ፈጣሪ ሆይ የሚያስብልን የምናስብለት ቅን መሪ ስጠን።


RecepTayyipErdoğan_(cropped)በ21ኛው ክ/ዘመን ካሉ ጥቂት እደግመዋለው በጣም ጥቂት ቅን መሪዎች መሐል አንዱ የሆኑት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን የትላንቱ ምሽት የመጨረሻቸው መስሎ ነበር
ባልተጠበቀና ባልተገመተበት ወቅት የግዜው ፍንዳታ ወታደሮች ሀገራቸውን ዳግም ሊቢያ ዳግም ሶርያ ዳግም ግብፅ ለማድረግ የነሆለሉ ወጣቶች ኤርዶጋንን ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ከስልጣን ሊያስወግዱት ወሰኑና እንቅስቃሴያቸውን ጀመሩ
ሴራቸውም ሰምሮላቸው በአጭር ሰአት ውስጥ የሀገሪቱን ታላላቅ ተቋማት በቁጥጥራቸው ስር አዋሉ
ይህቺ የአለም 13ኛዋ የኢኮኖሚ ፈርጣማ ሀገር እቺ የአውሮፓና ኤዢያ አገናኝ ድልድይ ቀደምት ስልጣኔን ከዘመናዊነት ጋር ያስተሳሰረች ሀገር ባልታሰበ ፍጥነት በፍንዳታዎቹ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ወደቀች
cnn bbc pres tv aljezira በአንድነት ስለ ኤርዶጋን ፍፃሜና ስለሚቀጥለው የሚሊተሪው ጉዞ ማውራት ኧለፍም ስል ስለ ስልጣን ክፍፍሉ(ይመስለኛል) በሰፊው ተነተኑት
ይህንን ሁሉ ክስተት ድምፃቸውን አጥፍተው ሲከታተሉ የነበሩት ቅኑ መሪ በመጨረሻም በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ለህዝባቸው አንድ መልእክት እደግመዋለው አንድ መልእክት ብቻ አስተላለፉ <<ህዝቤ ሆይ አደባባዩን በሰልፍ ሙሉት>> አሉ
ህዝቡም የዚህን ቅን መሪ ትእዛዝ ነበርና የሚጠብቀው በደቂቃዎች ውስጥ አደባባዮቹን ሞሏቸው …..አዛውንቶች ህፃናቶች ወጣቶች በልበ ሙሉነት ከታንኮች ጋር እየተጋፈጡ ለባለውለታው መሪያቸው በጭንቅ ሰአት አጋርነታቸውን አሳዩ
ሁሉን ነገር እንደተቆጣጠሩት የተወራላቸው ፍንዳታዎቹ ወታደሮች በደቂቃዎች ውስጥ ህልማቸው እየተነነ እንደ ውሻ እየታነቁ ወደ ማጎሪያ ተላኩ
ታላቁ መሪ ኤርዶጋን የዘራውን አጨደ

ፈጣሪ ሆይ የሚያስብልን የምናስብለት የሚሰዋልን የምንሰዋለት ቅን መሪ ስጠን።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።

Advertisements