት ሼክ መሐመድ ካቲብ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ “ልትገሉን ከፈለጋችሁ ይኸው እንካችሁ ጎራዴያችን። እንዲህ ያለው የእናንተ ግድያ እምነታችንን ያጠናክርልናል/ያጠብቅልናል። ለኛ ቸርነት የሕይወት መርሃችን ነው።”
ሆኖም ከዚህ ሁሉ በኋላ ከላይ ስለ ፍትህ በተሰበከላቸው በተማሩት መሰረት ምንም እንኳን ከሞት/ጭንቅላታቸው በሽጉጥ ከመመታት ምህረት/ይቅርታን አግኝተው በሕይወት ቢቆዩም ለፍትህ ሲባል ለፈፀሙት ውስጥን የሚያሳምም ወንጀል በእስር እንዲቀጡ ተደርገው ወደ ወህኒ ወርደዋል።
(☞ ይቅርታ የሚጠይቅ እና ይቅር የሚል ልቦና ይስጠን። በድሎ ይቅርታ መጠየቅ የህሊና ሸክምን ያቀላል፣ የህሊና ሰላምን ያላብሳል። ተበድሎ ይቅር ማለት ከአምላክ ያስታርቃል፣ ብልህና አስተዋይ ሰው ያደርጋል። ይቅር ያለ ይቅር ይባላል፣ ይቅር ያላለ ይፈረድበታል።)
http://www.mirror.co.uk/news/world-news/syrian-rebels-force-isis-captives-6973430?ICID=FB_mirror_main
CLICK HERE TO WATCH THE VIDEO