ስድስት የፖሊስ ሰራዊት አባላት ተገደሉ!


በልኡል አለም
በብሔራዊ መረጃ ትእዛዝ አደገኛ የግድያና የምርመራ ዘዴዎችን በመጠቀም ንጹሐን ኢትዮጵያዊያንን ሲያሰቃዩና እርምጃ ሲወስዱ የነበሩ ስድስት የብሔራዊ መረጃና ተደራቢ የፖሊስ ሰራዊት አባላት ሚስጥር እንዳያወጡ በሚል መነሻ ምክንያት በብሔራዊ መረጃዉ የዉስጥ ደንብና ክትትል የደህንነት ክፍል ትእዛዝ በተለያየ ውቅትና ግዜያት በተለያየ መንገድ መገደላቸዉን የዉስጥ ምንጮች አሳወቁ።
1. ሙሉቀን ይርጋ
2. ሰለሞን ከድር
3. ሰብስቤ ዘረሰናይ
4. የ10 አለቃ ስለሺ በርሄ
5. የ10 አለቃ ደርቤ ጉታ
እንዲሁም አንድ ለግዜዉ ማንነቱ ያልታወቀ የመረጃዉ ክፍል ግለሰብን ጨምሮ አፋኞች፣ገራፊዎችና ገዳዮች ከነተሸከሙት የግፍ ሚስጥር መወገዳቸዉን ለማረጋገጥ ተችሏል።
ህወሃት በኢትይጵያ ህዝብ ላይ የሰራዉ የግፍ ጽዋ ሞልቶ መፍሰስ በመጀመሩ እርስ በእርስ መበላላቱ ወደ አደገኛ ቀዉሳ እያመራ ለመሆኑ ሁኔታዎች ከማመላከታቸዉ በተጬማሪ ከላይ በስም ከተዘረዘሩት መካከል ሰብስቤ ዘረ ሰናይና ሙሉቀን ይርጋ በአደገኛ መርዝ መመረዛቸዉና ከብዙ ህመም በሗላ ህይወታቸዉ ማለፉን መረጃዎች አሳዉቀዋል፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !