የቅሊንጦን ግድያ የፈፀሙት የትግራይ አጋዚዎች መሆናቸውን፤ የማረሚያ ቤቱ ፖሊስ ምስክርነት ሰጠ (ኢ.ኤም.ኤፍ)


14191955_10210143480254247_5039184246326511135_nበቅሊንጦ እስር ቤት ውስጥ፤ ሆን ብለው እሳት በማስነሳት እስረኛውን ከትልቅ ማማ ላይ ሆነው ሲረሽኑ የነበሩት የትግራይ ተወላጆች፤ የአጋዚ ወታደሮች እንደነበሩ የኦሮሞ ተወላጅ የሆነውና በወቅቱ ከግቢው እንዲወጣ የተደረገ አንድ የፖሊስ አባል ገለጸ። ይህ በቀጥታ ከጥበቃ አባል ፖሊስ የተላለፈ መልእክት ነው። በመንግስት በኩል ተገቢው ምርመራ ተደርጎ ይህንን የጅምላ ግድያ በፈጸሙ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ካልወሰደ፤ በእርግጥም ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ “ያለምህረት እርምጃ እንዲወሰድ መመሪያ ሰጥቻለሁ” ያሉት እንዲህ ላለው ግድያም ጭምር ነው ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። ለማንኛውም የአይን ምስክሩ ፖሊስ ቃል ከዚህ በታች እንዳለ ቀርቧል።

“ዓርብ ማታ የማናውቀው አንዱ ትግርኛ ተናጋሪ ትግሬ መጣና ለተወሰኑ ሰዎች ቀጭን ትዕዛዝ አስተላልፎ ሄደ፡፡ ከዚያች ሰዓት ጀምሮ እኔ የማውቃቸው የኦሮሞ ፖሊሶች በሙሉ ከተመደቡበት ቦታ ተቀይረው ወደ ሌላ ከእስር ቤቱ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄዱ፡፡
ዓርብ ሌሊት ለቅዳሜ አጥቢያ፤ በእስር ቤቱ ውስጥ አደጋ ሊፈጠር ስለሚችል ሁሉም የእስር ቤቱ የጥበቃ ሰራተኞች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ የሚል ትዕዛዝ ተሰጠን፡፡ የእስር ቤቱ ወሳኝ የጥበቃ ቦታዎችና ማማዎች እንዳለ በአጋዚዎች እንዲሸፈን ተደረገ፡፡ እኔም ከሩቅ ከእስር ቤቱ ጥበቃ ውጭ በቅርብ ርቀት ላይ አከባቢውን ዱላ ብቻ ይዤ እንድቃኝ ተመደብኩ፡፡

ነገሩ ከወትሮው አዲስ ሆኖብን ግራ ቢገባንም ትዕዛዙን ለምን እንዴት ብለን እንኳን የመጠየቂያ እድል ስላልነበረን መመሪያውን ተቀብለን ቅዳሜ ጠዋት ደረሰ፡፡

አራት ሰዓት ሊሆን አካባቢ ትንሽ ግር ግርና ተኩስ ተጀመረ፡፡ በዚያን ሰዓት ምንም የእሳት ጭስም ሆነ ነበልባል አይታይም ነበር፡፡ እኔ ከሩቅ ሆኜ መንገደኞችን ከመከልከል ውጪ ጠጋ ብዬ ሁኔታውን ለማጤን እድሉ አልነበረኝም ነበር፡፡
ትንሽ እየቆየ ሲሄድ ተኩሱ በረታ! አሁን የእሳት ጪስ መታየት ጀመረ፡፡ ከጥበቃ ማማው ላይ የነበሩ አጋዚዎች ወደታች በቀጥታ ሲተኩሱ አየሁ፡፡
“ነገሩ ምንድነው?” ብዬ ጠጋ ማላት ጀመርኩ፡፡ አሁን እሳቱ እጅጉን እየነደደ መጣ፡፡ ቤት ውስጥ የነበሩ እስረኞች ራሳቸውን ለማዳንና ወደ ውጪ ለመውጣት መታገል ጀመሩ፡፡ ቃጠሎ በነበረበት አካባቢ በአብዛኛው ሁሉም እስረኞች በሚባል ደረጃ ከግቢ ሳይሆን ከእስር ቤቱ ውስጥ ወጥተው ተመልሰው እሳቱን ለማጥፋት ሲረባረቡ በአይኔ ተመልክቻለው፡፡ ትንሽ ቆይቶ በፍፁም ለማመን በሚያስቸግር ሁኔታ አዲስ ነገር ማየት ጀመርኩ፡፡
እሳቱን እያጠፉ ባሉ እስረኞች ላይ ካላይና ከታች አጋዚዎች የጥይት እሩምታ ማዝነብ ጀመሩ፡፡ እውነት ለመናገር አንድም እስረኛ ለማምለጥ ሙከራ ያደረገ አልነበረም። በቃ ብዙ እስረኞች በጥይት ተመተው መሬት ላይ ሲወድቁ አየሁ፡፡ ገሚሶቹ ጓደኞቻቸው በጥይት ተመተው መሬት ላይ ሲወድቁ ባዩ ጊዜ እራሳቸውን ለማዳን ተመልሰው ወደ እሳቱ ውስጥ በድንጋጤ የገቡም አሉ፡፡ ሌሎቹ በግቢው ውስጥ ከጥይቱ እሩምታ ለመሸሽ ወዲያና ወዲህ ሲሉ የተገደሉ ናቸው፡፡ እንዳልኩት በአብዛኛው የሞቱት እሳቱን እያጠፉ በነበረበት ወቅት ነው፡፡
የእሳት አደጋ ሰራተኞች የመጡት በጣም ቆይተው ብዙ ሰው አልቆ በአንቡላን ወደ ሆስፒታል መወሰድ ከተጀመረ በኋላ ነው፡፡ በኔ በኩል የሟቾች ቁጥር ሃያ እና ሰላሳ እንደተባለው ሳይሆን እጅግ በርካቶች ናቸው፡፡ በጣም የሚያሳዝነው በአብዛኛው የጥይቱ ሰለባ የሆኑት በዋህነት እሳቱን ለማጥፋት የተረባረቡ ምስኪን እስረኞች ናቸው፡፡ በሆነው ነገር በጣም አዝኛለሁ፡፡ በእውነት ምን እየተደረገ እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም” በማለት በምሬት የአይን ምስክርነቱን ገልጿል – የቅሊንጦ ፖሊስ የነበረው የኦሮሞ ተወላጅ።
ይህን የአይን ምስክር ስለነ በቀለ ገርባ ተጠይቆ ሲመልስ፤ “እንደነ አቶ በቀለ ገርባ ያሉ ትልልቅ የፖለቲካ እስረኞች ከሌሎች ራቅ ብለው በብሎኬት የተሰራ ልዩ እስር ቤት ውስጥ ስለሚታሰሩ ለአደጋው ተጋላጭ የሚሆኑ አይመስለኝም” ሲል መልሷውል፡፡
ያም ሆነ ይህ ጎበዝ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ያለኸው የሀገሬ ሰው፤ ወደዳችሁም ጠላቹህ ወያኔ በግልጽ ሙሉ ጦርነት አውጆብናል፡፡

የመረጃው ምንጭ፡ የቅሊንጦ ፖሊስ ሲሆን፤ ቃሉን ተቀብላ ያስተላለፈችው ኒሞና ራቢራ ናት።

Advertisements