ጤናማ የሆኑ እና ጤናማ ያልሆኑ የልጆች በሃሪያቶችን እንዴት መለየት እንችላለን?


images
አንዳንዴ ወላጆች የልጆቻቸውን ባህሪ ጤናማ የሆነ ወይም ጤናማ ያልሆነ ብለው ለመለየት ሲቸገሩ ይታያሉ፡፡አብዛኞቻችን በዘልማድ ጤነኛ ብለን የምንረዳው የልጆች በሀሪ ልጆች አርፈው የሚቀመጡ ከሆነ አድርጉ የተባሉትን ብቻ የሚያደርጉ ከሆነ…ወዘተ የመሳሰሉትን ነው ከዚህ በተቃራኒ ያሉትንን ባህሪያቶች እንደጤናማ አንቆጥራቸውም፡፡
በእውነታው አለም የልጆችን ባህሪ ሙሉ ለሙሉ ጤናማ ወይም ጤናማ ያልሆነ ብለን ለመየት የሚያስችል ድንበር የለም፡፡ጤነኛ ወይም ጤነኛ ያልሆነ ብለን ለመለየት የምንጠቀመው ንጽጽርን ነው፡፡ከዚህም በተጨማሪም ጤናማ የሆነ ወይም ጤናማ ያልሆነ ባህሪ በምንኖርበት ማህበረሰብ ባህል እና አኗኗር ላይም ይወሰናል፡፡ነገር ግን ከልጆች እድገት አንጻር ጤነኛ ሊባሉ ወይም ላይባሉ የሚችሉ እና ለሁሉም ህጻናቶች የሚሰሩ ባህሪያቶች አሉ፡፡
እነዚህን ባህሪያቶች ከዚህ እንደሚከተለው እናያቸዋለን፡፡
1.ጤናማ የልጆች ባህሪያት
1.1.ነገሮችን ያለማንም እገዛ መስራት መፈለግ
ህጻናቶች ነገሮችን በአብዛኛው በራሳቸው መንገድ የመስራት ፍላጎት አላቸው፡፡ከአቅማቸው በላይ የሆነ ነገር እንኳን ቢሆን እገዛን ላይፈልጉ ይችላሉ፡ አንዳንድ ወላጆች ይህን ባህሪ ጤናማ አይደለም ብለው ሊያስቡ ይችላሉ ነገር ግን ህፃናቶች በውስጣቸው ነገሮችን በራሳቸው መንገድ የመስራት ፍላጎት አላቸው፡፡ ስለዚህ ወላጆች ልጆችን በማይጎዳ መልኩ ነገሮችን በራሳቸው መንገድ እንዲሰሩ ልናበረታታቸው ይገባል፡፡
1.2.ትዕዛዝን አለመቀበል
አንዳንድ ጊዜ ልጆች አድርጉ የተባሉትን ነገር ለማድረግ ፍቃደኛ ላይሆኑ ይችላሉ ፡፡ልጆች በባህሪያቸው ነጻነት ይፈልጋሉ፡፡ወላጆች እንደዚህ አይነት ነገር ሲያጋጥማቸው ሊረበሹ አይገባም፡፡
1.3.እራስ ወዳድነት
ልጆች ያገኙትን ነገር ሁሉ የራሳቸው እንዲሆን ይፈልጋሉ በዚህም የተነሳ እራስ ወዳድነትን ያሳያሉ ወላጆች እንደዚህ አይነት ነገር ሲያጋጥማቸው ጤነኛ የሆነ ባህሪ መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡
1.4.አለምን በራሳቸው መንገድ ለመረዳት መሞከር
ልጆች ትንንሽ ሳይንቲስቶች ናቸው በዚህም የተነሳ አለምን ለመረዳት በሚያደርጉት ሙከራ ውስጥ ብዙ ጥፋቶችን ሊያጠፉ እንዲሁም እራሳቸውን ለጉዳት ሊያጋልጡ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ወላጆች ይህንን ባህሪ እንደመጥፎ ባህሪ ከማየት ይልቅ ልጆችን ጉዳት ላይ በማይጥል መልኩ ነገሮችን እንዲሞክሩ ልናበረታታቸው ይገባል፡፡
2.ጤናማ ያልሆነ የልጆች ባሀሪያት
ጤናማ ያልሆኑ የልጆች ባህሪት የሚባሉት በልጆች አይምሮአዊ፣አካላዊ፣ማህበራዊ እና ስሜታዊ እድገት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ባህሪያት ናቸው፡፡ የተወሰኑትን ከዚህ እንደሚከተለው እናያቸዋለን
2.1.ስሜትን መቆጣጠር አለመቻል እና ከመጠን ያለፈ ቁጣ
ልጆች ከመጠን ያለፍ ስሜታዊነት እና ቁጣ የሚያሳዩ ከሆነ አስፈለጊውን እርምት ወስደን ማስተካከል አለብን፡፡
2.2.የሚያደርጉትን ነገር መቆጣጠር አለመቻል፡፡
ይህ ነገር ልጆች እያደጉ ሲመጡ የሚዳብር ክህሎት ነው፡፡ ነገር ግን ልጆች እያደጉም ሲመጡ ከመጠን ያለፈ አካላዊ እና ቃላዊ ቁጣ የሚያሳዩ ከሆነ ለሚናገሩት እና ለሚስሩት ስራ ምንም አይነት ትኩረት የማያሳዩ ከሆነ አስፈለጊው ማስተካከያ ሊደረግ ይገባል፡፡
2.3.የተለያዩ ባህሪያቶች እረቃ እያካሄድንባቸውም እንኳን የማይስተካከሉ
ልጆች ተከታትለን ባህሪያቸውን ማረም ካልቻልን ጤናማ ያልሆነ ባህሪ ያሳያሉ ይሄ የነሱ ችግር አይደለም ነገር ግን አስፈላጊውን እርምት እየወሰድንም ያንኑ ባህሪ የሚያሳዩ ከሆነ ከባለሙያዎች ጋር መመካከር ይጠበቅብናል፡፡
2.4.ከትምህርታቸው ወደኋላ የሚያስቀሯዋቸው ባህሪያቶች
ልጆችን ከትምህርት ወደኋላ ሊያስቀሩ የሚችሉ ማንኛውም አይነት ባህሪያቶች ጤናማ ባህሪያት አይደሉም ወላጆች እነዚህን ባህሪያት በመለየት አስፈለጊውን እርምጃ መውሰድ አለባቸው፡፡
2.5.የዕለት ተዕለት ማህበራዊ ግንኙነታቸውን የሚያበላሹ ባህሪያቶች
ልጆች ከሌላ ልጆች ጋር ሊጣሉ ይችላሉ ይሄ እንደችግር ላይታይ ይችላል ነገር ግን ከእኩዮቻቸው በጣም ወጣ ያለ እና ከሰዎች ጋር በተደጋጋሚ የሚያጋጭ ባህሪ ከታየባቸው ጤናማ አይደለም፡፡
2.6.እራስ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ባህሪያቶች
ልጆች እራስን ስለመጉዳት ወይም ስለማጥፋት የሚያወሩ ወይም በተግባር ለመፈጸም የሚሞክሩ ከሆን ጤናማ ባህሪ አይደለም ፡፡
በበሱፍቃድ ዜና

Advertisements