ሰሞኑን ሊካሄድ ታስቦየነበረው የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ተሰረዘ!


teddyafro1
ቅዳሜ የካቲት 26 ቀን እንዲካሄድ ዕቅድ ተይዞለት የነበረው የድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ኮንሰርት፣ እስካለፈው ዓርብ ድረስ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዕውቅና አላገኘም፡፡
ኮንሰርቱን ያዘጋጀው ሐበሻ ዊክሊ ፕሮሞሽን ድርጅት ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከተው የከንቲባው ጽሕፈት ቤት ምላሽ ባለማግኘቱ፣ ቅሬታውን ለመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ቢያቀርብም፣ ምላሽ ግን አለማግኘቱን አስታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ሥር የሚገኘው የሰላማዊና ሕዝባዊ ስብሰባዎች ፈቃድ ክፍል፣ ኮንሰርቱን ለማካሄድ ለቀረበለት ጥያቄ ግልጽ ምላሽ ባይሰጥም፣ ኮንሰርቱ እንዳይካሄድ መከልከሉን ግን የሪፓርተር ጋዜጣ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡
ቴዲ አፍሮ በሀገር ውስጥ ሊያደርጋቸው የነበሩት ኮንሰርቶች በተለያየ ምክንያት ሲሰረዝ አሁን ለሶስተኛ ጊዜ ነው።
ምንጭ፡-ሪፓርተር

Advertisements