ኢሳት ሰበር ዜና ) በጎንደር ህዝባዊ አመጹ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎአል


13645236_1117312414976542_698316397470244866_nትናንት እስከ ምሽቱ አራት ሰአት በተደረገው የተኩስ ልውውጥ በርካታ የህወሃት ታጣቂዎች ተገድለዋል። ጥቃቱን የፈጸሙት የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢዎችን ለመታደግ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ጎንደር ከተማ የገቡ ነዋሪዎች ናቸው። በተኩሱ ልውውጥ መሃል ከወልቃይት ጠገዴ ጥያቄ አቅራቢዎች መካከል አቶ ሲሳይ ታከለ፣ አቶ ሰጠኝ፣ አቶ አለቃ እስበሶም እና ሌሎች ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎችም ሲገደሉ፣ በፌደራል ፖሊስና በህወሃት ደህንነት አባላት በኩል ደግሞ በርካታ ወታደሮች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በርካታ ወጣቶች እንደተገደሉም መረጃዎች እየወጡ ነው።

ተቃውሞው ዛሬም የቀጠለ ሲሆን አንድ የህወሃት የንግድ ድርጅትና አንድ የፌደራል ፖሊስ መኪና መቃጠላቸው ታውቋል።

በተጣቂዎች ተከበው የነበሩት ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ እርሳቸውን ሊረዱ በመጡ ሰዎች ታግዘው እየተኮሱ ማምለጣቸውን እየተነገረ ነው። ኢሳት ግን በትክክለ ስለማምለጣቸው ማረጋገጥ አልቻለም።

ኢሳት

Advertisements

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s