አቶ በቀለ ገርባ፣ ዮናታን ተስፋዬና ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ስማቸው ቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ተለጥፏል ተባለ


Bekele-Gerba
በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት እሳት መነሳቱን ተከትሎ መንግስት 23 ሰዎች መሞታቸውን ሲናገር ሐ ሌሎች ምንጮች የሟቾቹን ቁጥር ከ49 ከፍ አድርገውት ስንዘግብ ቆይተናል:: ሕወሓት መራሹ መንግስት ዛሬ በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት በሕይወት ያሉ እስረኞች ዝርዝር ይለጠፋል ባለው መሰረት በርካታ ወላጅ በጠዋቱ ቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ተገኝቷል::

Yonatan-Tesfaye-Facebook

በዚህም መሠረት በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት በተለጠፈው ማስታወቂያ ላይ ታዋቂውና ሰሞኑን ስለደህነነታቸው አነጋጋሪ ሆነው የቆየት ፖለቲከኛ አቶ በቀለ ገርባ፣ ዮናታን ተስፋዬና ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ስማቸው ተለጥፏል ሲሉ በስፍራው ስማቸውን ተመልክቻለው ያለው ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ በፌስቡክ ገጹ ዘግቧል::

አቶ በቀለ ገርባ; ዮናታን ተስፋዬ ደጀኔ ጣፋና አዲሱ ቡላላ እዚያው ቅሊንጦ እንደሚገኙ ስማቸው ሲለጠፍ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራውና ፍሬው ተክሌ ወደ ዝዋይ መወሰዳቸው ስማቸው ተለጥፏል ብሏል:: አቶ አንጋው ሰጠኝም ወደ ሸዋሮቢት ተወስደዋል ተብሎ ስማቸው ተለጥፏል::

እስረኞች በዝዋይ, በቃሊቲና በሸዋሮቢት እንደተወሰዱ ቀድመው የተዘገበ ሲሆን በነዚህ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ አለ ተብሎ ስሙ ያልተለጠፈ እስረኛ በሕይወት የለም ማለት ነው::

ጉዳዩን ተከታትለን እንዘግባለ

Advertisements

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s