የሽንት ትቦ ኢንፌክሽን ምንድነው???


ከዶክተር አለ! 8809

የሽንት ትቦ ኢንፌክሽን ምንድነው???

-የሽንት ትቦ ኢንፌክሽን የምንለው እንደ ኩላሊት፤የሽንት ፊኛ እና የሽንት ትቦ ያሉት ሽንትን ለማስወገድ የምንጠቀምባቸ አካላት በተለያዩ ምክንያቶች በባክቴርያ ሲጠቁ ነው፡፡

ምልክቶቹ

-ሽንት በሚሸናበት ወቅት ማቃጠል
-ከእንብርት በታች ህመም
-የጎን እና ጎን ህመም
-የሽንት ከለር ወደ ቀይነት እና ደመናማነት መቀየር
-መጥፎ ጠረን ያለው ሽንት
-የሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት ስሜት
-ወደ መፀዳጃ ቤት ሲሄዱ ትንሽ መጠን ያለው ሽንት መውጣት
-ትኩሳት
-ማቅለሽለሽ
-ማስመለስ

ተጋላጭ የሆኑት እነ ማን ናቸው???

-በሰው ሰራሽ የሽንት ትቦ ሚጠቀሙ ወይም ከዚ በፊት የተጠቀሙ
-የኩላሊት ጠጠር ያለባቸው
-በሽታን የመከላከል አቅምን የሚቀንሱ በሽታዎች ለምሳሌ፡የስኳር በሽታ፤ኤች.አይ.ቪ
-እርጉዝ ሴቶች
-በመሀፀን ሚቀበር የወሊድ መቆጣጠርያ ሚጠቀሙ
-ያልተገረዙ ወንዶች

እንዴት መከላከል እንችላለን

-ሽንት በሚሸናበት ወቅት ሙሉ በሙሉ ወቶ እስኪያልቅ መጠበቅ
-ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ ቶሎ ወደ መጸዳጃ ቤት መሄድ እና መታጠብ
-በምንጸዳዳበት ወቅት ከፊት ወደ ኋላ ማጽዳት
-በቀን ውስጥ 1.5 እስከ 2 ሊትር ውሃ መጠጣት
-አትክልትና ፍራፍሬ በደንብ መመገብ

የሚደረገው ህክምና

-ለላብራቶሪ ሽንት በመስጠት በሽታ አምጪ ተዋሲያኑ ይለያል በባክቴርያ ለመጣ ኢንፌክሽንም በጸረ ባክቴርያ በቀላሉ መታከም እና መዳን ይችላል
-ከመድሀኒት በተጨማሪም ውሀ እስከ 2 ሊትር ድረስ በየቀኑ መጠጣት
– እስኪሻሎት የሽንት ትቦ መቆጣትን የሚያባብሱ ነገሮችን ድረስ ማስወገድ ለምሳሌ፡ አልኮል፤ቡና፤ጣፋጭ መጠጦች

ለተጨማሪ መረጃ 8809ዶክተር አለ ይደውሉ!!!
076

Advertisements