ዶክተር መረራ ጉዲና አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ከሰ


13592648_10206799327562653_1235297475823341349_nአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፕሮፌሰርነት የደረጃ እድገቴን ያለ አግባብ ከልክሎኛል ያሉት ዶ/ር መረራ ጉዲና፤ ከዩንቨርስቲው ማግኘት የሚገባኝን የአገልግሎትና ልዩ ልዩ ክፍያዎችም ነፍጎኛል ሲሉ ክስ አቀረቡ፡፡

ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ መናገሻ ምድብ ሥራ ክርክር ችሎት የቀረበው የዶክተር መረራ የክስ ማመልከቻ፤ በዩንቨርስቲው ውስጥ ከግማሽ በላይ ዕድሜዬን ያገለገልኩና ብርቱ፣ ብቁና ተጠያቂ ዜጐችን ሳፈራ የቆየሁ ሲሆን ለፕሮፌሰርነት ደረጃና የሙያ እድገት ብቁ የሚያደርገኝን መስፈርቶች ሁሉ ያሟላሁ ቢሆንም፣ የፕሮፌሰርነት ደረጃውና እድገቱ በ3 ወር ጊዜ ወስጥ ሊፈቀድልኝ ወይም ሊሰጠኝ ሲገባ፣ ያለ ሕግ አግባብ መብቴን ተነፍጌአለሁ ይላል፡፡
ዩኒቨርሲው ያለ ህግ የነጠቀኝን መብቴን እንዲሰጠኝና የፕሮፌሰርነት ማዕረጉ እንዲፈቀድልኝ፣ እንዲሁም በዩንቨርስቲው ውስጥ ለረዥም ዓመት የሰራሁበት የአገልግሎት ክፍያም 282 ሺ 960 ብር እንዲከፈለኝ እጠይቃለሁ ብለዋል በክሳቸው ፡፡ዶክተር መረራ በአሁኑ ወቅት በአሜሪካን አገር ይገኛሉ፡፡
ይሄው ነው የኢህአዴጓ ኢትዮጵያ ለስብሃት ነጋ የክብር ዶክትሬት ትሰጥና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማቷ በመምህርነት ሞያ ለአመታት ያገለገሉትን እንደ መረራ ያሉትን በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ ‹‹ባዶ እጃቸውን ትሰዳለች››፡፡የዜና ምንጭ አዲስ አድማስ