የአክራሪዎች መፅሃፍ ተቃጠለ በሚል የተቃጠለ ቁርአንን ያሳየው መንግስት በነኤልያስ ከድር ላይ በመፍረድ በሙስሊሞች ላይ ዘመቻውን አጠናክሯል


የአክራሪዎች መፅሃፍ ተቃጠለ በሚል የተቃጠለ ቁርአንን ያሳየው መንግስት በነኤልያስ ከድር ላይ በመፍረድ በሙስሊሞች ላይ ዘመቻውን አጠናክሯል ሙስሊሙ አንድነቱን አጠናክሮ ብሄራዊ ጭቆናውን መታገል አለበት ተብሏል።

በፍትህ እጦት ፍርድ ቤት ከ 40 ግዜ በላይ የተመላለሱት ጀግኖቹ በኤልያስ ከድር መዝገብ የተከሰሱት ወጣቶች የደህንነቱ የካንጋሮ ፍርድ ቤት ከደህንነቶች የተላከለትን ወሳኔ በወንድሞቻችን ላይ ማቅለያ ውድቅ በማድረግ የ7 አመት ኢ,ፍትሃዊ ውሳኔ አስተላለፈ።
እነ ኤልያስ ከድር የክስ መዝገብ የተከሰሱት ከአዲስ አበባ እና ከወልቂጤ የተያዙት 16 ሙስሊሞች ሃምሌ 27/2007 በነበረው ችሎት በደህንነቶች የሚመራው ፍርድ ቤት የአቃቢ ህግን ሃሰተኛ ክስ እና የውሸት ምስክር በመቀበል ጥፋተኛ ናቹህ ተከላከሉ በማለት ብይን መስጠቱ አይዘነጋም ተከሳሾች ከበቂ በላይ ማስረጃዎችን አቅርበው የነበረ ሲሆን በሳላፍነው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ፍርድ ቤቱ የመጨረሻ ብይን ተሰጥቶ መቁዋጫውን ያገኛል ተብሎ ቢጠበቅም የደህንነቶች የሚመራው ፍርድ ቤት መዝገቡን አላየነውም በማለት ድጋሜ ለዛሬ ለታህሳስ 18 ከሰዓት ቡሃላ ቀጠሮ ቢኖራቸው ፍርድ ቤት አቅርበዋቸዋል ፍርድ ቤቱም በመጨረሻ ብይኑ ብቸኛዋ ሴት ታሳሪዋ መሬማ ሃያቱን ጨመሮ በኤልያስ ከድር መዝገብ የተከሰሱትን 16 ሁሉንም ሙስሊሞች የካንጋሮ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ናቹህ በማለት ብይኑን አሰምቱዋል በቀጣዩ ጥር 2 የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ከ2 ሳምንት ቡሃላ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን በእለቱ ፍርድ ቤት ቀርበው የ3 ንፁሃን ተከሳሾች የቅጣት ማቅለያ አልደረሰንም አላየነውም በማለት አሳፋሪ ምክንያት ለዛሬ ጥር 10 ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በደህንነቶች የሚመራው የካንጋሮ ልደታ ፍርድ ቤት 19 ወንጀል ችሎት ንፁሃን ሙስሊሞች ላይ የ7 አመት ፍርድ ፈረዱዋል ንፁሃን ወንድሞቻችን ከፍርዱ ቡሃላ ሙስሊሙን በተላለፈባቸው ፓለቲካዊ በፍርድ ሳይከፉ አብሹሩ ኢነላሃ ማዕና ዱዓ አድርጉ ሲሉ ተሰምተዋል አጃቢ ፓሊሶችም፣ሙስሊም ማህበረሰብ፣በአጠቃላይ በችሎት የተገኘው ህዝብ በፅናታቸው ሲገረም ታይቱዋል በርግጥም ፓለቲካ ውሳኔ ሙስሊሞቹን አታስደነግጥም ይበልጥ ትግላቸውን እንዲያፋፍፋሙ ይረዳል።

አቃቢ ህጉ 1996 የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጵ 32/1/ለ ፣ 38/1/፣ለ እና በፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀፅ 7/1/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ በነ ኤልያስ ከድር መዝገብ የተከሰሱትን ወጣቶች የህዝበ ሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን እነ አቡበክር አህመድን ከእስር ለማሰለቀቅ ሞክረዋል፣የህዝበ ሙስሊሙን መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴን በመተካት ተንቀሳቅሰዋል፣ህብረተሰቡን አስፈራርተዋል፣ድማፃችን ይሰማ የሚል በራሪ ወረቀት በትነዋል እና ሌሎችም ክሶች ራሱ የሸባሪ ህግ በሚባለው በፀረ ሽብር ህጉ ነው የከሰሳቸው በኤልያስ ከድር የክስ መዝገብ የተከሰሱት ሙስሊሞች ስም ዝርዝር የክስ ቻርጃቸው ላይ የተዘረዘረው እንደሚከተለው ነው:–
1,ኤልያስ ከድር ሽኩር
2,ሙባረክ ከደር ሃሰን
3,ቶፊቅ መሃመድ ኡመር
4,ፈይሰል አራጋው ኡመር
5,አብዱልመጂድ አብዱልከሪም መሃመድ
6,ኢስማኢል ሙስጠፋ ሃሰን
7,ሬድዋን አብደላ አህመድ
8,አንዋር ሱልጣን መሃመድ
9,አብዱልአዚዝ ፈትሁዲን በድሩዲን
10,ጃአፈር ደጋ ሃሰን
11,ፍሩቅ ሰኢድ አብዶ
12,መሬማ ሃያቱ ዑመር
13,መሃመድ አሊ ሃሰን
14,መሃመድ አይለየን
15,አቡበክር ሰልማን ሙሳ
16,ሙአዝ ሙደሲር አወል ናቸው ዛሬ ፓለቲካዊ ብይን የተላለፈባቸው ጀግኖች ወንድሞቻችን

ሙስሊሙ ማህበረሰብ በፓለቲካዊ ብይን ከጀመርኩት ትግል አይገታኝም በማለት መልዕክቱን እያስተላለፈ ይገኛል12573750_456734647843653_5346997551937903513_n

Advertisements