ለተሰደደው የሲኖዶስ አባላት | ከመኳንንት ታዬ


ephremይመስለኝ  የነበረው በክርስትናው አለም የመጀመሪያው ህግ እግዚያብሔርን ከመፍራት ጥበብ የሚነሳና በሌሎች ሰዋዊ ስነምግባር ታንፆ አንድ ሙሉ ሰው ሊያደርገው የሚችለውን ውህድ በማንነቱ ክህሎት ላይ ባለቤት ሊያደርጉት  የሚችሉትን  ባለመስመር ቀለሞች  ሰው ወደሚለው ምእራፍ  አልፈው ክርስቲያን  የሚያሰኘበውን መታወቂያ ያሰጡታል ብዬ አስባለሁ።በዚህ ሁሉ ውስጥ ሞራል  የሚባል ነገር  ደሞ  ትህትና ለሚሉት የባህሪያት ሁሉ የበላይ ለሆነው መልካምነት ውበት ሆኖ ይገለፃል የሚል እምነት  ነበረኝ ።ነበረኝ ለማለት ያነሳሳኝ  አሁን የለኝም ለማለት ሳይሆን ወደ ቤተክርስቲያን ጎራ ብዬ ለአበው ካህናት ከላይ  ያለኩትን አምነቴን  ማሻማት ስጀምር  ከመንገድ ሆኜ ሁሉ አንድ አደለም ቆብና ባለቤትነት  ይለያያሉ የሚለውን ካርድ ሳይ እምነቴን ቆም ብዬ  እንድፈትሽ አደረገኝ ።ለዚህም ነው ነበረኝ ለማለት የተገደድኩት ።

እስቲ ከላይ ለመንደርደሪያ ያህል ይህን ካልኩ ወደ ዝርዝር ጉዳዬ ልግባ ።ለመፃፍ ያነሳሰኝም አባይት ጉዳይ  ወደ አሜሪካው ገዳም  የተሰደዱ አባቶች መስመሩን በመርገጥ ለምን እንደሚፎርሹ  ሳስብ አለማው አልገባ ይለኝና  እቸገራለሁ።በደርግ መውደቂያ ማግስት ጎጠኛው የኢሃዲግ መንግስት ሐገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ የቀድሞን ፓትሪያሪክ አቡነ መርቆሬዮስን ከስልጣን በማባረሩ ምክንያት እሳቸውም የስጋ ገዳም ወደሆነችው አሜሪካ እንደ እኛው ተሰደዱ።መልካም አባቶቻችን ግንባራቸውን ለጥይት ሰጥተው  ሃገራቸውን ከጠላት ተከላክለው ለትውልዱ   አስረከቡ እንጂ ሐገር ጥለው መሸሸጊያ ፍለጋ  አልፈረጠጡም ።በርግጥ ሁሉም እኩል የሆነ ፀጋ የለውም ።ስለዚህ አባታችን  የኔ አቅም እስከዚህ ነው ካሉ ምንም ማለት አልነበረም።ማለት የሆነው እዚህ አሜሪካ ከመጡ በኋላ ተከወኑ ድርጊቶች ናቸው ።ሲጀመር አስተዳደር  አይሰደድም።ሲኖዶስ ማለት የግለሰብ ሐብት ሳይሆን  የ ኢ/ተ/ቤ/  መንፈሳዊ አስተዳደራዊ ስርአት ነው ።

ይህ    በእንዲህ እንዳለ ሆኖ   በስራ አጋጣሚም ይሆን ሆን ተብሎ ታስቦበት ከሀገር የወጡ የአንድ ሰፈር ልጆች በመሰባሰብ የቅድስት  ቤ/ክ አቁማዳ ፈተው  ትልቁን  ስርአት የልጅ ጫወታ በማድረግ  ሲኖዶስ ተሰዷል አሉን ።በዚህ እግዞ እግዞ ብለን ቀን እየቆጠርን በሐገር ቤት ያለችው ቅድስት  ቤተክርስቲያን  በዘረኛውና በጎጠኛው ወያኔ ስርአት እየደማች መኖሯአና ልጆቿ መስዋትነት እየከፈሉ መኖራቸው ሳያንስ ሲኖዶስ እኛ ነን ካላልን አባ አባ አንባልም በሚል  ሰበብ ይሁን መንፈሳዊ አባት መሆናቸው የሚያንሳቸው ስለመሰላቸው የነ አብነ መልከፀዲቅ  ጎንደር መራሹ የመለኩሴ አባቶች ስብስብ  ሳያሰልስ  በጥፋት ላይ ጥፋት  እየደገመ ይኸው ዘመናትን ተሻገርን ።አላማው ማንን ለመጥቀምና  ማንን ለመጉዳት እንደሆነ በፍፁም አይታውቅም።

ephrem

የሐገር ቤቱን አስተዳደር የሚከሱት  በጎጠኝነት ሆኖ እያለ እነሱ ግን ስሙን ብቻ ሳይሆን ልብሱንም ጭምር ጎጥ አድርገውታል።ቤተክርስቲያን አንድት ናት ።አስተዳደርም አንድ ነው ።አባቶች ግን ብዙ ናቸው ።በአባቶች ቁጥር ልክ ግን ሲኖዶስ  መኖር አለበት የሚል ስርዓትም ህግም የለም ።ከዚህ በፊት የተለያዩ እህት አባያተ ክርስቲያናት   በአንድም በሌላም መልኩ ችግር አጋጥሞአቸው ያቃሉ።ተሰደውም ኖረዋል ።ግን ሲኖዶስ ተሰደደ አላሉም ።ይህ ሁሉ ሆኖ ሐገራችን ኢትዮጲያ ከ80 በላይ ብሔረሰቦችን የያየዘች ሀገር ከመሆኗም በላይ አሁን ባለው መንግስት ጉዳት የደረሰበት ሰው ጎነደር ብቻ አደለም ።የጥቃቱ ሰላባ የትግራይ ወንድሞቻችንም ጭምር እንጂ።ስለ ክርስትናው ካነሳን ግን መስመሩ ሁሉ የመከራ መሆኑ የማይካድ ነው ።”የሚወደኝ ቢኖር እራሱን ይካድ መስቀሌን ተሸክሞ ይከተለኝ ብሏል እና ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ  ማንም ቢሆን በማመኑ ለሚመጣበት መከራ መፍራት እንደሌለበት ኣስቀድሞ ተሰብኮልናል ።እንግዲህ በዚህ ሁሉ ወስጥ እጅግ ብዙ አብያተ ቤተክርስቲያናትና  ክርስቲያኖች በተለያየ ምክንያት በብዙ ችግር ውስጥ ተቀምጠው  የመሰባሰብና አንድ ሆኖ እነዚህን ችግሮች  ለመቀነስ ከመታግል ጀምሮ ስጋዊ ፍላጎትን ለማርካት ጎንደር ተሰብስብ እያሉ እርስ በእርስ መሿሿም ምን የሚሉት ነው ?።በውኑ የጎንደር መለኩሴ ክንፍ አለው ወይስ መንግስተ ሰማያትም  በጎነደሬነት ብቻ ነው የሚገባው?

አርግጥ እንደዛ ከሆነ ሌሎቻችን  አለቀልን።ምን አይነት ሞራል ነው ?ምን አይነት ክርስትና ነው ?ትምህረቱስ ከየት መጣ ? ይህን አለም አንፈልግም ብለው sign out  አደርገው ከወጡ በኋላ ለዚህ አለም ስልጣንና ምኞት መሽቀዳደም  እነማን ነበሩ ያሰኛል።ደግሞስ ከመንፈቅዱስ ያልሆነ ሹመት ሽልማት በውኑ መንገዱ አስከየት  ነው? ።የተሹሙት ሰዎች ብቃታቸው እና ትምህርታቸው የተለካው በፖለቲካ መስፈሪያ  ነው? ወይስ በመንፈሳዊ ትምርታቸው ?እነ አባ ወልደ ትንሣኤ  ማናቸው? እስቲ ከዚህ ሁሉ ጥያቄ በኋላ የሹመቱ ቃለ ማህላ ላይ ለምን ተዋህዶ የሚለው ቃል ተዘለለ? የ ኢ/ኦ/ተ/ የሚለው ቃል ስለከበደ ወይስ ስለተዘነጋ? ይህን በራሱ ለእነሱ እንተወውና  አስቲ የከዚ በፊት ሹመኞቹን አስበን  የዛሬዎችን እንመልከት ።

1. የአባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ       ትውልድ ሃገር   ጎንደሬ እና  በተለያየ ትምህርታቸው አፀፅ ያለባቸው

2.  አባ ጽጌ ድንግል ደገፋው          ትውልድ  ሃገር ጎንደር 

3. የአባ ገብረ ሥላሴ ጥበቡ             ትውልድ ሃገር  ጎንደር

4.  የመልአከ ሰላም አባ ሳሙኤል ዳኘው   ትውልድ ሃገር ጎንደር

5.  መልአከ ሰላም አባ ሳሙኤል         ትውልድ ሃገር ጎንደር

6.  የመልአከ ብርሃናት አባ ገብረ ሥላሴ የኋላሸት    ትወልድ ሃገር ጎንደር

የህይወት ታሪካቸው  ላይ ሁሉንም ጎንደር ለማለት ፈርተው ይመስላል  በቅድስት ሃገር ኢትዮጲያ ተወለዱ። ብቻ ብለው ዝቅ ብላችሁ     የአንደኛ ደረጃትምህርታቸውን  የተማሩበት ቦታ ላይ ጎንደር እንደሆነ ተጠቅሶአል።በርግጥ እንኳን እኛ  እናንተም በስራችሁ  እንዳፈራችሁ በትልቁ ማሳያ ነው ። ነግር ግን መፅሃፍ ቅዱሳችን   በትንቢተ ኢሳያስ ምራፍ 30 ቁ15-18  እንዲህ ይላል፦ 

“የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፤ እናንተም እንቢ አላችሁ፥

ነገር ግን፦ በፈረስ ላይ ተቀምጠን እንሸሻለን እንጂ እንዲህ አይሆንም አላችሁ፥ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ደግሞም፦ በፈጣን ፈረስ ላይ እንቀመጣለን አላችሁ፥ ስለዚህም የሚያሳድዱአችሁ ፈጣኖች ይሆናሉ።  

ከአንድ ሰው ዛቻ የተነሣ ሺህ ሰዎች ይሸሻሉ፤ እናንተም በተራራ ራስ ላይ እንዳለ ምሰሶ፥ በኮረብታም ላይ እንዳለ ምልክት ሆናችሁ እስክትቀሩ ድረስ፥ ከአምስት ሰዎች ዛቻ የተነሣ ትሸሻላችሁ። 

እግዚአብሔርም የፍርድ አምላክ ነውና ስለዚህ እግዚአብሔር ይራራላችሁ ዘንድ ይታገሣል፥ ይምራችሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው። ውድ አባቶቻችን  ታዲያ በውኑ እንተ ቃሉ ተስቶአችሁ ወየስ ተረስቶአችሁ  ለሹመት ለሽልማት መጓጓታችሁ?ውይስ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል  እንዳለችው በቅሎ መሆኑ ነው ።በዚህ አጋጣሚ ይቀርታ የምላችሁ እናንተን አከብራለሁ ስለደፈርኩአችሁም አደለም ከላይ ያለውን ሃሳብ ለመስጠት የተነሳሁት ።አንድም ዘረኝነትና ጎጠኝነታችሁ ከወያኔ የባሰ በመሆኑ አንድም  ትህትና ያልተከለበት ክወረስናትና የቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምሮ ስላልሆነ ነው ።በፖለተካና በፖለተከኞች አፍ ህጋዊ ናችሁ። መንግስቱ ሐይለማርያምም  ህጋዊው ፕሬዘዳንት ነው። ምክንያቱም  እሱም ተገዶ ነው ከስልጣኑ የወረደውና ። ግን እናንተ ጋ ሲሆን ህጋዊ ትባላችሁ እርሱ ጋር ሲሆን የቀድሞ ይባላል።ለምን  ጎንደሬ ስላልሆነ ወይስ  ሐራሬ ያለ ሰው ህጋዊ አይደለም  ?።ይህንና ይህን  የመሳሰለው  ጥፋታችሁ የቅድስት ቤተክርስቲያንን  አንገት ያስደፋ ቢሆንም  ህዝበ ክርስቲያኑ ግን ቆም ብሎ የሚያስብበት  እና “አውነት ምንድነው ?” ብሎ የሚጠይቅበት  ግዜ ነው ።እግዚያብሔር ይታገሳል እንጂ አይቆጣም  አልተባለም ።አቡነ ጳውሎስንና  መለስ ዜናዊን  ያያ  በኢሳት አይጫወትም።ክብርአችሁ አምነታችሁ ና ትህትናችሁ ሆኖ ለትውልድ  መተላለፍ ሲኖርበት ማን አለበኝነታችሁንና ትውሉዱን  አሰፍስፎ ለሚጠብቀው ተሃድሶ መናፍቃን ለማስበላት  የምታደርጉት  እሩጫ  በእግዚያብሔር  ዘንድ ሳያስጠይቃችሁ የሚቀር አይመስለኝ ም።

በስተመጨረሻም:

እግዚያብሔር  በነብዩ በ ኢሳያስ  አንደበት  እንዲህ  ብሎ ተናግሮአልና “ከቃሌ የተነሣ ወደ ሚፈራ የዋህ ትሑትና ትግስተኛ  ወደሚሆን  ነው  እንጂ ወደ ማን  እመለከታለሁ?” ዳግመኛም ወንጌል  እንዲህ  ይላል “የዋሆች  ብፁዓን  ናቸው  እነርሱም ምድርን ይወርሳሉና “ዲድስቅልያ  አንቀፅ ፮ አና፯። በዚህ  ሁሉ ምሃል ለስልጣን የሚጓጉና  ጎጠኞች አላለምና አስቡበት ።

ችር እንሰንብት

Advertisements