የሳሞራ ታማኝ የአድዋው ተወላጅ ሜ/ጄኔራል መሃመድ ኢሻ የአማራ ምድር ኮማንድ ፖስቶች አዛዥ ሆኖ ተሾመ


mohamed-ishaአለበል አማረ እንደዘገበው
ጄኔራሉ የአድዋ ተወላጅ ሲሆን የጄ/ል ሳሞራ የቅርብ ታማኝና እስከ 2008 አጋማሽ የአግአዚ ክ/ጦር ዋና አዛዥ የነበረ ነው። ጄኔራሉ ምንም ፊደል ያልቆጠረ፣ ከህወኃትና ከሳሞራ ሌላ እምነት የለለው ድፍን ነው። ጀኔራሉ በ23/02/09 ከሌላው ከሜቴክ በለስ ስኩአር ፋብሪካ ስ/አስኪያጅ ከሆነው ኮ/ል ገ/ሚካኤል ሃጎስ ጋር በመሆን በአዊ ዞን ጃዊ ወረዳ ህዝባዊ ስብሰባ ጠርተው ነበር፤ በስብሰባው የአዊ ዞን አስተዳዳሪወች፣የጃዊ ወረዳ ካቢኔዎች፣በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት፣በብረታ ብረት ኮርፖሬሽን ሜቴክ አመራር ሰራተኞች እና ከግንባታ ድርጅቶችና የአካባቢው ነዋሪወች የተካተተበት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ ማብራሪያና ማስፈራሪያ ለመስጠት ያለመ ነበር።
በስብሰባው በጀኔራሉ በአዠንዳነት ከተገለፁ ነጥቦች፤
1. በሁሉም የአማራ ምድር በዞን እና በወረዳ ደረጃ ኮማንድ ፖስት ማቋቋምና በነውጥ(በነሱ አማርኛ) ተሳታፊ የነበሩ ግለሰቦችን በሚደረገው ጥቆማና ማጣራት ለፍርድ ማቅረብ፤ጥፋተኛ ነን ብለው አምነው ተጸጽተናል ብለው ራሳቸውን አጋልጠው ለሚቀርቡት ደግሞ እንደ ጥፋታቸው መጠን ታርመውና ታድሰው መኖር እንዲችሉ ማድረግና ይህንንም ህዝቡ እንዲያውቀው ለማድረግ፤
2. ማንኛውም አካል ነውጠኞችን በማጋለጥ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ ለህዝቡ ለማቅረብ፤
3. በህዝባዊ አመጹ ንብረታቸው የወደመባቸው ግለሰቦችን ካሳ ለመስጠትና ወደነበሩበት ለመመለስ ዞኑ እንቅስቃሴ መጀመር እንዳለበት ለመንገርና ይህም የህብረተሰቡን ተሳትፎ የሚሻ በመሆኑ ህዝቡን ለመቀስቀስና መዋጮም እንዲያዋጣ ለመንገር፤
4. በአዋጁ መሰረት እያንዳንዱ ከያዘው ሞባይል ጀምሮ በአዋጁ የተቀመጡትን እገዳዎች ማክበር እንዳለበትና እራሱንና አካባቢውን ከነውጠኞች እንዲጠብቅ ትዕዛዝ ማስተላለፍ ነበር፤
በዚህ መሃከል በነበሩ ዲስኩሮች ጄነራሉ ያለፋ ነግስታቶቻችን ለመተቸት ሲሞክር ተደምጧል። በተለይም ህዝቡን ቋቅ ያሰኘና እና ያስጠየፈ ነገር ቢኖር ጀኔራል ተብየው የሚያወሩትን የማያውቁና እና በርሳቸው አፍ እምዬ ምኒልክን ለመተቸት መሞከራቸው ነበር። የአሜሪካ የምርጫ ሂደትም በዚሁ ወደል ማህይም በጥቂት ቢልየነሮች የሚመራ መንግስት፣ለባለሃብት የቆመ መንግስት እያለ ለመተቸት ሲውተረተር ሲታይ ተሰብሳቢው በሳቅ እና በጩሀት አቁአረጠው ።
በመጨረሻም ተሰብሳቢው ለጀኔራል ተብየው በርካታ ጥያቄወች በማንሳት ጀኔራሉ መመለስ ተስኗቸው ሲቁለጨለጩ መዋላቸውና መጨረሻም ተሰብሳቢው ስብሰባውን በራሱ ኃይል በትኖት ወደ ቤቱ መሄድ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አረጋግጧል።

Advertisements