ኢትዮጲያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በጽጋቡ ገብረማርያም አማካኝነት በአለም ቁጥር አንድ የብስክሌት ውድድር በሆነው Tour-de-France ላይ በመካፈል ላይ ትገኛለች ፤ ግን ብዙም የሚዲያ ሽፋን አላገኘም ?


 

13615383_1043673169021507_1480619484186211141_n

ኢትዮጲያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በጽጋቡ ገብረማርያም አማካኝነት በአለም ቁጥር አንድ የብስክሌት ውድድር በሆነው Tour-de-France ላይ በመካፈል ላይ ትገኛለች፤ ክስተቱ ትልቅ እና በሀገራችን ላሉ ወጣቶች ተስፋ የሚሰጥ ቢሆንም ክስተቱ ግን ብዙም የሚዲያ ሽፋን አላገኘው በዚህ ያዘነው Ztseat Saveadna Ananya የሚከተለውን ጽፋል

ኢቢሲ በታሪኩ ሰፊ ሽፋን ነፍጎት የማያውቀውን Tour-de-France ለምን ዘንድሮ ያለዐመሉ ስሙን እንኳ ለመጥራት ተጠየፈ?- መልሱ- “ፅጋቡ ስላለበት፣ ስለደመቀበትም” ይሆን?….ይመስላል…በጣም ይመስላል

አስታውሳለሁ የቱር ደ ፍራንስ ውድድር ባለበት ወቅት በተለይም ሰለሞን ገብረእግዚአብሄር የሚባል ነባር ጋዜጠኛ ለጀሮ ብዙ ባልተመቸ ድምፁ ስለ አርምስትሮንግ፣ ካቨንዲሽ፣ አልቤርቶ ኮንታዶር፣ ፍሎይድ ላንዲስ ወ.ዘ.ተ በየቀኑ የሚያወራ ምድብተኛ ነበር፡፡ ስለነ ኮንታዶር፣ አርምስትሮንግ ሲያወራ በከፍተኛ ወኔ ነበር፤ እንደውም ስለ ሐገሩ ብሔራዊ ቡድን የሚያወራ ይመስል ነበር፡፡ ብቻ የብስክሌት ውድድር በኢቲቪ ከፍተኛ ሽፋን የሚሰጠው ውድድር ነበር፡፡
2016ን እንይ የቀድሞ ኢቲቪ፣ የዘንድሮ EBC በታሪኩ የዘንድሮን ያክል Tour-de-Franceን ሽፋን ነፍጎ አያውቅም- የዘንድሮን የTour-de-France ውድድርን ጨርሶ ስሙ እንዳይነሳ፣ በዐለም አቀፍ ሚድያዎች የኢትዮጵያን ስም በበጎ እያስጠራ ያለን ብርቱ ጥጋቡም እንዲሁ ስሙ እንዳይነሳ የተወሰነ ይመስላል፤

ለምን- ጽጋቡ ገብረማርያም የተባለ እጅግ ምርጥ የኢትዮጵያ ልጅ ስላለ
ለምን ሲሉ- ኢትዮጵያና ፅጋቡ በታሪካቸው ለመጀመርያ ጊዜ በቱር ደ ፍራንስ ተሳታፊዎች ስለሆኑ
ለምን ቢሉ- ፅጋቡ በአስገራሚ ሁኔታ በየቀኑ እጅግ እየተሻሻለ፣ እየደመቀ፣ መልካም የሚባል ውጤት እያመጣ ስለሆነ
ኢትዮጵያ እምብዛም በማትጠራበት የስፖርት መስክ ኢትዮጵያን እያስጠራ ስለሆነ፤
ጽጋቡ ገብረማርያም ስለሆነ….….ምክንያቱ አንድምም ብዙም ሊሆን ይችላል…

በጣም አሳፋሪም፣ አስገራሚም፣ አሳዛኝም ነው፤ የሚያስገርመው ነገር፤ የኤርትራ ቲቪ ከኢብኮ የተሻለ ሽፋን እየሰጡት መሆኑ ነው! EBCዎች እጅግ አፍረንባችኃል፤ በዚህ ክፉ ስራችሁ ልታፍሩ ይገባችኃል፤ ይህንን ዝም ብሎ የሚመለከት የኢትዮጵያ መንግስት፣ በተለይም የስፖርትና የወጣቶች ሚኒስቴር… ልታፍሩ ይገባችኃል!

ለጽጋቡ ላይክ እና ሼር በማድረግ ድጋፎን ይስጡ

Advertisements