ፓስተሮቹ በመብረቅ ተመተው ሞቱ


ናምቢያዊው ፓስተር የተመታው ስብከት ላይ እንዳለ ነው ተባለ

በናምቢያ ምስራቃዊ ግዛት ካቫንጎ ወረዳ በምትገኘው የሐዋሪያት ቤተክርስቲያን የ41 ዓመቱ ፓስተር (መጋቢ ) ስብከቱን ያዳምጡ በነበሩ ተከታዮቹ ፊት ለፊት በመብረቅ ተመትቶ መሞቱን ኢንስፔክተር ካውና ሺክዋምቢ መናገራቸውን የአገሪቱ ጋዜጦች ዘግበዋል ።
መጋቢው ካቫንጋ ጆን ካሮራ እንደሚባል የጠቆሙት ኢንስፔክተሩ ሌላ ሰው ላይ ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም ብለዋል ።
ሌላኛው የመብረቅ አደጋ በፓስተር ላይ የደረሰው በአውስትራሊያ አዴላይዴ ሂልስ ሲሆን የአራት ልጆች አባትና የወጣቶች ፓስተር መሆኑ የተነገረለት ክሪስ በአደጋው ህይወቱ አልፏል ።
የ39 ዓመቱ ፓስተር ክሪስ በመብረቁ የተመታው ኮርነርስቶን ኮሌጅ ውስጥ በክረምቱ እረፍት ላይ የሚገኙ ወጣቶችን ለማስተናገድ ካምፕ በማዘጋጀት ለቤተክርስቲያን አገልግሎት እየተጣደፈ በሚገኝበት ሰዓት ነበር ።
ከክሪስ አደጋ በኋላ ያገለግልባት የነበረች ቤተክርስቲያን ባወጣችው የሐዘን መግለጫ “ክሪስ በሁሉም የሚወደድ አገልጋይ ነበር ።ለቤተሰቦቹና ለወዳጆቹ በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን “ብላለች ።<a

Advertisements