አሁን የደረሰ ዜና…..ዳባት…ወያኔ ጋር ትንቅንቅ


ሰሜን ጎንደር ዳባት ከተማ ላይ የጅምላ እስርና ስቃይ እየተፈፀመ ነው። ከተማዋ በትግሬ አዛዥ በሚመራ አጋዚ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ውላለች።
*ወጣት ሽማግሌ ሳይሉ በጅምላ በየቤቱ እየገቡ እየደበደቡ እያሰሩ ነው። በጣም ብዙ ወጣት እያመለጠamhara ዱር ቤቴ እያለ ነው። ህዝቡ በጣም ተበሳጭቷል። ወያኔ የጎንደር አብዮት መነሻ በሆነችው በዳባት ላይ የበቀል ዱላውን እየሰነዘረ ነው። የአጋዚ ሰራዊት በአቅራቢያ ከተሞች የፍተሻ ኬላ ከፍቶ ወጣት እያሰሩ ስለሆነ ጥንቃቄ ይደረግ።
*ወያኔ በለስ ቀንቶት ስልጣን ላይ ከመውጣቱ በፊት ዳባት ታሪካዊ የወልቃይት ጠገዴ የወረዳ ዋና ከተማ ነበረች።
ከቦታው ያናገርናቸው ዳባቴዎች ይህ አፈና ቁርጠኝነታችንን ይጨምራል ወያኔን እስከሞት እንጋፈጣለን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በያለበት ጠላት ላይ በመረባረብ ወያኔን እንደምስስ ብለዋል። የጀግና ቃል። ይህን እየዘገብኩ እንኳን እኔኑ አይዟቹህ የሚሉ ጀግኖች! እባካቹህ ደጀን እንሁናቸው።
ስማቸው የደረሰኝን ታሳሪዎች እያጣራሁ እለጥፋለሁ… እስካሁን ባለኝ መረጃ የሚከተሉት ታስረዋል::

1. አዳሙ መኩሪያው
2. አመሀ ማሞ
3. መላኩ ፉንቱ
4. አቶ ምትኬ እንዳለ (ታዋቂ የሃገር ሽማግሌ)
5. ሚኪያስ ንጉሴ
6. እንዳልክ ተስፉ (ርእሰ መምህር)
( ሙሉነህ ዮሃንስ)

Advertisements