ሂዩማን ራይት ዎች በኢትዮጵያ ላይ ጠንከር ያለ መግለጫ አወጣ።


imagesይህ ባለ 61 ገጽ ሪፖርት “‘እንዲህ ያለ ግፍና ጭካኔ’ – ግድያና እስራት፤ የኦሮሞ ብሄረሰብ ተወላጅ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ባካሄዱት ሰላማዊ ተቃውሞ በጸጥታ ሀይሎች የተሰጠ ምላሽ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ” የተሰኘ ሪፖርት የኢትዮጵያ መንግስት ተቃውሞሙን ለመቆጣጠር የተጠቀመውን ከመጠን ያለፈ ሀይልና አላስፈላጊ ግድያ፣ የጅምላ እስር፣ ጭካኔ የተሞላበት የእስር ቤት አያያዝ፣ እንዲሁም የተቃውሞ ሂደቶችን በተመለከተ መረጃዎች ለህዝብ እንዳይሰራጩ ማፈንን አጠቃሎ በዝርዝር የሚያትት ነው።

“የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ሰብአዊነት በጎደለው ሁኔታ የተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ በቀጥታ በመተኮስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን፣ ገበሬዎችን እና ሌሎች የሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎችን ገድለዋል።” በማለት የሂይውማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ዳይሬክተር የሆኑት ሌስሊ ሌፍኮው ተናግረዋል። ሌፍኮው አያይዘውም “መንግስት ያለ አግባብ የታሰሩትን በአስቸኳይ እንዲፈታ፣ ለገለልተኛ እና ተአማኒነት ላለው አጣሪ ቡድን አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ፣ እንዲሁም ይህን የጭካኔ እርምጃ የወሰዱት የጸጥታ ሀይሉን አባላት ላደረሱት የመብት ጥሰት ተጠያቂ እንዲያደርግ” ሲሉ ጠይቀዋል።
የሪፖርቱን ጭብጥ ከዚህ ማስፈንጠሪያ ውስጥ ያገኙታል።

Advertisements

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s