የፌደራል ፖሊስ ኢንስፔክተር ተስፉ በርካታ አባላቱን ይዞ ስርዓቱን ከዳ


inspecterየኢሕ አዴግ አስተዳደር ኢንስፔክተር ተስፉ የተሰኘ የፌደራል ፖሊስ ጦር መሪ በርካታ አባላትን ከነሙሉ ትጥቃቸው ይዞ ከሁመራ ስርዓቱን መክዳቱን የአርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ ዘገበ::
እንደራድዮው ዘገባ ኢንስፔክተር ተስፉ ሁመራ እና አካባቢው የሚንቀሳቀሰው ፌደራል ፖሊስ መሪ፣ ለህወሓት ታማኝ እና ጠንካራ ከሚባሉት ቀዳሚው የነበረ ሲሆን በትናንትናው ዕለት የካቲት 19 2008 ዓ.ም የሚመራቸውን በርካታ አባላት ከነሙሉ ትጠቃቸው ይዞ ሁመራ ከሚገኝ ጦር ግንባር ጠፍቷል፡፡
በራድዮው ዘገባ መሠረት የኢንስፔክተር ተስፉን እና በርካታ ተከታዮቹ የሆኑ የፌደራል ፖሊስ አባላትን መጥፋት ተከትሎ ህወሓት ጎዳናዎችን በጦር ዘግቶ ወጥሯል፤ ከፍተኛ አሰሳም እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ኢንስፔክተር ተስፉና ተከታዮቹ እስካሁን የገቡበት አልታወቀም፡፡ አገዛዙ እነ ኢንስፔክተር ተስፉ ወደ ኤርትራ ተሻግረው ብረት ያነሱ የነፃነት ድርጅቶችን እንደተቀላቀሉ ያምናል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ ከኢንስፔክተሩ ጋር የከዱት ወታደሮች ቁጥር ምን ያህል እንደሆኑ ባይገልጽም በርካታ ሲል ይጠራቸዋል::

Advertisements