ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተመረጡ ተጫዋቾች አብዛኞቹ የዕድሜ ምርመራን ሳያልፉ ቀሩ


stadium

ከቀናት በኋላ የኢትዮጵያ ወጣት(ከ17 ዓመት በታች) ብሄራዊ ቡድን በግብፅ ካይሮ ኦገስት 5 ለሚያደርገው ጨዋታ ልምምድ ይጀምራል፡፡

ለዚህ ጨዋታ እንዲረዳ ከሰሞኑ በጳውሎስ ሆስፒታል ተጨዋቾቹ ላይ የኤም አር አይ ወይንም እድሜን የማጣራት ምርመራ ተከናውኖ ነበር፡፡ በ3 ቡድን ተከፍለው ወደሆስፒታሉ የተጓዙት ተጨዋቾች ውጤት ይህን ይመስላል።
በመጀመሪያው ቡድን 40 ተጨዋቾች ተመርምረው 2ቱ ብቻ ምርመራውን ሲያልፉ በሁለተኛው ቡድን ከ19 ተጨዋቾች ውስጥ 7ቱ ማለፍ ችለዋል፡፡ በሶስተኛው ቡድን ደግሞ ከ35 ተጨዋቾች ያለፉት 15ቱ ሆነው ተገኝተዋል፡፡
እነዚህን ተጨዋቾች ከመጡበት ቦታ ወይም ክለብ አንፃር ብንመለከት፡-
አዳማ ከ4/0፣
ወላይታ ዲቻ ከ5/1፣
ሀዋሳ ከ8/0፣
ሲዳማ ከ6/1
ቅ/ጊዮርጊስ ከ6/1፣
ደደቢት ከ9/2፣
ንግድ ባንክ ከ9/2፣
ኢትዮጲያ ቡና ከ11/2፣
ኤሌክትሪክ ከ9/3 ተጨዋቾች ያለፉ ሲሆን ተስፋ ከተጣለበተው አምቦ ጎል ፕሮጀክት 8 ተጨዋቾች ተመርምረው ምንም ማለፍ የቻለ ተጨዋቾች የለም፡፡ ከብሄራዊ አካዳሚ ደግሞ ከ10 በላይ ተጨዋቾች መጥተው ያለፈው 1 ብቻ ነው። በአጠቃላይ በ94 ተጨዋቾች ላይ እድሜ የማጣራት ምርመራ ተከናውኖ በትክክል እድሜያቸው ከ17 በታች ሆኖ የተገኙት 24 ብቻ ናቸው ማለት ነው፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s