ፈረንሳዊ ባለሃብት በፓሪስ የሚገኙ የባንክ ሰራተኞች ወደ ምግብ ሬስቶራንት ቦታዎች ድርሽ እንዳይሉ አዘዘ ፤ ለምን?


532aefef94f15ff0e61485337616b81b_XL
በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ጎርሜት የተባለ ምግብ ቤት ባለቤት ነው አሌክሳንደር ካሌት።

ምግብ ቤቱ ከተራው የአካባቢው ሰው ጀምሮ በበርካታ የፊልም ተዋናዮች ጭምር የሚጎበኝ ነው።

ካሌት ከሰሞኑ በምግብ ቤቱ በራፍ ላይ በለጠፈው ማስታወቂያ የባንክ ሰራተኞች ወደ ምግብ ቤቱ እንዳይገቡ አግዷል።

ነገር ግን 70 ሺህ ፓውንድ የመግቢያ ክፍያ ከፈፀሙ በምግብ ቤቱ መስተናገድ እንደሚችሉ በማስጠንቀቂያ ፅሁፉ ላይ ሰፍሯል።

ካሌት በዚህ ታዋቂ ምግብ ቤቱ የባንክ ሰራተኞች እንዳይገቡ እገዳ የጣለው ከተለያዩ ባንኮች ብድር ጠይቆ ስላልተፈቀደለት መሆኑን ነው የገለፀው።

አፃፋ በመመለስ አምናለሁ የሚለው ወጣቱ፥ ብድር እንደከለከሉኝ እነሱም ወደ ምግብ ቤቴ እንዳይገቡ አግጃለሁ ብሏል።

“የማውቀውን የባንክ ሰራተኛ ከተመለከትኩት ወደ ምግብ ቤቴ እንዲገባ አልፈቅድለትም፤ ከገባም አስወጣዋለሁ” ሲልም በባንክ ሰራተኞች መማረሩን ይናገራል።

ካሌት ምግብ ቤቱን ለማስፋፋት በሚል ከባለፈው አመት ገቢው አንፃር አነስተኛ የሆነ 70 ሺህ ዩሮ ብድር የጠየቃቸው ባንኮች ፈቃደኛ አለመሆን እጅግ ቅር አሰኝቶታል።

ከሰባት አመት በፊት የአሁኑን ምግብ ቤቱን ከባንክ ገንዘብ ተበድሮ ከመክፈቱ በፊትም 20 ጊዜ ብድር ጠይቆ አልተሳካለትም ነበር።

በቀልን የመረጠው ካሌት አሁንስ ባንኮች የከለከሉትን ብድር ለማግኘት ጥያቄውን ይቀጥል ይሆን? ወይንስ የባንክ ሰራተኞችን ወደ ምግብ ቤቱ እንዳይገቡ በመከልከል ቂሙን በመወጣት ብቻ ይገፋበታል? የሚለው ወደፊት የሚታይ ጉዳይ ነው።

ካሌት በመዲናዋ ፓሪስ ከሚገኙ የባንክ ሰራተኞች ምን ያህሉን እንደሚያውቅም አልተገለፀም።

ምንጭ፦ http://www.mirror.co.uk/

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s