ሰበር ዜና ሪፖርተር ጋዜጣ እና አዲስ አድማስ የድምጻችን ይሰማ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ እንዲያጨናግፉ በጀት ተሰጣቸው!!


የበረከት ስምኦን እና የሽመልስ ከማል የጡት ልጆች የሆኑት ሪፖርተር እና አዲስ አድማስ በኢትዮጵያ እየተቀጣጠለ ነው ብሎ ወያኔ የሰጋበትን የሙስሊሞች እንቅስቃሴ በፕሮፓጋንዳው መስክ በተለየ ሑኔታ እየዘገቡ ህዝቡን እንዲያሳምኑ መመሪያ በማስተላለፍ ለዚህ ጉዳይ የሚሆን በጀት እንደተመደበላቸው ዉስጥ አዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::

አደርባይ የሆኑት እና በወያኔ ትእዛዝ የሚሽከረከሩት እነዚህ ጋዜጦች አቶ ሽመልስ ቢሮ ተጠርተው በተለያዩ ሚዲያዎች እና የማህበራዊ ድህረ ገጾች የሚተላለፈውን ጸረ መንግስት እንቅስቃሴ ከመንግስት ጎን በመቆም እንዲታገሉት እና እየተስፋፋ ያለውን የሙስሊሙን ህብረተሰብ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ያመች ዘንድ አስፈላጊዉን የፕሮፓጋንዳ ስራ እንዲሰሩ እና ለዚሁም መንግስት አስፈላጊዉን እገዛ እንደሚያደርግላቸው ቃል በመግባት ለመጀመሪያ ጊዜ በነብስ ወከፍ 70.000 የኢትዮጵያ ብር ለያንዳንዳቸው በድምሩ 140.000 ብር በጥሬ ገንዘብ ተሰጥቷቸዋል::

የወያኔ መንግስት በመንግስት ሚዲያዎች ላይ የተነሳውን የህዝብ ጥላቻ በተደጋጋሚ እየተወያየበት መሆኑን የሚናገሩት የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች የህዝብ ግንኙነት ስራ የሚሰሩ ሰዎቻቸውም ቢሆን በተለያዩ የጥቅማጥቅም ጥያቄ የመጣ እየተሰላቹ መሆኑን ሲናገሩ በመንግስት በኩል ግን ጠንክረው ከሰሩ ጉርሻ እንደሚሰጥኣቸው ኣቶ በረከት ብተለያየ ወቅት እየነገሩዋቸው ነው ::

በቅርቡ ይከፈታል ተብሎ የሚጠበቀው የሪፖርተር ቴሌቭዥን ጣቢያም ከዚህ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ጋር የተያያዘ እና የታቀደ እንደሆነ ታውቁዋል::እንዲሁም አዲስ አድማስ ፕሮፖሳል እንዲያቀርብ የተነገረው ሲሆን በዚህ መሰረት መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ አቶ ሽመልስ ከማል ተስፋ ሰተውታል::
ከዚህ ቀደም በአዲስ አድማስ ላይ የነበረው የምንሊክ ሳልሳዊ ብሎግ በሽመልስ ከማል ተዛዝ መታገዱ ይታወሳል :: ሳልሳዊ ከከተባቸው ብሎጎች አንዱ
http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_lyftenbloggie&author=62222628&Itemid=11

Advertisements