ለኢህአዴግ የመጨረጫው መጨረሻ ማስጠንቀቂያ ከወደ ጎንደር ተሰማ – ከተማ ዋቅጅራ


እንደዚህ አይነት እብሪት የሚመጣው ስልጣን የዘላለም የሚመስላቸው እና በመሳሪያቸው ብዛት ተመክተው ሁሌም እራሳቸውን እንደአሸናፊ አድርገውtimthumb ከሚያስቡ ደካማ እና ስህተታቸውን ከማይቀበሉ ሰዎች ዘንድ ነው። እንደነዚ አይነቶቹ ሰዎች ምንም ልቦናቸው በክፋት እና በትእቢት የተወጠረ ቢሆንም ቅሉ ቀድሞ ከስህተታቸው እንዲመለሱ እና ሊቀበሩበት የሚችለውን ጉድጓድ መቆፈራቸውን እንዲያቆሙ ቀድሞ በተለያየ መንገድ እና በተለያዩ አመልካች ሰዎች የማስጠንቀቂያ መልዕክት ይነገራቸዋል።

ሕዝቤን ልቀቅ የሚለው ቃል ለፈርኦን ሲነገረው የልመና ቃል ሳይሆን የማስጠንቀቂያ ቃል ነበረ። የፍራቻ ሳይሆን የትእዛዝ ነበረ። የፈርኦን መልስ ግን ሕዝብህን አለቅም እግዚአብሔርንም አላውቅም የሚል የእብሪት ቃል ነበረ ምላሹ። ይሄንን ቃል ላስተዋለው በሙሴ እና በፈርዖን መካከል የተደረገውን ሁለት ጎራ እንደሚፈጥር የታወቀ ነው። በሙሴ ወገን የነበሩት ፈርዖን ፈጽሞ እንደሚጠፋ ስሙም ታሪክ ብቻ ሆኖ እንደሚቀር ሲያውቁ….. በፈርዖን ወገን የነበሩ ደግሞ የጀግንነት የአሸናፊነት ያልበገርነት መስሏቸው ፈርዖን ጀግና ነው የጀግና ዘር ብለው ማስጠንቀቂያውን ከመስማት ይልቅ ፈርዖንና ተከታዮቹ ልቦናቸውን በማደንደን የበለጠ በትእቢት እንዲወጠር አደረጋቸው። ወይ አስተዋይ መሪ አልያም አስተዋይ ህዝብ ከሌለ የጥፋት ማእበሉ በራፋቸው ደርሶ እብሪነታቸውን አይተውም።

ሙሴም እግዚአብሔር እንደሚያዘው ማድረግ ጀመረ… የመጀመሪያው መቅሰፍት ወደፈርዖንና ወደ ህዝቡ መጣ የዚህን ግዜ ፈርዖን እና ሕዝቡ ተጨነቁ ፈርኦንም ሙሴን አለው…. ሙሴ ይሄ መቅሰፍት ከአገሬ እንዲጠፋ አድርግልኝ እንጂ ህዝብህን እለቃለው አለው። ሙሴም እንዳለው አደረገለት የመጣው መቅሰፍት እንዲጠፋ አደረገ። መቅሰፍቱ ከራቀ በኋላ ተመልሶ ሕዝብህን አለቅም በማለት የጭቆና ቀንበሩን መልሶ ይጭንባቸውዋል። እንዲ እንዲ እያለ ዘጠኝ የማስጠንቀቂያ መቅሰፍቶች በፈርዖን እና በሕዝቡ ላይ ይወርድ ጀመረ መቅሰፍቱ ሲመጣ እለቃለው ብሎ ተማጽኖ ያቀርባል መቅሰፍቱ ሲርቅለት ተመልሶ ጭቆናውን ይቀጥላል አስረኛው መቅሰፍ እና የመጨረሻው መጨረሻ ማስጠንቀቂያ በፈርዖን እና በሕዝቡ መጣ። በፈርኦን ግዛት ውስጥ የሚኖሩት የበኩር ልጆቻቸውን የሚገድል መቅሰፍት ተላከባቸው የበኩር ልጆቻቸው በሙሉ በሞት ተመቱ የዚህን ግዜ ፈርዖንና ህዝቡ ደንግጠው ሙሴን እንዲ አለው ህዝብህን ለቅቄአለው ብሎ ተናገረው ይዘህ ወደ አገርህ ግባ አለው። ሙሴም ህዝቡን ይዞ ከፈርኦን ግዛት መውጣት ጀመረ። ሙሴም ባህረ ኤርትራን ለሁለት ከፍሎ ህዝቡን በደረቅ መሬት በመሃሉ መሻገር ሲጀምሩ ፈርዖን ልቡ አንዴ ደንድኗልና ከለቀቃቸውም በኋላ በመቆጨቱ መልሼ በግዞት መያዝ አለብኝ ብሎ ሰራዊቱን በሙሉ በማዝመት ሙሴን እና እዝቡ ወደግዞቱ ሊመልስ ወደ ኤርትራ ባህር ደረሰ ሙሴም ባህሩን እንደ ግንብ አቁሞ ህዝቡን እያሻገረ እያለ ሙሴ በከፈለው ባህር ውስጥ ፈርዖንና ሰራዊቱ ገቡ ሙሴም ህዝቡን አሻግሮ ከጨረሰ በኋላ ባህሩን ከደነው የፈርዖን ሰራዊት ከነሙሉ ሰራዊቱ ሰጥመው ላይመለሱ ፍጻሜአቸው ሆኗል።

በፈርዖን ግዛት ውስጥ ወንድ የወለዱ እስራኤላውያን በሙሉ ይገደልባቸው ነበረ ያላለቀሰች እናት ያላዘነ አባት የለም ነበረ። ግፍ ሲበዛ ግፍ አድራጊው መጥፊያውን ያቀርባል ይባላል።

ዛሬም እንደ ፈርዖን ልቦናቸውን ያደነደኑ ሲነገራቸው የማይሰሙ ትዕግስት እንደ ፍራቻ የህዝብም ድምጽ በንቀት የሚመለከቱ በስልጣናቸው እና በመሳሪያቸው ተመክተው የማስጠንቀቂያ ደውሎችን ረግጠው እና ጨፍልቀው የሚያልፉ የመስጠሚያችሁ ባህር ከፊታቹ እንዳለ ላሳውቃችሁ እወዳለው።

selam bus gonderለኢህአዴግ ብዙ ምልክቶች ተነግረውታል ብዙ ማስጠንቀቂያዎችም ደርሰውታል በማን አለብኝነት እና በመሳሪያ ኃይል አፈንኩኝ ብሎ ያስባል እንጂ… ከአዲስ አበባ ጀምሮ የተነሱ የህዝብ የማስጠንቀቂያ ማዕበል መልስ ሳይሰጣቸው ተዳፍነው እንዲቀሩ ተደርጓል። ልብ በሉ ተዳፍኗል እንጂ አልጠፋም። በኦሮሚያም የተነሳው የህዝብ ማእበል አሁንም መልስ ሳይሰጥበት በመሳሪያ ኃይል እንዲዳፈን ተደርጓል። በጋንቤላም የተነሳው እንዲሁ እንዲዳፈን ተደርጓል። ይሄን ሁሉ ሲያደርግ ግን ኢህአዴግ ፍጹም የበላይ ነኝ ብሎ ነበረ። የኢትዮጵያ ህዝብ ለውጥ እንሻለን …100% ተሸንፈህ 100% አሸነፍኩኝ አትበል… ውሸት ሰለቸን… ነጻነት እንሻለን… አደባባይ የወጣውን ህዝብ የኔ በሚላቸው ታጣቂዎች ህዝቡን በመፍጀት የተነሳውን የህዝብ ማእበል ትክክለኛውን መልስ ሳይሰጥ በኃይል እንዲዳፈን ተደርጓል።

የአዲስ አበባው፣ የሰንዳፋው፣ የጋንቤላው፣ የአንቦው፣ የወለጋው፣ የባህር ዳሩ፣ የወሎው፣ የአሪሲው፣ የሃረሩ፣ የባሌው፣ የሻሸሜኔው እያልን ስንቀጥል ለኢህአዴግ ፈጽሞ ከመጥፋታቸው በፊት የተነገራቸው የማስጠንቀቂያ ምልክቶች ቢሆኑም ቅሉ ሊጠቀሙበት አልቻሉም። ጭራሽ 5 ሚሊዮን ሆነን 90 ሚሊዮንን አንቀጥቅጠን የምንገዛ ጀግና የጀግና ዘር ነን ገና ቂጥ ቂጣችሁን እያልን 100 አመት እንገዛችኋለን በማለት በህዝባችን ላይ ይዘባበታሉ። ልብ በሉ እሳቱ በሁሉም ኢትዮጵያ ውስጥ ተዳፍኖ ነው ያለው።

ለኢህአዴግ የመጨረጫው መጨረሻ ማስጠንቀቂያ ከወደ ጎንደር ታይቷል።

bus eየመጨረሻ መጨረሻ ማስጠንቀቂያ በጎንደር ህዝብ ተነግሮታል። ይሄ ማስጠንቀቂያ ለኢህአዴግ የመጨረሻ መጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነው።ከዚህ ቀደሙ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ድምጻቸውን ለማሰማት ወደ አደባባይ የወጡትን በጥይት እየቆሉ የተቀረውን ደግሞ ቤት ለቤት እየገቡ ያለበደሉ ለእስር እየዳረጉ አሰቃቂ ግፍና በደል በማብዛት ለአመታት አሰቃይተዋል። ማንም እኔን አይነቀንቀኝም ሲልና ሲፎክር የነበረ ኢህአዴግ የጎንደር ህዝብ በሁለት ቀን የመጨረሻ መጨረሻቸውን ማስጠንቀቂያ አሳይቷቸዋል። እንደለመዱት ገድዬ እና አፍኜ እወስዳለው በማለት የመጣውን ጎንደሬዎቹ ገድለውና ማርከው የመጨረሻው መጨረሻህ ደርሷል ሞት ደጃፋችሁ እንደደረሰ ነጻነት ለህዝቡ እንደመጣ እወቁ ብሎ ነግሯቸዋል። ካሁን በኋላ ገላችሁ እና ማርካችሁ መሄድ ሳይሆን ተገላችሁም ተማርካችሁም የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነትን የሚያውጅበት ቀን ቅርብ ነው ሲሉ የጎንደር ህዝብ አሳይቷቸዋል።

የጎንደሩ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ለኢህአዴግ የመጨረሻ መጨረሻ ማስጠንቀቂያ ደውል ነው። ከዚህ በኋላ እንደድሮው አፍኜ እቀጥላለው ማለት ወደማይቀረው እና ኢህአዴግ ላይመለስ ወደሚሰጥምበት ባህር ውስጥ መግቧቷ ነው። ካሁን በኋላ ምንም አያመጡም ጀግና የጀግና ዘር እኛ ነን የምትለዋ ተረት ግዜዋ ያለፈችበት ቀልድ እንደሆነች ተረዱ። በኢትዮጵያ ዙሪያ የተዳፈነው እሳት አመዱን ገለጥ አድርጎ ይነሳል ያም እሳት የህዝብ ባህር ይባላል የመጨረሻውን የኢህአዴግ የመጨረሻዋ ሞትን የሚያበስራት ኃይን ነው። ይህንን ስል እያስፈራራው አይደለም ወይንም ያለምክንያት አይደለም የሚታይ እና ሊመጣ የተቃረበ እውነት እንጂ።

ማሳሰቢያ 1:- ከተለያዩ ኢትዮጵያ ምድር በአማራነቱ ሲፈናቀል ሲገደል ዝም ያለ ሁላ… ከተለያዩ ከኢትዮጵያ ምድር የኦሮሞ ገበሬ መሬቱ ተነጥቆ ሲባረር እና ሲገደል ዝም ያሉ ሁላ ባእድ እንኳን ሳይቀሩ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ጋንቤላ ገብተው ህዝባችንን ጨፍጭፈውና ማርከው ሲወስዱ ዝም ያሉ ሁላ ሌላም ሌላም ግፎች በአገሪቷ ሲፈጸም ያልተነፈሰ ሰላም ባስ ተቃጠለ ሆቴል ፈረሰ ንግድ ቤት ተቃጠለ እያሉ የሚሊዮኖች የሰው ነፍስ ሲጠፋ እና የሚሊዮኖች መብት ሲረገጥ ሳይጨንቃቸው ለቁስ የሚያለቃቅሱትን መልስ አትስጧቸው። በተለይ በተለይ ትላልቅ ሚዲያዎች የሚዲያ አካሎች መስራት ያለባችሁን ትክክለኛውን ስራ ብቻ ስሩ። ማልቀስ ካለባቸው ያልቅሱ.. መጮህ ካለባቸው ይጩሁ… መመለስ ካለባቸውም ይመለሱ… ስለነሱ በደልና ችግር መናገር ካለባቸው እራሳቸው መሆን አለባቸው እንጂ እነሱ እንዲ ናቸው እንዲ አያደርጉም ብሎ ያልሰሩትን እና ያላሰቡትን መናገር የበለጠ እንዲኮፈሱ ሲለሚያደርጋቸው ቢታሰብበት ጥሩ ነው።

ማሳሰቢያ 2:- ምርጫውን 100% በኦሮሚያ አሸነፍን ባሉበት ማግስት 100% በአማራ አሸንፍን ባሉበት ማግስት 100% በአዲስ አበባ አሸንፍ ባሉበት ማግስት 100% ከሁሉም አቅጣጫ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። በከፍተኛ የመንግስ የስልጣን ቦታውን የያዛችሁ ኢትዮጵያዊያኖች በእድሜ የሸመገላችሁም አላችሁ ልጅ እና የልጅ ልጅም ያያችሁ አላችሁ ሌላው ቢቀር ለልጃችሁ እና ለልጅ ልጆቻችሁ ስትሉ ለዚህች አገር ሰላም በእውነት መስራት አይገባችሁምን? እስከ መቼ ሕሊና ተሸጦ ጥቅም ብቻ በመፈለግ ስልጣንን በኃይል ለማቆየት የሚፈጸመውን ግፍ ትክክል ነው ትላላችሁ? አገር ስትጠፋስ እንዴትስ ቆማችሁ ትመለከታላችሁ? ልጆቼ ብላችሁ ለምትጠሯቸው ለአብራካችሁ ክፋይ ጨለማን ለማውረስ ስቃይን ለማስረከብ ስለምን ልቦናችሁ አሰበ? የሰው ክብሩ እውነተኛነቱ እና አገሩ ነው። እውነትን እና በነጻነት የሚኖሩባትን አገር ለማውረስ ስለምን መልካም መስራት ተሳናችሁ? ግዜው እየረፈደ ነውና ነጻነት ከሚፈልገው ህዝብ ጋርና ከእውነት ጋር የምትቆሙበት ሰዓት አሁን ነው። ይህንን ሳታደርጉ ብትቀሩ ግን ለሚመጣው ነገር ጥርስ ሟፏጨት ብቻ ይሆናልና ይታሰብበት።

ማሳሰቢያ 3:- ለአርቲስቶች… ገጣሚ በግጥሙ ጸሃፊም በጽሁፉ ዘፋኙም በዘፈኑ ስለ አገር ፍቅር፣ አንድነት፣ ህዝባችን ለይ ስለሚደርሰው ግፍ፣ ወደፊት ስለሚመጣው አደጋ፣ ባጠቃላይ የኢትዮጵያን ህዝብ ስሜት እና በደል ያለፍራቻ እውነትን በመናገር ህዝባችንን ታስተሳስሩት ዘንድ ትልቅ አቅም አላችሁ። ይሄንን አቅማችሁን ተጠቅማችሁ ከህዝብ ጎን የምትቆሙበት ሰአቱ አሁን ነውና ስለምትወዱት እና ስለሚወዳችሁ ህዝብ ብላችሁ ስለምትወዷት ኢትዮጵያ አገራችሁ ብላችሁ ብዕራችሁን አንሱ እና በተሰጣችሁ ጸጋ በድምጻችሁ ለህዝብ ያላችሁን ፍቅርና ለአገራችሁ ያላችሁን ስሜት አሰሙ። ነገሮች የከፋ ደረጃ ላይ ደርሶ እንዲ ብልና ባደርግ ተብሎ የሚቆጭበት ግዜ ሳይመጣ አሁኑኑ ሁሉም አርቲስት ለአገሩ እና ለህዝቡ ቅድሚያ ይስጥ። የህዝብ ወዳጅ ማን እንደሆነ የሚለይበት ግዜ ተቃርቧልና ይታሰብበት። ፈሪ አይጸድቅም… ገለባም አይበቅልም… ይባል የለ።

ሳጠቃልለው :- ኢህአዴግ ሆይ የተናገሩትን እያነቁ ማሰር እና መግደል ጋዜጠኞንን እና ጸሃፊዎችን እያነቁ ማሰርና መግደል አቁሙና የመጨረሻ መጨረሻ የማስጠንቀቂያ ደውሉ በጎንደር ህዝብ ስለተነገራችሁ ቆም ተብሎ ይታሰብ።ይሄ ሳይሆን ቀርቶ አሁንም የተለመደውን የማፈን ስራ በመስራት ስልጣኔን አስቀጥላለው የሚለውን ተረት ካልተዋችሁ የኢትዮጵያ ህዝብ የተዳፈነው እሳትን አራግፎ ለነጻነቱ በመነሳት ነጻነቱን የሚያውጅበት ቀን ተቃርቧል እና በህዝብ ባህር ሰጥሞ ከመጥፋት በፊት ቢታሰብበት መልካም ነው እላለው። አበቃው።

Advertisements