ሰይፉ ፋንታሁን ሰኔ 30ጀምሮ ከሸገር ሬዲዮ ጣቢያው ሊያሰናብት መሆኑን ታማኝ ምንጮች ተናገሩ፡፡


Fantahun-Seifu-and-Mahder-Assefa

በዚህ ሳምንት መነጋገሪያ ሆኖ የቆየው ሰይፉ ፋንታሁን ከሸገር ሬዲዮ ከሰኔ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ሰይፉ ፋንታሁንን ከጣቢያው ሊያሰናብት መሆኑን ታማኝ ምንጮች ተናገሩ፡፡

ለአንድ ቀን ፖሊስ ጣቢያ አድሮ በነጋታው በ50 ሺህ ብር ዋስ የተፈታውና በስም ማጥፋት ተከሶ የነበረው ሰይፉ እንደ ዘ-ሐበሻ ምንጮቹ ከሆነ በሸገር ኤፍ ኤም ላይ የሚያቀርበውን ታዲያስ አዲስ ፕሮግራሙን አቁሞ ከጣቢያው የሚሰናበተው አዲስ ሬዲዮ ጣቢያ ከእነሰራዊት ፍቅሬ ጋር በመክፈቱ ነው፡፡

‹‹ዋን ላቭ›› የሚል መጠሪያ ያለውን አዲሱን ሬዲዮ ጣቢያ የምትመራው አርቲስት ማህደር አሰፋ ስትሆን ለጣቢያው የሚያስፈልገውን ወጪ የሸፈኑት ደግሞ ሼህ አልአሙዲ ናቸው፡፡ ዋን ላቭ ሬዲዮ ስራ የሚጀምረው በመጪው መስከረም ወር ነው ተብሏል::

ማኅደር አሰፋ በአሜሪካ ቆይታ አድርጋ ወደ ሃገር ቤት መመለሷ አይዘነጋም::

Advertisements