–ከልክ በላይ ውፍረት መንስኤው ቫይረስ ነው


b70c3bab
የአሜሪካ ተመራማሪዎች ብታምኑም ባታምኑም ከልክ በላይ ውፍረት በትንፋሽ እና በእጅ ንክኪ ይተላለፋል እያሉ ነው።
ተመራማሪዎቹ አደረግነው ባሉት ጥናት፥ ከልክ በላይ ውፍረት መንስኤ የሰውነት ህዋሳትን የሚያጠቃ እና ራሱን የሚያራባ ቫይረስ ነው።
እንደ ተመራማሪዎቹ ገለፃ ቫይረሱ በመጀመሪያ ወደ ሳንባችን የሚያመራ ሲሆን፥ ከዚያም ወደ ጉበት፣ ኩላሊት እና አዕምሯችን ይስፋፋል።
ቫይረሱ እነዚህን ህዋሳት ሲያጠቃም እራሱን በእጥፋ እያባዛ ይሄዳል፤ ይህ ሂደት በሰውነታችን አዲስ የስብ ህዋሳት እንዲፈጠሩና ቁጥራቸው በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያሻቅብ በማድረግ አላስፈላጊ ውፍረትን ያስከትላል ይላሉ ተመራማሪዎቹ።
በአይጦች እና ዶሮዎች ላይ በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ ሙከራዎች እነዚህ እንስሳት አዴኖ ቫይረስ ሴሮታይፕ 36 (AD- 36) የተሰኘ ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በዚህም መሰረት ክብደታችን የሚጨምረው በተመገብነው ምግብ አይነት እና ብዛት ሳይሆን በዚህ ቫይረስ ምክንያት መሆኑን ደርሰንበታል ብለዋል ተመራማሪዎቹ።
በፔኒንግተን ባዮ ሜዲካል የጥናት ማዕከል የተከናወነ ሌላ ጥናትም በርካታ ወፍራም ሰዎች ይህ ቫይረስ በውስጣቸው እንዳለ የሚያረጋግጥ ነው።
ተመራማሪዎች በአሁኑ ወቅት ይህን ቫይረስ የሚዋጉ መድሃኒቶችን ለማቅረብ እየሰሩ መሆኑ ተገልጿል።
እነዚህ ክኒኖች ወደ ገበያ እስኪገቡ ድረስም የአመጋገብ ስርአትን ማስተካከል እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ተገቢ ነው ተብሏል
http://bit.ly/1NmjbcU

Advertisements