የሕወሓት የደህንነት ሹማምንት እና ወታደራዊ አዛዦች አስቸኳይ ድንገተኛ ስብሰባ ተቀምጠዋል::


ecadf-ethiopian-news3 (2) ሃገራችንን በጉልበት እና በመሳሪያ ሃይል ከሕዝብ ፍቃድ ውጪ እየገዛ የሚገኘው ሕወሓት መራሹ የገዳዮች እና የዘራፊዎች አገዛዝ የደህንነት ሹሞች እና ወታደራዊ አዛዦች አሰቸኳይ ድንገተኛ ስብሰባ መቀመጣቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ተናግረዋል::በኢሕኣዴግ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ አለመተማመን እና በጥርጣሬ መተያየት እየሰፋ መምጣቱ በሃገሪቱ ያለው ተቃውሞ ከመበርታቱም በላይ ውስጥ ለውስጥ ሊፈነዳ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መሆኑ በየቀኑ ስብሰባ ቢደረግም የተቃውሞ ጉዳይ እየሰፋ እና እያደገ መምጣቱ መወገድ ስላለባቸው የብኣዴን እና ኦሕዴድ አባላት/ካድሬዎች በተጨማሪም የውጪ ሃይሎች ጫና ሕወሓትን ከበፊቱ በተለጠጠ መልኩ ውጥረት ፈጥረው አጣብቂኝ ውስጥ እንደከተቱት እና ካሁን በፊት ውጤት ያመጣሉ ተብለው በስብሰባ ከተወሰኑ በኋላ የተወሰዱት እርምጃዎች ምንም ውጤት ስላላመጡ አስቸኳይ ስብሰባው ፈጣን እርምጃዎች ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ ምንጮች ይናገራሉ::

አገሪቷን ቡድናዊ የጥቂቶች ስብስብ የሆነ ዘረኛ ቡድን እየመራት ነው የሚሉት ምንጮች ስብሰባው ላይ የተሳተፉ የሕወሓት ሰዎች ብቻ መሆናቸው እና ሊወስዱት ያቀዱት እርምጃ ከዘረንነት እና ከግለኝነት የማይዘል መፍትሄ አልባ ነው ሲሉ ለምንሊክ ሳልሳዊ ይገልጻሉ::በፍትህ አካሉ ላይ ሞትን በማወጅ እየገደሉ ያሉ የፍርድ ቤት አለቆች የተእሰበሰቡት እና የሚወስኑት ውሳኔ ከሕዝብ ጋር እልህ ከመጋባት ውጪ ምም መፍትሄ እንደማያመጣ እና አወዳደቃቸውንም ከማፋጠን ውጪ ተመራጭ ባለመሆኑ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና የለውጥ ሃይሉ ከበፊቱ በበለጠ ሕዝብ ውስጥ ዘልቀው በመግባት ጠንካራ ስራ መስራት ከቻሉ ስርዓቱ አጣብቂኝ ውስጥ ሆኖ እየተንገዳገደ በመሆኑ ማስወገድ እንደሚቻል ምንጮቹ ይናገራሉ::

ይህ በእንዲህ እንዳለ ለሁለት ሳምንት የሚቆይ ግምገማ በደህንነት አባላት እና በወታደራዊ መኮንኖች ላይ እንደሚካሄድ እና የግምገማውን መሪነት የሕወሓት ሰዎች ይዘውት ሌሎች አባላትን ለማጥቃት እና ለማስወገድ እንደሚጠቀሙበት ከወዲሁ ለማወቅ ተችሏል:(ምንሊክ ሳልሳዊ) –

Advertisements