ካፍ የስድስት ኢትዮጵያውያን አሰልጣኞች የኢንስትራክተርነት ደረጃ አፀደቀ


የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን /ካፍ/ የስድስት ኢትዮጵያውያን አሰልጣኞችን የኢንስትራክተርነት ደረጃ ማፅደቁን አስታወቀ። አብርሃም መብራህቱ፣ አብርሃም ተክለሀይማኖት፣ ሰውነት ቢሻው፣ አንተነህ እሸቴ፣ መኮንን ኩሩና ዶክተር ጌታቸው አበበ በአዲሱ የካፍ ኢንስትራክተሮች አፀዳቂ አካል የኢንስትራክተርነት ማዕረግ የፀደቀላቸው አሰልጣኞች ናቸው። የኢንስትራክተርነት ደረጃው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2016 እስከ 2018 ድረስ እንደሚቆይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የላከው መረጃ ያመለክታል። ሌሎች በፌዴሬሽኑ ስር የሚገኙ ኢንስትራክተሮች በፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ዳይሬክተር ኃላፊነት አማካኝነት የትምህርትና ስልጠና ዝግጅታቸው እየተገመገመ በአገር ውስጥ እውቅና እንደሚሰጣቸውም ገልጿል። –12313630_694725944001115_1407293853555234612_n

Advertisements