ሁለት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አበረታች መድሃኒት መጠቀማቸው በመረጋገጡ ለአራት አመት ከውድድር ታገዱ


fd1bc1596c8a6a0a55119f8ecb0beca5_Lሁለት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አበረታች መድሃኒት መጠቀማቸው በመረጋገጡ ከውድድር መታገዳቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

ፌዴሬሽኑ በላከልን መግለጫ የአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የፀረ አበረታች መድሃኒቶች ዲፓርትመንት እና የፀረ አበረታች መድሃኒቶችና ቅመሞች ኤጀንሲ ባደረጉት የላብራቶሪ ምርመራ አትሌት ጣእሞ ሹምዬ ወልደገብርኤል እና አትሌት ስንታየሁ መርጋ እጅጉ የአበረታች መድሃኒቶች እና ቅመሞች በትክክል መጠቀማቸውን ማረጋገጣቸውን ጠቁሟል።

በዚህም መሰረት አትሌቶቹ ከጥር 25 2016 ጀምሮ እንዲታገዱ ለፌዴሬሽኑ ማሳወቃቸውንም አመላክቷል።

ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌቶቹ በአበረታች መድሃኒቶችና ቅመሞች መውሰድ ተጠርጥረው ምርመራ ከተጀመረባቸው እና ውሳኔ ከተሰጠባቸው ጃንዋሪ 25 2016 ጀምሮ የሚፀና ከማንኛውም የአትሌቲክስ ውድድር ለአራት አመት እንዲታገዱ ወስኗል።

ፌደሬሽኑ በአበረታች መድሃኒቶችና ቅመሞች ዙሪያ በቀጣይም በመላ ሀገሪቱ የጀመረውን የግንዛቤ ማስጨበጥ እና የቁጥጥር ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የፀረ አበረታች መድሃኒቶች ዲፓርትመንት እና የፀረ አበረታች መድሃኒቶችና ቅመሞች ኤጀንሲ ከዚህ ቀደም ስድስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አበረታች መድሃኒቶችና ቅመሞች ተጠቅመዋል በሚል ምርመራ መጀመሩ ይታወሳል።

Advertisements

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s