አምቦ ከተማዋ በጥይት ድምጽ ተወጥራለች


amboበአምቦ ከፍተኛው ተቃውሞ በቀጠለበት በዚህ ወቅት በከተማዋ የሚገኘው እስር ቤት በ እሳት እየነደደ መሆኑን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::
በተለምዶው ቀበሌ 06 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ይኸው የፖለቲካ እስረኞች ማሰቃያ እስር ቤት ውስጥ ከኦሮሞ ሕዝብ ንቅናቄ ጋር በተያያዘ የታሰሩ በርካታ ወገኖች እንደደሚገኙበት ምንጮች አስታወቀዋል::
በአምቦ ከተማ በአሁኑ ወቅት የጥይት እሩምታ እየተሰማ ሲሆን ከዚህ እስር ቤት እስረኞች ያምልጡ አያምልጡ ዘ-ሐበሻ እያጣራች ትገኛለች:: ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስም በ እስረኞች ላይ ከባድ ጉዳት ስለመድረሱ የታወቀ ነገር የለም:: ሆኖም ግን እሳቱ እየተዛመተ ባለበት ወቅት እንኳ እስረኞቹ እሳት እንዳያጠቃቸው ከቦታ ቦታ ለማዘዋወር ከበላይ ት ዕዛዝ ካልመጣ በስተቀር የአካባቢው ፖሊሶች ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ይነገራል::

Advertisements