ከፍተኛ የወያኔ ባለስልጣናት በቋራ ህዝብ ውርደት ተከናንበው ተመለሱ


tplf-in-gondar

አባይ ፀሐዬ፣ ደመቀ መኮንን፣ ገዱ አንዳርጋቸውና ሌሎች በዛሬው ዕለት ወደ ቋራ አምርተው ህዝቡን ለመሰብሰብ ሲሞክሩ ህዝቡ በአንድነት አምፆ ከእነሱ ጋር ፈፅሞ መነጋገር እንደማይፈልግ ገልፆ የውርደትና ሀፍረት ጉንጉን አበባ አንገት አንገታቸው ላይ አስሮ መልሷቸዋል፡፡tplf-in-gondar
የጀግናው አፄ ቴዎድሮስ አጥንት ፍላጭ የሆነው ጀግናው የቋራ ህዝብ አሳፍሮ የመለሳቸው እነ አባይ ፀሐዬ በጎንደር ከተማ ሲኒማ አዳራሽ የፀጥታ ኃይሎችን፣ የዞኑን አመራሮች፣ ወሬ ለማዳመጥና እግር ጥሎት የገባውን ህዝብ ለማወያየት ሞክረው ነበር፡፡ ባለስልጣናቱ ፀረ ሰላም ኃይሎችና አሸባሪዎች ያሏቸውን ጠብመንጃ ያነሱ የነፃነት ድርጅቶች ህዝቡ እንዳይደግፍ ሲያሳስቡ ህዝቡ “ቢመጣ ቢመጣ ከእናንተ የባሰ አይመጣ…” ሲል ምላሽ ሰጥቷቸዋል፡፡ በጎንደር ከተማ የሚኖሩ የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በስማቸው እየነገደ ከሌሎች ቋንቋዎች ተናጋሪዎች ጋር እንዳቆራረጣቸው በመግለፅ ህወሓትን ከሰውታል፡፡ ከዚህ በኋላ የህወሓት ደጋፊም እንዳልሆኑ የአቋም ለውጣቸውን በይፋ አስታውቀዋል፡፡
የጎንደር ከተማ የፀጥታ ኃይሎች ደግሞ በበኩላቸው ከእንግዲህ ወዲህ ወደ ወጡበት ህዝብ አፈሙዝ አዙረው ምላጭ መስበር እንደማይሹና አገዛዙ ወደ ወገናቸው ተኩሱ የሚላቸው ከሆነ አስቀድሞ የጦር መሳሪያቸውን እንዲረከባቸው ጠይቀዋል፡፡

Advertisements