አስደንጋጭ ሙስና!


በግልጽ እና በስፋት የሙስናውን መንደር ከተቀላቀሉት እና “ተከታይዋ ወይም ግልገሏ አዜብ”የሚል ቅጽል የወጣላቸው የበረከት ስምኦን ባለቤት አሰፉ በቀዳሚነት ትጠቀሳለች ።

በረከት “አሲ”እያሉ በቁልምጫ የሚጠሯት አሰፉን ጨምሮ 6 የቤተሰብ አባላት በፓርቲው አባላት “ደቂ ማዘር” በሚል መጠሪያ ይታወቃሉ ።የታምራት ላይኔ ባለቤት የዚሁ ቤተሰብ አባል ስትሆን ከብአዴን የወጣችው (ከ6ቱ)እሷ ብቻ ናት ።የታደሰ ጥንቅሹ ባለቤት እንዲሁ የአሰፉ ቤተሰብ አካል ናት ። የበረከት ባለቤት አሰፉ የመንግስት ስራ በመተው ወደ ከፍተኛ ንግድ መግባቷ ምንጮቹ አረጋግጠዋል። በአስመጭና ላኪ ንግድ የተሰማራችው አሰፉ በተለይ ወደ ዱባይ እና ሳኡዲ የተዘጋጁ የከብት ስጋ እና ቡና በመላክ እንዲሁም ከዱባይ እና ቻይና የሞባይል ቀፎዎችን የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን እና የተለያየ ይዘት ያላቸውን ጄነረተሮች በማስመጣት ንግዷን አጧጡፋለች ።አብዛኞቹ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው በጉምሩክ ሰትት ብለው እንደሚያልፉ ሲታወቅ የአዜብ ቀጥተኛ ድጋፍ እና ትእዛዝ እንዳለበት ተጠቁሞአል። አብዛኛውን ጊዜ ሁለቱም አብረው እንደሚያሳልፉ ምንጮቹ ገልጸዋል። በአስር ሚሊዮኖች የሚገመት ዶላር በመዛቅ ላይ የምትገኘው የበረከት ሚስት አሰፉ ለህወሃት ስር የሰደደ ጥላቻ እንዳላት የገለጹት እነዚህ ወገኖች በተደጋጋሚ ይህን አቋሟን በይፋ ስታንጸባርቅ መታየቷን አስታውቀዋል። በሌላም በኩል አባይ ፀሃዬ ለበርካታ ባለሃብቶች በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ብድር በመፍቀድ በቅርብ ስጋ ዘመዶቻቸው በኩል ሃብት እንዳካበቱ ታውቆአል ።

ቀደም ሲል የነበራቸውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሃላፊነት ተገን አድርገው የፈጸሙት ዘረፋ ነው።የሙስናው ተዋናዮች አምስት የአባይ ጸሃይዬ የቅርብ ዘመዶች ናቸው ። ባለሃብቶችን በማግባባት ደላላ ሆነው እየቀረቡ በተፈለገው መጠን የገንዘብ ብድር ማሰጠት እንደሚችሉ ከገለጹ በኋላ ያለምንም ውጣ ውረድ አባይ ጸሃዬ እንዲፈቅዱ ይደረጋል። ከብድሩ እስከ 50 ሚሊዮን ኮሚሽን ይወስዱ እንደነበር ተጠቁሞአል ።ተመሳሳይ ተግባር አቶ ግርማ ብሩ ይፈጽሙ እንደነበር ምንጮቹ አያይዘው ገልጸዋል። በተለይ “ራዲሰን”የተባለው እና ካዛንችስ አካባቢ የተገነባው ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ለግንባታ ተብሎ የተፈቀደለት 400 ሚሊዮን የብድር ገንዘብ እንደሆነ ሲረጋገጥ ከዚህ ገንዘብ ባለስልጣናቱ በኮሚሽን መልክ 150 ሚሊዮን ኪሳቸው እንደከተቱ ተረጋግጦአል። በጣም የሚገርመው ሸራተን ሆቴል እንኳን በአንድ መቶ ሰባ ሚሊዮን እንደ ተገነባ በይፋ እየተነገረ ለዚህኛው ሆቴል ግን ሁለት እጥፍ በብድር ስም ተፈቅዶ ሲመዘበር አቶ መለስ ጭምር ያውቁ ነበር ።በማያያዝም በባንክ ብድር የተሰራው ሸራተን ላለፉት 15 አመታት ብድሩን ያለመክፈሉና ባለፈው አመት ባንኩ የመሰረተው ክስ እንዲቆም መደረጉ አስገራሚ ሆኖአል ።ይህ እዳ ሳይከፈል በባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አቶ በረከት ስምኦን ትእዛዝ 942 ሚሊዮን ብር ለሼሁ ድርጅቶች መፈቀዱ እና በቅርቡ ደግሞ ታግዶአል መባሉ እንቆቅልሽ ከመሆኑም ባሻገር ምን ያክል የተበላሸ እና ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ስርአት አልበኝነት በሃገሪቱ መንገሱ አመላካች ነው ተብሎአል ።

በነገራችን ላይ አቶ በረከት ወደ ደቡብ አፍሪካ በሼሁ ቻርተር አውሮፕላኖች እንደሚመላለሱ ምንጮቹ አረጋግጠዋል። በሌላም በኩል በቃሊቲ- አቃቂ በ7 ቢሊዮን የተቋቋመው ግዙፍ የብረት ማቅለጫ ፋብሪካ ሲጠቀስ ከጀርባ የአንበሳው ድርሻ ባለቤቶች ስዩም መስፍን እና አዲሱ ለገሰ ይገኛሉ ። ከዚህ በማስከተል በተለያዩ ባለስልጣናት የተገነቡ እና እየተገነቡ ያሉ የሙስና ውጤቶች እንመልክት ።በትግራይ መቀሌ ከተማ “ለአካባቢ የአየር ጥበቃ “በሚል ተተክሎ የነበረውን ደን በመጨፍጨፍ መሬቱን የተቀራመቱት ስብሃት ነጋ ፣ቴዎድሮስ ሃጎስ ፣ሃለቃ ጸጋይ፣ጎበዛይ ፣ኪሮስ ቢተው፣ተክለወይኒ፣… ዋና ዋናዎቹ ናቸው ።”አፓርታይድ መንደር”በሚል በነዋሪው በተሰየመው በዚህ ቦታ የተደረገው የአደባባይ የመሬት ቅርምት የተቃወመ የማዘጋጃቤት ሃላፊ ከስልጣን ተነስቶ እስካሁን የደረሰበትም አይታወቅም ።የተጠቀሱት የህወሃት ሹማምንት እጅግ ምርጥ እና ዘመናዊ ቪላ በጥድፊያ እያስገነቡ እንዳሉ ሲታወቅ ባለ ሁለት እና ሶስት ፎቅ የሆኑት ቪላዎች ከአስር ሚሊዮን ብር በላይ ለእያንዳንዱ ቤት ግንባታ መድበው ስራውን ወደ ማጠናቀቅ መድረሳቸውን ማረጋገጥ ተችሎአል ።

በስምንት ሚሊዮን ብር የተገነባው የኪሮስ ቢተው ዘመናዊ ባለ ሁለት ቪላ ግንባታው በቅርቡ እንደተጠናቀቀ ታውቆአል። ሽማግሌው ስብሃት በቀድሞው የአየር ሃይል ም/አዛዥ ጄነራል ሰለሞን እና በአሜሪካ በሲያትል እና በዋሽንግተን ዲሲ በሚኖሩ ስምንት የስብሃት የአጎት እና የአክስት ልጆች ስም በአክሲዮን ሽፋን የከፈቱት “ሉሲ አካዳሚ”ከሙስና የተገኘ ትልቅ የገቢ “ዘረፋ” ምንጭ ሆኖአል ።አካዳሚው በገርጂ እና ሳር ቤት – ባለ ስድስት ፎቅ ህንጻ አቅፎአል። የፌደራል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር ሃሰን ሺፋ በቦሌ ያስገነቡት ባለሁለት ቤት ቪላ ተጠናቆ በየወሩ 25 ሺህ ብር መከራየት ጀምሮአል። የጄነራል ሳሞራ ቪላ ከለንደን ካፌ ፊት ለፊት ሲገኝ ከ1997 አመተ ምህረት ጀምሮ በየወሩ 30 ሺህ ብር ይከራያል። ባለ ሶስት ፎቅ የአባዱላ ቪላ ከሳሞራ ቪላ ቀጥሎ ሲገኝ ከሚያዚያ 97 አመተ ምህረት ጀምሮ በየወሩ 4 ሺህ ዶላር ለነጮች ይከራያል። ቦሌ ኤርፖርት መግቢያ ከኖክ ማደያ ጀርባ የብርሃነ ገ/ክርስቶስ እና የአዲስአለም ባሌማ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ባለሶስት ፎቅ ምርጥ ቪላዎች ይገኛሉ።በ1988 አመተ ምህረት የተገነቡት የሁለቱ ቪላ ሁለት የአሜሪካ ከፍተኛ መኮንኖች እያንዳንዳቸው በአራት አራት ሺህ ዶልር ተከራይተውታል። ከኢምፔሪያል ሆቴል አጠገብ የተገነባው እና በሰባት ሚሊዮን ብር ወጪ የተሰራው የተፈራ ዋልዋ ባለ ሦስት ፎቅ ቪላ በወር 30 ሺህ ብር መከራየት የጀመረው በ97 አመተ ምህረት መጨረሻ ነበር።

የሙስናው ዝርዝር እና ስፋት በጣም ሰፊ ነው ።ወደ ውጭ እየሸሸ የሚገኘው የሃገር እና ህዝብ ሃብት ሳይካተት ማለት ነው ። በዚህ አጋጣሚ ሳይጠቀስ የማይታለፈው በታይላንድ ባንኮክ የሚጸመው አሳዛኝ የሙስና ድራማ ነው። በርካታ የህወሃት ጄነራሎች እና ሌሎች ባለስልጣናት ከራሳቸው አልፈው የቅርብ ዘመዶቻቸውን እና ውሽሞቻቸውን ጭምር በከፍተኛ ወጭ ማሳከምን ተያይዘውታል። ከህወሃት ጀነራሎች መካከል ጄነራል ሰአረ እና ጀነራል ተስፋዬ በዋናነት ይጠቀሳሉ ።የሆስፒታሉ የህክምና ወጭ እንዲሁም የሚያርፉባቸው ባለ5 ኮከብ ሆቴሎች (ኢንተር ኮንቲኔታል እና ቻል ዲፖሎ )ናቸው ። በየሶስት ወሩ በሚቀርበው የክፍያ ዝርዝር ሪፖርት ከሰባት እስከ አንድ ሚሊዮን ዶላር እንደሚከፈል የቅርብ እማኞች ያስረዳሉ። ከፍተኛ ክፍያ የተፈጸመው ለአባዱላ ገመዳ ልጅ ነው ።የሶስት አመቷ ህጻን ዲቦራ አባዱላ ስትወለድ የአንጀት ፣የሳምባ እና የአእምሮ ችግር ነበረባት ….

Advertisements