የሃይሌ ገብረስላሴ ንግግር እጅግ የሚያበሳጭ ነው።


Gebrselassie-HailePC1-Nijemegen11 ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለጠቅላላው የአፍሪካ ህዝብ እንደ ስድብ የሚቆጠር ነው ። አትሌቱ ታዋቂ ሯጭ ፣ ባለሃብት አ ንጅ ስለደሞክረሲ ብዙ የሚያውቀው ነገር የለም ወይም እያበደ ነው ። በነገራችን ላይ ሃይሌ ቢቢሲ ላይ የተናገረው ” ብላሽ ” ንግግር የአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ” ምሁራን ” ተብዬዎችም አመለካከት ነው ።
መለስ ዜናዊም በአንድ ወቅት ” ወርልድ ኢኮኖሚክ ፎረም ” መድረክ ላይ ” ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ከደሞክረሲ በፊት ልማት ነው ። ” ሲል ነበር ።
በኋላ ፈረንጆቹ በሙግት ወጥረው ሲይዙት ” ደሞክረሲም ልማትም የህልውናችን ጉዳይ ነው ማለት ጀመረ ። ይሄን ለይስሙላ ቢለውም ገዥው መንግስት የሚመራበት ” ልማታዊ መንግስት ” (Developmental state) ርእዮት ለደሞክረሲ ደንታ የሌለው ርእዮት እንደሆነ ይታወቃል ።

ጥቅምት ወር ይመስለኛል “Vision Ethiopia ” የሚባል የሲቪክ ማህበር ዋሺንግተን ድሲ ውስጥ ብዙ ጥናታዊ ፅሁፎች የቀረቡበት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር ። ፕሮግራሙ በኢሳት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ለመላው አለም ተሰራጭቷል ። በመድረኩ ብዙ የፖለቲካ ተንታኞች ተጋብዘው ነበር ለመጥቀስ ያክል አምባሳዴር ህርማን ኮህን ፣ አምባሳደር ዴቪዲ ሺን ፣ ፕሮፌሰር መስፍን ፣ አምባሳዴር ካሳ ተሰማ የመሳሰሉ ሰዎች ታድመውበት ነበር ።
በዚህ የውይይት መድረክ ላይ በቀጠናው የፖለቲካ ጉዳይ ላይ ጥናታዊ ፅሁፋቸውን ካቀረቡት መካከል አምባሳደር ህርማን ኮህን ነበሩ ። ፅሁፋቸውን ካቀረቡ በኋላ ለተጠየቁት ጥያቄዎች ሲመልሱ በአንድ ወቅት አዲስ አበባ ሄደው የገጠማቸውን እንደሚከተለው ተናግረው ነበር: … ”

” በአንድ ወቅት ” አለ ህርማን ኮህን ” ከስቴት ድፓርትመንት አፍሪካ ደስክ ሃላፊነቴ ከወጣሁ በኋላ አንድ ወቅት ወደ ኢትዮጵያ ሄጄ ነበር ። ኢትዮጵያ እንደደረስኩ ህዝቡ በፍርሃት ቆፈን ውስጥ እንደሆነ ተሰማኝ ። ኢህአድግ ፍፁም አምባገነን ሆኗል ። ፈፅሞ ያልጠበኩት ነገር ገጠመኝ ። ኢህአድግ እንደ ደርግ ጨቋኝ ይሆናል ብዬ ፈፅሞ አስቤ አላውቅም ነበር ።
ሁኔታው ለእኔ አስገራሚ ነበር ። በወቅቱ ለዚህ እንቆቅልሽ ለሆነ ነገር መልስ ፍለጋ ነበርኩኝ ።
አንድ ስሙን መጥቀስ የማልፈልገውና አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የሚያስተምር ሰው ጋር ምሳ እየበላን ስለ እና ስለሃገሪቱ መወያየት ጀመርን እኔም ይሄን ምሁር
” ኢህአድግ ባልገመትነው ሁኔታ ጨቋኝ እና አምባገነን እየሆነ ነው ለምን ይመስልሃል ? ” ብየ ጠየቀሁት
ምሁሩም እኔን በወቅቱ እጅግ ያስደነገጠኝንና ያስገረመኝን መልስ እንድህ በማለት መለሰልኝ:
” የኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ መንገድ እየቆነጠጥክ ካልሆነ መግዛት አይቻልም ። ህዝቡ ገና ለደሞክረሲ አልደረሰም ።” በማለት መለሰልኝ ” ብለው ገጠመኛቸውን ለታዳሚው ተናግረው ነበር ።

… አምባሳደር ህርማን ኮህን ኢህአድግ አዲስአበባን እንድቆጣጠር ከደርግ ጋር ተደራድረው ” ግሪን ላይት ” ያሳዩትና ለኢህአድግ ያልተቋረጠ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር የአፍሪካ ደስክ ሃላፊ የነበሩ ናቸው ።
አምባሳደሩ በወቅቱ መድረኩ ላይ በግርምትና በሚመስል ንግግር እናንተ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ደሞክረሲ ለእኛ አይጠቅመንም እያላችሁ እየተናገራችሁ አሜሪካ ምን ታድርጋችሁ በሚመስል ንግግር ታዳሚውን ሸንቁጠውት ነበር ።

እውነት ለመናገር እኛ አፍሪካውያን ለራሳችን ክብር መስጠት ካልጀመርን ማንም እንድያከብረን መጠበቅ የለብንም ። ፈረንጆቹ ብዙ ጊዜ አፍሪካ ውስጥ የሚደርሰውን ከፍተኛ ግፍና የሰብአዊ መበት ጥሰት ባላየ የሚያልፉት ለጥቁር ደሞክረሲ አያስፈልገውም ከሚል ንቀት የመነጨ ነው ። እንደ ሃይሌ ገ/ ስላሴ ያለለ በንዋይ የሰከረ ነገር ግን የታወቀ ሰው ይሄን በሚዲያቸው ሄዶ ፈረንጆቹ ለአፍሪካውያን ያላቸውን የተሳሳተ አመለካከት ማረም ሲገባው ሲያረጋግጥላቸው ሲታይ ሰውየው ምን ነካው ያስብላል ።

Advertisements