ሰበር ዜና የአቡነ መልከ ፄዴቅ የኦርጋን መልእክት ተቃውሞና ብጥብጥ እየ ቀሰቀሰ ነው!


በመምህረ ኦርጋን አቡነ መልከ ፄዴቅ የኦርጋን ጉዳይ ከተነሣ ጀምሮ በውጭው ሲኖዶስ ጥላ ሥር የሚገኙ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ውጥረት ነግሦባቸው ሰንብቷል።እስካሁን ድረስ ጉዳዩን የግል ጥላቻ አድርገው በመገመት ቸል ሲሉ የቆዩ ምእመናን ከሰሞኑ የተከሰተው ሁኔታ በተሐድሶ አራማጆች እንደተከበቡ እንዲረዱ አድርጓቸዋል።
በካናዳ ቶሮንቶ ቅድስት ማርያም የሰነበተው ቅራኔ እያገረሸ መጥቷል ምእመናኑ በደብሩ አስተዳዳሪ በቄስ ምሳሌና በግብረ አበሮቹ የተሐድሶ እንቅስቃሴ በማዘኑ ደብሩ ለከፍተኛ ብጥብጥ ተዳርጓል።

በዴንቨር ኮሎራዶ ፖስተር ትዝታው ሎስ አንጀለስ ላይ በኦርጋን መዘመሩን፣በፌስ ቡክ ገፁም ስለ ኦርጋን መፃፋን የተመለከቱ ምእመናን አስተዳዳሪው አባ ሳሙኤል ዘንድ በመቅረብ ቅሬታቸውን ሲያሰሙ ሰንብተዋል።አንዳንዶቹም በቁጣና በብስጭት ከቤተ ክርስቲያን ቀርተዋል። ሳውዝ ዳኮታም ላይ ስደተኛው ሲኖዶሱ ያስተላለፈው ከገበያ በተገዛ አልኮልነት ባለው ወይን ይቀደስ ዘቢብ አያስፈልግም በሚለው ውሳኔ ምክንያት ባለፈው ሳምንት ከባድ ብጥብጥ ተከስቷል።ከዚህ ጋር በዚህ ሳምንትም በኦርጋን ዘምሩ የሚለው የአቡነ መልከ ፄዴቅ የክህደት ትምህርት ተሰምቶ ምእመናን ቅሬታቸውን የበለጠ አባብሶታል።በካናዳ ቶሮንቶ ቅድስት ማርያም የሰነበተው ቅራኔ እያገረሸ መጥቷል ምእመናኑ በደብሩ አስተዳዳሪ በቄስ ምሳሌና በግብረ አበሮቹ የተሐድሶ እንቅስቃሴ በማዘኑ ደብሩ ለከፍተኛ ብጥብጥ ተዳርጓል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ለጥምቀት በዓል መዝሙር እንዲያቀርቡ ከተጋበዙት ወጣት ሰንበት ተማሪዎች መካከል የላስ ቬጋስ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን( የብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ልጆች) ከቅዱስ ሚካኤል(ላስ ቬጋስ)ወጣቶች ጋር በመሆን በሚዘምሩበት ወቅት ኦርጋን እንዳይመታ አድርገዋል።እኛ ስንዘምር ኦርጋን እንዳትመቱብን ያሉ እነዚህ ወጣቶች በከበሮ ታጅበው ያቀረቡት መዝሙር እጅግ ማራኪ እንደነበር ብዙዎች መስክረዋል።በመናፍቅ መንጋ መሀል ደምቀው ለታዩ ለእነዚህ ቁርጠኛ የተዋሕዶ ልጆች ምስጋናችን ከያለንበት ይድረሳቸው ብለናል።

በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እንዳሻቸው ሲፈነጬ አቡነ መልከ ፄዴቅን አይተው የማይናገሩ ጳጳሳትም በጥምቀት በዓል በተላለፈው የክህደት መልእክት እጅግ ማዘናቸውን ሲገልጡ ተሰምተዋል።ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ(ላስ ቬጋስ)፣ብፁዕ አቡነ መቃሪዎስ(ካናዳ)፣ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ(ካናዳ) ቅሬታቸውን ካሰሙ አበው መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።የተሐድሶ መንፈስ አራጋቢ የሆኑት እነ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ(አትላንታ)፣አቡነ ሰላማ (የቀድሞው አባ ፅጌ አትላንታ)፣በመልእክቱ መደሰታቸውን ሲናገሩ እንደዚሁ ተሰምተዋል።

በውጭው ሲኖዶስ ሥር የሚገኙ አብዛኞቹ አብያተ ክርስቲያናት ከኦርጋን በተጨማሪ በተሐድሶ አራማጆቹ የተከሉ አሳዛኝ ሥርዓቶች ይታዩባቸዋል።ተአምረ ማርያም አለማንበብ፣ከገበያ በቀረበ አልኮልነት ባለው ወይን መቀደስ፣የእመቤታችን፣በቅዱሳን ሥም ማስተማር እና መዘመርን እንደነውር መቁጠር በየአብያተ ክርስቲያናቱ የሚታዩ የተለመዱ ክስተቶች እየሆኑ መጥተዋል።ተሐድሶ በሀገር ቤት ከላይ ጀምሮ ደጋፊዎች ያሉት ሲሆን በውጭው ሲኖዶስ ግን ሲኖዶሱን እስከ መቆጣጠር ደርሷል።

Advertisements