ተገኔ እና ሙክታር


12729165_1079208205434419_3660117773553303643_n“መጥፎ ሰላም” ወይም “ጥሩ ጦርነት” የማለት ያህል “አብዮታዊ ዴሞከራሲ” የሚባል እርስበርሱ የሚጋጭ “ሃይማኖት” ጀማሪ የሆኑትን ጨምሮ አዳዲስ ጨቅላዎችንም ሳይቀር በድጋሚ እያጠመቁ ደቀመዛሙርት ያደረጉት ተገኔ ጌታነህ “በህመም” ከአጥማቂነት ሥልጣናቸው ተነስተዋል፡፡ (በፈቃዳቸው ለቅቀዋል) በከፍተኛ ሙስና እና ሌሎች ኢ-ልማታዊ በሆኑ አሠራሮች ችግር ውስጥ የገባው መ/ቤታቸው “የልማታዊ ፍትህ ጸር” የሆኑ ሦስት ዳኞችን ካጣ በኋላ የተገኔ ሕመምም ከቀድሞው ይልቅ በርትቶ ሥልጣን አስለቅቋቸዋል፡፡
የህወሃት አሽቃባጮች “ከታመሙ ቆይተዋል” በማለት የተገኔ መባረር ፖለቲካዊ ይዘት የለውም ለማለት ቢሞክሩም እስካሁን “ይሻለኝ ይሆን” እያሉ በተስፋ በሥልጣን ስለመቆየታቸው የተናገሩት የለም፡፡
ህወሃት/ኢህአዴግ ተራማጅ ነው፤ “በሽተኛ” አይፈልግም፡፡
“ዶ/ር” ሙክታር ከዲርም ሰሞኑን “በሽታቸው” ጨምሯል፡፡ በአስተዳደርና በሌሎች ለራሳቸውም ግልጽ ያልሆኑ “ችሎታዎች” የዶክተርነት የክብር “ዲግሪ” የተሰጣቸው ሙክታር “አመመኝ” ብለው ሰሞኑን ጠፍተው ነበር፡፡ ተሸሏቸው ይምጡ በዚያው አሟቸው ይቀጥል የታወቀ ነገር የለም፡፡ አፍቃሪ ህወሃቶች አሁንም “ሙክታር ታሞ ነበር፤ አሁን ወደ ሥራ ሊመለስ ነው” እያሉ ነው፡፡ ሙክታር ግን “እንባ እንባ ይለኛል፤ ይተናነቀኛል” እያሉ እንደሆነና ይሰማል፡፡ (ጎልጉል)

Advertisements