የፓሪሱ ጥቃት ዋና አቀናባሪ መገደሉ ተረጋገጠ


የአርብ ዕለቱን ጥቃት አቀናባሪ እንደሆነ የሚታመነው አብድልሃሚድ ባውድ ከትናንት ጀምሮ በፓሪስ ሰሜናዊ ዳርቻ በሚገኘው በቅዱስ ዴኒስ አካባቢ በተደረገው አሰሳ መገደሉን ቢቢሲ ዘግቧል ።

በዛሬው እለትም አስክሬኑ በሰሜናዊ ፓሪስ መገኘቱ ነው ተነገረው።

የ27 አመቱ ቤልጂየማዊ ወጣት በእጣት አሻራው መለየቱንም ፖሊስ አስታውቋል።

አርብ እለት በፓሪስ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ፈረንሳይን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ ሃገራት በከተሞቻቸው ጥብቅ ቁጥጥር እያደረጉ ይገኛል።

ከአሜሪካ ወደ ፈረንሳይ ይደረጉ የነበሩ ሁለት በረራዎችም፥ ከደህነነት ስጋት ጋር በተያያዘ ካናዳ እና እዛው አሜሪካ ተመልሰው እንዲያርፉ ተደርጓል።

በዛሬው እለት አሰሳውን የተቀላቀለው የቤልጂየም ፖሊስ የ129 ሰዎች ህይወት ያለፈበትን የፓሪሱን ጥቃት ፈጽሟል ተብለው ከተጠረጠሩት ውስጥ ሳላህ አብዲሰላምን ቀደም ሲል በቁጥጥር ስር ማዋሉ ይታወሳል።

ግለሰቡ በቤልጂየም እና ፈረንሳይ ፖሊስ በጥብቅ የሚፈለግ እና ከሶሪያ ፈረንሳይ ዱካውን እያጠፋ ሶመላለስ የነበረ ቀንደኛ አሸባሪ መሆኑም ተነግሯል።

ፖሊስ ሌላው በጥቃቱ ተባባሪ የነበረውና ከፓሪሱ ጥቃት በኋላ ወደ ቤልጂየም መሸሹ የተነገረውን ሳላህ አብድሰላምን እያደነ ይገኛል።

Advertisements