ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን ከአውሮፓ ህብረት አባልነት ለመነጠል በመወሰኗ ምክንያት ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ገለፁ


eabad652bc67462d5ac48b80077b86b2_XLብሪታንያ በህዝበ ውሳኔ ከአውሮፓ ህብረት አባልነት ለመነጠል መወሰኗን ተከትሎ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን ስልጣናቸውን እንደሚለቁ አስታውቀዋል።

የህዝበ ውሳኔው የመጨረሻ ውጤት ይፋ ከተደረገ በኋላ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ካሜሮን ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው እንደሚለቁ የተናገሩት።

ብሪታኒያ በቀጣይ ጥቅምት ወር አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ይኖራታልም ብለዋል።

ካሜሮን ላለፉት አራት ወራት ብሪታንያውያን ከህብረቱ ጋር እንዲቆዩ ሲወተውቱ መቆየታቸው ይታወሳል።

ከህብረቱ መውጣት ኢኮኖሚያዊ እና የደህንነት ችግር ይፈጥራል በሚል ህዝባቸው በህዝበ ውሳኔው በህብረቱ ለመቆየት ድምፅ እንዲሰጥ ቢጠይቁም አልተሳካላቸውም።

በትናንቱ ህዝበ ውሳኔ 17 ሚሊየን 410 ሺህ 742 ብሪታንያውያን (51 ነጥብ 9) ከህብረቱ እንነጠል ሲሉ፤ 16 ሚሊየን 141 ሺህ 241 መራጮች (48 ነጥብ 1) ከህብረቱ ጋር እንቀጥል በማለት ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

ብሪታንያ ከ43 አመታት በኋላ 28 አባል ሀገራት ካሉት የአውሮፓ ህብረት አባልነት የወጣች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisements