«Al-Shamiyya Front የተባለ የሶሪያ አማፂ/ተቃዋሚ ታጣቂዎች ግንባር ለፅንፈኛው አሸባሪ ISIS ምርኮኞች እጅግ ልብ የሚነካ ይቅር ባይነት፣ ፅንፍ የሌለው ምህረት አደረጉ»


2015-12-09 at 09-36-41
ነገሩ እንዲህ ነው። የሶሪያ ተቃዋሚ ታጣቂዎች የፅንፈኛው አሸባሪ ቡድን ታጣቂ የሆኑ ምርኮኞችን አሸባሪ ቡድኑ ብዙሃኑን በሚቀላበት/በሚገድልበት መልኩ ብርቱካናማ ቱታ አስለብሰው በጉልበታቸው እንዲንበረከኩ ከተደረጉ በኋላ ሽጉጥ ጭንቅላታቸው ላይ ይደግኑባቸዋል። በዚህ ሰአት የአሸባሪ ቡድኑ ምርኮኞች በደቂቃዎች ውስጥ ሞታቸውን እየጠበቁ ነበር። ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ እዚች ሰአት ላይ የሶሪያ ተቃዋሚዎች ቪዲዮ ላይ ከመቅፅበት “ሙስሊሞች ወንጀለኛ አይደሉም” የሚል መልእክት ተነበበ።
እጅግ እጅግ እጅግ በሚገርም ሁኔታ የአረመኔው አሸባሪ ቡድን አባላት የሆኑትን ምርኮኞች በሽጉጥ ጭንቅላታቸውን ለማፍረስ ተዘጋጅተው የነበሩት የሶሪያ አማፂያን ታጣቂዎች ሽጉጣቸውን ከሽብር ቡድኑ ምርኮኞች ጭንቅላት ላይ በማንሳት በኩራት እና በአሸናፊነት ፊታቸውን አዙረው ሲሄዱ ያሳያል።
‪#‎ከዚያም_ቀጥሎ_በሙስሊም‬ የአለባበስ ስርዓት ነጭ ልብስ የለበሰ እና የሐይማኖቱ መገለጫ የሆነ ነጭ ቆብ ያደረገ አንድ የእስልምና እምነት ሰባኪ ድንገት ከፊታቸው ድቅን አለ፣ ምርኮኞቹም አንገታቸውን ካስደፋቸው ስራቸው ካቀረቀሩበት በግድ ቀና አሉ። ነጭ ለባሹ ሰውም ስለ ፍትህ/Justice በዝርዝር አስተማራቸው/አስረዳቸው፣ ሰው በላው አሸባሪ ቡድን እስከዛሬ በግፍ ለጨፈጨፋቸውና እንደ እንስሳ ላረዳቸው ንጹሃን የነፈገው ርህራሄ/ምህረት/ይቅርታ በውስጡ ምን ያህል ጉልበት/ሃይል እንደነበረ አሳያቸው።
አል- ሻይማ የተባለው የሶሪያ ተቃዋሚ ግምባር ፕሬዝዳንት ሼክ መሐመድ ካቲብ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ “ልትገሉን ከፈለጋችሁ ይኸው እንካችሁ ጎራዴያችን። እንዲህ ያለው የእናንተ ግድያ እምነታችንን ያጠናክርልናል/ያጠብቅልናል። ለኛ ቸርነት የሕይወት መርሃችን ነው።”
ሆኖም ከዚህ ሁሉ በኋላ ከላይ ስለ ፍትህ በተሰበከላቸው በተማሩት መሰረት ምንም እንኳን ከሞት/ጭንቅላታቸው በሽጉጥ ከመመታት ምህረት/ይቅርታን አግኝተው በሕይወት ቢቆዩም ለፍትህ ሲባል ለፈፀሙት ውስጥን የሚያሳምም ወንጀል በእስር እንዲቀጡ ተደርገው ወደ ወህኒ ወርደዋል።
(☞ ይቅርታ የሚጠይቅ እና ይቅር የሚል ልቦና ይስጠን። በድሎ ይቅርታ መጠየቅ የህሊና ሸክምን ያቀላል፣ የህሊና ሰላምን ያላብሳል። ተበድሎ ይቅር ማለት ከአምላክ ያስታርቃል፣ ብልህና አስተዋይ ሰው ያደርጋል። ይቅር ያለ ይቅር ይባላል፣ ይቅር ያላለ ይፈረድበታል።)
http://www.mirror.co.uk/news/world-news/syrian-rebels-force-isis-captives-6973430?ICID=FB_mirror_main
CLICK HERE TO WATCH THE VIDEO

Advertisements