ቴዲ አፍሮ በካናዳ ዌኒፔግ ከንቲባ እጅ ሽልማቱን ተቀበለ


teddy-afro-1

ዝነኛው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ በካናዳዋ ዌኔፔግ ግዛት ውስጥ ከፍተኛውን ሽልማት ከሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተቀበለ:: ቴዲ ዛሬ ምሽት በዌኔፔግ ከተማ በተደረገ የሽልማት ስነ ስር ዓት ላይ የትውልዱ ኮከብ ተሸላሚ (Star of the generation) የተሰኘ የክብር ሽልማትን ተቀብሏል::
ቴዲ ከሽልማቱ በኋላ በሰጠው አስተያየት “በካናዳ ዊኒፔግ ከተማ (The Star of a Generation Award) የዘንድሮ አመት ተሸላሚ በመሆኔ ለዊኒፔግ ከተማ ከንቲባ እና ለከተማው ኗሪ በሙሉ ምስጋናዬ ከልብ ነው።” ሲል ገልጿል::

በካናዳ ቶሮንቶ ባለፈው ሳምንት ሃሙስ በሺህዎች የሚቆጠሩ አድናቂዎቹ በተገኙበት ሥራዎቹን ያቀረበው ቴዲ አፍሮ በካናዳ የተለያዩ ግዛቶች በመዘዋወር ኮንሰርቶቹን እንደሚያቀርብ የቅርብ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::

ቴዲ ዛሬ ማምሻውን በርካታ ካናዳውያን እና ኢትዮጵያውያን አድናቂዎቹ ሽልማቱን ሲቀበል እንደተለመደው “ፍቅር ያሸንፋል” ብሏል:: ሽልማቱ የርሱ ብቻ እንዳልሆነና በጣም መደሰቱንም ገልጾ ላከበሩት ክብሩን ገልጿል::

Advertisements