ኤርትራ “200 የኢትዮጵያ ወታደሮችን ገድዬ 300 አቆስለኩ” አለች(BBC)


eritrean-troopsየኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴርን ገልጾ እንደዘገበው ኤርትራ በ2 ቀን ጦርነት 200 የኢትዮጵያ ወታደሮችን ገድላ 300 ማቁሰሏን አስታወቀች::

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ባለፈው እሁድ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት በጾረና በኩል ጥቃት ፈጸመብኝ ማለቱ ይታወሳል::

እንደሚኒስትሩ መግለጫ እሁድ እና ሰኞ ዕለት በተደረገው ጦርነት 200 ሰዎችን መግደሉን ይገልጽ እንጂ ከራሱ በኩል የተጎዱ ወይ የሞቱ ወታደሮች እንዳሉ የገለጸው ነገር የለም::

የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ለኤርትራ መንግስት እስካሁን ለፈጸመው ትንኮሳ ተመጣጣኙን እርምጃ ሰጥተነዋል:: ወደፊትም እንደ ኤርትራ መንግስት እንቅስቃሴ ጦራችንን እናንቀሳቅሳለን ማለቱን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::

የመንግስት ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ በዚህ ሳምንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫም ከኤርትራ ጋር ወደለየለት ጦርነት መግባት የኢትዮጵያ ምርጫ አይደለም ማለታቸው ይታወሳል::

ኢትዮጵያና ኤርትራ ከ1998 – 2000 ዓ.ም ድረስ ባደርጉት የድንበር ግጭት ከ100 ሺህ ሰዎች በላይ ህይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ የታሪክ መዛግብት ይመሰክራሉ::

Advertisements

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s