በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የውጪ ግንኙነት ኰሚቴ፣ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ አዲስ ህግ አጸደቀ


13501626_1180161788681697_292345056669483640_n#‎Ethiopia‬ ‪#‎USA‬ ‪#‎SenBenjaminCardin‬ ‪#‎VOAAmharic‬ ‪#‎HR‬
በሜሪላንዱ ዴሞክራት፣ በሴናተር ቤንጃሚን ካርዲን የቀረበውና S.Res.432 የተሰኘው የሰብዓዊ መብት ማስከበሪያ ህግ፣ በምክር ቤቱ የውጪ ጉዳዮች ኰሚቴ መጽደቁ ተገለጸ።
እአአ ባለፈው ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም በ114ኛው ኮንግሬስ ላይ የቀረበውና የጸደቀው ህግ፣ በኢትዮጵያ ሁሉን ያካተተ አስተዳደር እንዲኖርም ያበረታታል። የቴኔሲው ሬፓብሊካን ሴናተር ቦብ ኮርከር ህጉን በመደገፍ፣ ዋናውን የህጉን አቅራቢ ሴናተር ቤንጃሚን ካርዲንን፣ እንዲሁም ተባባሪ አቅርቢ ሴናተሮችንአመስግነዋቸዋል።

Advertisements