የትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን የመጨረሻዉሲሸሽገዉ የነበረዉን ጦርነት ሳይወደዉ በግዱ እየተጋፈጠዉ ይገኛል!


Ethiopia-armyኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን ለሁለት አስርት አመታት በቀኝ ግዝት ይዞ የቆየዉ ይህዉ የወያኔ ቡድን በተለያየ የሐገሪቷ ክፍሎች ከገባበት የጦር አጣብቂኝ ዉጥረት የተነሳ ሲሸሸዉና ሲሸሽገዉ የነበረዉን ጦርነት ሳይወደዉ በግዱ እየተጋፈጠዉ ይገኛል።
በሰሜናዊ የሐገራችን ክፍል በጾረና አካባቢም የወያኔ ቡድን ያደረገዉ ትንኮሳ መክሸፉን ምንጮች የጠቆሙ ሲሆን፡ የኢትዮጵያና የኤርትራ ድንበር ጋሽ ባርካ እና ላ ኢላይ ጋሽ አዋሳኝ ስፍራዎች ላይ ጦርነት ተቀስቅሷል!
በዚህ ጦርነት ወያኔ ከፍተኛ አደጋ እንደደረሰበት የተረጋገጠ ሲሆን የ 25ኛ ክፍለ ጦር የደጀን ጦርን ለማጠናከር በሚል ወደ አዉድማዉ ተጠግቷል።
በጦርነቱ የደረሰዉ የጉዳት መጠን ያልተረጋገጠ ከመሆኑ ባሻገር ከትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን መከላከያ ዘመቻ ስምሪት መምሪያ አካሎች የተገኘዉ መረጃ እንደሚጠቁመዉ በወያኔ በኩል የተሞከረዉ ትንኮሳ በተዘዋዋሪ መንገድ በኤርትራ ከሚገኙ የነጻነት ሐይሎች ጋር እንደሆነ የሚያሳይ ሲሆን ድንበር ዘለልነቱ የኤርትራ ወታደሮችንም ተሳታፊ እንዳደረጋቸዉ እንዲሁም እንደሚያደርጋቸዉ በጉልህ ያሳየ ነዉ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Advertisements