ሀይሌ እና BBC


ትላንት ከBBC ጋዜጠኛ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ላይ ‹‹ዴሞክራሲ ለአፍሪካውያን ቅንጦት ነው:: ለአፍሪካ የሚያስፈልገው መልካም አስተዳዳሪ ነው›› … “As an African citizen democracy is a luxury… the most important thing is a good governor,” ብሎ ተናግሯል፡፡ ይህም የሀይሌ ግላዊ አስተያየት ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል፡፡

***
ሀይሌ በቃለ መጠይቁ ላይ የአፍሪካ መንግሥታትን እንዲሁም ኢሕአዴግን የሚተች ሂስ ሰንዝሯል፡፡

ጋዜጠኛው የWorld Bankን ሪፖርት ጠቅሶ ቢዝነስ ለመጀመር ምቹ ናቸው ተብሎ በወጣው ደረጃ ኢትዮጵያ ከ189 አገራት ጋር ተወዳድራ 176ኛ መሆኗን ሲገልፅለት ሀይሌም ‹‹ሁሉም ያልካቸው ችግሮች መኖራቸውን አምናለሁ፡፡ እናት አለህ፤ ምናልባትም ይህቺ እናትህ አንተ የማትወደው መጥፎ ባህሪይ ሊኖራት ይችላል፤ ግን እናቴ አይደለችም ማለት ትችላለህ? አትችልም፡፡ ኢትዮጵያ አገሬ ናት፡፡ ስለዚህም ችግሮቹን መጋፈጥ አለብኝ››

“If we have that, Africa has the potential to change.”

***
‹‹አህጉራችን፤ አፍሪካ ካሉባት ችግሮች አንዱ ‹አገር መምራት ያለብኝ እኔ ብቻ ነኝ!› የሚል አስተሳሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ እኔ ሁሌም ሳሸንፍ የምኖር ሯጭ አይደለሁም፡፡ የኔን ሪኮርዶች የሰበረ ከኔ የተሻለ ሯጭ አለ፤ አፍሪካውያን ማመን ያለብን እንደዚህ ነው››

Like, Comment, Share.Lot’s of thanks.

የሀይሌ 3፡44 ደቂቃ የሚፈጀውን ቃለ መጠይቅ ማዳመጥ ከፈለጉ ይህንን ሊንክ ይጫኑ! http://www.bbc.co.uk/programmes/p03j72kv
Gebrselassie-HailePC1-Nijemegen11

Advertisements