ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል መሬት ላይ ሊረገጥ አይገባም!!!


12669547_471176846407357_3683880091143091013_n

“ስለ ክርስቶስ መስቀል የሚመለከተው ሁሉ ሼር ያድርግ”

መስቀል የእግዚያብሔር ታላቅ ሀይሉ የተገለፀበት ዲያብሎስን ያዋረደበት መእምናንን የታደገበት የሰላም ዙፋን ከመሆኑም በላይ በዕለተ አርብ ቅዱስ ስጋው የዋለበት፣ካሳ የተከፈለበት፣ወርቅ ደሙ የፈሰሰበት ስለሆነ እናከብረዋለን። እንሳለመዋለን፣ እንመካበታለን። የፀጋ ስግደት እንሰግድለታለን።

ሆኖም ግን ይህን ክቡርና ቅዱስ መስቀል የያዘ የመሬት ምንጣፍ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ ሀገርን እንመራለን ህዝብን እናስተዳድራለን ከሚሉት ባለስልጣን የቢሮ ወለል ላይ ተነጥፎ በእግር ሲረገጥ ማየት ለህዝበ ክርስትያን በተለይም ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መእምናን ትልቅ ውርደት ነው።

ስለሆነም ይህንን ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል የያዘ የወለል ምንጣፍ ባስቸኳይ ከምኒስትሩ ቢሮ እንዲነሳ እና ይህንንም አስነዋሪ ድርጊት ያከናወኑ ግለሰቦች ህዝበ ክርስትያኑን ይቅርታ እንዲጠይቁ እናሳስባለን።

ከዚህ በታች ያለው ፎቶ የአልጀዚራ ጋዜጠኛ የኢትዮጵያ የህዝብ ግንኙነት ሚንስተር የሆኑትን አቶ ጌታቸው ረዳን በቢሯቸው ተገኝቶ በኦሮምያ የተከሰተውን ግጭት አስመልክቶ ቃለመጠየቅ ሲቀርብ ያሳያል!

“መስቀል ሀይላችን ነው”
ይህንን ፎቶ የያዘውን ቪዲዮ ለመመልከት ያህንን ሊንክ ይጫኑhttp://youtu.be/7jN0PawlakM
ምንጭ: በትረ ሙሴ

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s