ገዳይ ና ገዳይ ና! !


(አሌክስ አብርሃም)
12313965_1665426350407241_1673665649194094717_nጦር ሜዳ ላይ ነው,,,,, ጀኔራሉ,,,ልብሱ በደም ተጨመላልቆ,,,, በአንድ እጁ የተቆረጠ የሰው እግር በሌላኛው እጁ ሳንጃ ይዞ በታላቅ ጀግንነት ከጠላት ቀጠና ወደራሱ ወታደሮች ተመለሰ,,,,, ወታደሮቹ ሲጠፋባቸው ወይ ሙቶ አልያም ተማርኮ ይሆናል ብለው ተጨንቀው ስለነበር ሲያዩት ደስ አላቸው,,,,,,በጦርነቱ የተሰው ጓደኞቻቸውንም ረስተው በጀኔራሉ መትረፍ ተደሰቱ! !
“ጀኔራላችን,,,,,የት ሂደህብን ነው የጠፋህብን,,,,, እያሉ ተንጫጩ,,,, ጀኔራሉ በፍፁም ኩራትና ጀግንነት በእጁ የያዘውን የተቆረጠ ትኩስ እግር ወታደሮቹ ፊት ለፊት ወረወረና
” እኔ የእናተ ጀኔራል ጠላትን ረፍርፊ የጠላታችንን ጦር መሪ እግሩን ቆርጨ አመጣሁት ” አለ ወታደሮቹ በደስታ ወደሰማይ ተኩሱን አንደቀደቁት,,,, ጭፈራውና ሙገሳውን አወረዱት ጀኔራሉን አቅፈው ከአናታቸው በላይ ከፍ እያደረጉ አሞገሱት,,,,,”እናት ወልዳለች ” አሉት! !
በጭፈራው መሃል አንድ በነገሩ የተገረመና በጦርነቱ አንድ አይኑን ያጣ ወታደር ወደጀኔራሉ ጆሮ ጠጋ ብሎ እንዲህ አላቸው,,,, “ጀኔራሌ በጀግንነተዎ ድፍን የአገራችን ህዝብ ታላቅ ኩራት ይሰማዋል መቸም ”
“እርግጥ ነው ” አሉ ጀኔራሉ በኩራት
“እንደው ግን ጀኔራሌ ያንን ከይሲ የጠላት መሪ እግሩን ብቻ ከመቁረጥ አንገቱን አይቀሉትም ነበር?” ሲል ጠየቀ ና በአንድ አይኑ አጨንቁሮ መልሳቸውን መጠበቅ ጀመረ,,,,
ጀኔራሉ ኮራ እንዳሉ መለሱለት
” አስቤ ነበር,,,,, ግን እኔ ከመድረሴ በፊት የሆነ ሰው አንገቱን ቀልቶት ነበር “smile emoticon
“አይ ይች አገር ” አለ ወታደሩ በተረፈች አንድ አይኑ ተራራ ሸንተረሩን በግርምት እየቃኘ,,,,,, ጭፈራው ግን ቀጥሎ ነበር,,,, ለጀኔራሉ ክብር ነግቶ መድፍ እስኪተኮስ እና የ25 ሚሊየን ብር ቪላ እስኪሰራላቸው,,,,, ለጀግናው:)
ወዳጀ የነገረኝ መራር ቀልድ ነች! !

Advertisements