ሰበር ዜና — ወደ ኤርትራ ለመዝለቅ የሞከሩ የህወሃት ወታደራዊ ደህንነት ሰላዮች ተረሸኑ


በልኡል አለም

በኤርትራ እና በዙሪያዋ ለስለላ ስራ እንዲሁም ለቅኝት የዉጊያ ስምሪት እንዲጠቅሙ ተብለዉ የተሰማሩ የህወሃት ወታደራዊ መረጃ አባላቶች እየታደኑ መታፈናቸዉን የሚያረጋግጡ መረጃዎች አፈትልከዉ ወጥተዋል።Patriotic Ginbot7 Conference

በተልይም ሞላ አስገዶም ከኤርትራ ወደ ህዉሃት ከፈረጠጠ ወዲህ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ ነጻነት ሐይሎች የደህንነት ክትትል ምክንያት በህወሃት መረጃ ሰንሰለት ስር የነበሩ ሰላዮች በሙሉ መረሸናቸዉን የወያኔ ወታደራዊ ደህንነት በማረጋገጥ ለመከላከያ ሚኒስቴሩ እና ለሚመለከታቸዉ የደህንነት ክንፎች አሳዉቋል።

ወታደራዊ ደህንነቱ ሌሎች በተለያየ ምክንያት ወደ ኤርትራ ሰርገዉ እንዲገቡ የተደረጉ የስለላ ሰዎች በተለይም የአርበኞች ግንቦት ሰባትን አጠቃላይ ፖለቲካዊና መሰረታዊ የአደረጃጀት እርከን፣ እንዲሁም ወታደራዊ ኮርሶችና ዲስፕሊኖችን፣ ስልታዊ መዋቅርንና አቀማመጥን ለመሰለል እንዲረዱ ከተሰማሩ ግለሰቦች ዉስጥ አንዳቸዉም የት እንደገቡ ለማወቅ ያለመቻሉን ምንጮቻችን ጠቅስዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወደ ዉጊያዉ አምድ ከተቀላቀሉ ወዲህ ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ በፍጥነት እየአሰገሰ በመምጣት ላይ የሚገኘዉን የለወጥ ነዉጥ መቛቋም የተሳነዉ የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን ወታደራዊ ደህንነት የአርበኞች ግንቦት7ን እና የጥምር ሐይሎችን እንቅስቃሴ ማወቅ እንኳ እንደተሳነዉ በወታደራዊ የደህንነት ስልትም መበለጡን በተለይም የተሳሳቱ መረጃዎች እየደረሱት ላም ባልዋለበት… ሲቅበዘበዝ የነጻነት ሐይሎቹ ሽምቅ ዉጊያ ሰለባ እየሆነ መምጣቱን ለተደራቢ አዛዡ ሌተናንት ጄኔራል ዮሃንስ ገብረመስቀል ውይይት እንዲደረግበት ከቀረበው አጀንዳ ለመረዳት ተችሏል።

ስርአቱ አሁን ባጋጠመዉ የመረጃ መዳፈን ምክንያት ስጋት ላይ ስለወደቀ ድንገተኛና የተጠናከረ ተመላላሽ ጥቃት እንዲሰነዘር እንዲሁም በጎንደር ዙሪያ የሚገኘዉ የመከላከያ ሰራዊት በእጅጉ እንዲጠናከር ለማድረግ ከሸዋሮቢት የመጡ አዲስ ወታደሮች ወደ ክፍለ ጦሮቹ እንዲካተቱ እና አጥቂዉ የግንባር ሐይል ለመመሪያ ዝግጁ እንዲሆን በአመራሮች ቢወሰንም ከተራ ወታደር አንስቶ እስከ ከፍተኛ አመራሮች መመሪያ ለመቀበል ስጋት ላይ ናቸዉ።

ይህን መረጃ አያይዘዉ የላኩልን ምንጮች በኤርትራ የሚገኙ የነጻነት ሐይሎች ከምንዜዉም በበለጠ በንቃትና በመጠናከር እየወደቀ የሚገኘዉን ባለ ሁለት እግር ዝሆን ለመጣል እንዲዘጋጁ መዘናጋትን ፈጽመዉ እንዳያስቡት አስጠንቅቀዋል።

ከአራት እግሮቹ ሁለት የፊት እግሮቹን የቆሰለ ዝሆን ለመጣል ዝሆን መሆን አያስፈልግም።
patriotic-ginbot7-conference2

Advertisements