“…ድርድር የሚባል ነገር የለም” – ኦቦ ቃሲም አባነሻ የኦነግ ቃል አቀባይ | ሊደመጥ የሚገባ ቃለምልልስ


ኦቦ ቃሲም አባነሻ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቃል አቀባይ ናቸው። በወቅቱ አገር ቤት በኦሮሚያ ክልል በከፍተኛ ደረጃ የተስፋፋውን እንዲሁም በሰሜን ጎንደር የታየውን ሰላማዊ የህዝብ ተቃውሞና ቁጣ የአገዛዙ ታጣቂዎች በመሳሪያ ለማፈን በወሰዱት የጭካኔ እርምጃ ከ80 በላይ ንጹሃን ተገለዋል። የህወሃት ገዢዎች ያሳሰባቸው በሰላማዊ ሰዎች ላይ መተኮሳቸው ሳይሆን በእነሱ ሂሳብ አራርቀነዋል ያሉት የኦሮሞና የአማራ ሕዝብ እንዳሰቡት አለመጋጨቱ አስደንግቷቸዋል።በኦሮሞያ አመያ ላይ አማሮች ባሉዋቸው ላይ በተቀነባበረ ሁኔታ ጥቃት እንዲፈጸም አድርገዋል።አምስት ሰዎች ሞተዋል። ይህ የተቃዋሚዎቹ ጥያቄና እርምጃን የማይወክል ድርጊት ነው። በሚኒሶታ ላይና ዋሽንግተን፣ ካይሮና ሌሎችም ከተሞች በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵአውያን በግፍ የተገደሉ ንጹሃን ላይ የተወሰደውን ግፍ አውግዘው የኦሮሞ ተማሪዎች ያነሱትን የፍትህ ጥያቄ ደግፈው ቆመዋል። አገዛዙ በአንድ በኩል በጥይት፣በአጥፊው ቅስቀሳ የተነሳበትን ተቃውሞ ለማብረድ ይሞክራል በሌላ በኩል ተቃዋሚዎችን ለመከፋፈል በአደባባይ አሸባሪዎች ያላቸውን ጭምር በጓሮ በር እንደራደር በሚለው ባህሪው ይታወቃል።ዛሬስ ይህንና ሌሎችን ወቅታዊ ጉዳዮችን አንስተን ቃል አቀባዩ ምላሽ ሰጥተዋል።