የሽንታችን ቀለም ስለጤናችን ምን ይነግረናል?


FI-Pee

የሰው ልጅ ከረጅም ጊዜ በፊት ጀምሮ ሽንትን በመመርመር የጤንነት ሁኔታን ለማወቅ ሲጠቀምበት ቆይቷል።

የሽንት ቀለም እና ጠረን እንዲሁም አጠቃላይ ሁኔታ ምን አይነት የጤና እክል በየትኛው አካላችን ላይ እንደገጠመን ለማወቅ እና ለዚያም የሚሆን ሕክምናን ለማግኘት እንድንዘጋጅ የሚጠቁም መሆኑ ነው የሚነገረው።

ከዚህ በተጨማሪም በሰውነታችን የሚገኘው የውሃ መጠን በምን አይነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ለማወቅ ይረዳል።

እስኪ ዋና ዋና የሽንት ከለር አይነቶችንና ስለጤናችንስ ምን እንደሚናገሩ እንመልከት።

ቀለም አልባ ወይም ( Transparent )፦

ይህ አይነቱ ቀለም በቂ ወይም ከበቂ በላይ ውሃ መጠጣታችንን የሚሳይ ነው።

በቂ እና ከበቂ በላይ ውሃ መውሰድም ምንም አይነት የጤና ጉዳት ወይንም አሳሳቢ ችግር እንደሌለብን አመላካች መሆኑ ነው የተገለፀው።

ቤዥ ቀለም፦

ይህ በመጠኑ ደብዘዝ ያለ የማር ከለር ያለው የሚባል ሲሆን፥ በቂ ውሃ መጠን በሰውነታችን እንደሚገኝ ይጠቁማል ።

ግን የቀለሙ ሁኔታ እየጠቆረ በመጣ መጠን ሰውነታችን ውሃ እያጣ እንደሚገኝ እና በቅርቡም ውሃ መጠጣት እንደሚኖርብን እያመላከተን እንደሆነ ነው የተጠቀሰው ።

ቡኒ ቀለም፦

ሽንታችን ቡናማ መልክ ከተስተዋለበት ሰውነታችን በቂ ውሃ አለማግኘቱን የሚጠቁም ነው።

በመሆኑም ፈጠን ብለን ውሃ ለመጠጣት መሞከር ይኖርብናል።

ቡኒ የሽንት ቀለም ከዚህ በተጨማሪ በጉበታችን ላይ የጤና እክል እንዳለ የሚጠቁም በመሆኑ የህክምና ባለሙያዎችን ድጋፍ ለማግኘት መሞከሩ ነው የሚመከረው።

ቀይ ቀለም፦

ይህ አይነቱ የሽንት ቀለም የአሳሳቢ የጤና እክል ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል።

በመሆኑም በአስቸኳይ የህክምና ምርመራ ማድረግን የሚጠይቅ ነው።

ቀይ የሽንት ቀለም የተመገብነው ምግብ የተበላሸ፣ የተመረዘ አልያም በሌላ በማንኛውም ሁኔታ ለጤና የማይመከር ሲሆን በአብዛኛው ይከሰታል።

ከዚህ በተጨማሪ የውስጥ አካሎቻችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲደርስ ሊከሰት የሚችል በመሆኑ በፍጥነት የህክምና ዕርዳታ ማግኘት ያሻል ነው የተባለው

ምንጭ፦ http://health.clevelandclinic.org

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s