የለውጡ ማእበል እንደማያስተርፋቸው ያወቁ የወያኔ ባለስልጣናት በደህንነት ቢሮ መከታ ብዝበዛውን ተያይዘውታል::


12189163_413365625528871_4032452364699816312_n

‪ ራሱ እየሰረቀ ሌላውን ማማት ፋሽን እየሆነ ነው፡፡ እራሱ እየገረፈ እንደ ጅራፉ የሚጮኸው እየባሰ ነው፡፡ ሃገራችን በፖለቲካውም ይሁን በኢኮኖሚው መስክ እጅግ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ናት:: በአገራችን ተንሰራፍቶ የሚገኘው ጠባብ – ዘረኛ የወያኔ ጉጅሌ አገዛz ወገኖች በረሃብ – ድርቅ እያለቁ አለም በሚጮኽላቸው በዚህ ወቅት የሃገር ሃብት ምዝበራውን ገፍቶ ቀጥሎበታል:: ባለስልጣናቱ ከአስተዳዳሪነት ይልቅ እጅግ አደገኛ ሌብነት የሚዘውን ዘርፍ መርጠው ከባድ ወንጀለኦችን በሃገር እና ሕዝብ ላይ እየፈጸሙ ነው::ሀገራችን እስከወሲብ ድረስ የተወሳሰበ ሙስና እያስተናገደች ነው::ህልውናዋን ጭምር የሚፈታተኑ ከተላላኪ እስከ መመሪያ አስፈፃሚ የሌብነት ባለድርሻ አካላት የሆኑባት የዘረፋ መናኸሪያ ሆናለች::
በሃገሪቱ በሚገኘኡ የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ በዝምድና በቤተሰብነት እና በዘረፋ ሸሪክነት ተደራጅተው የሃገሪቱን ሃብት የሚቦጠቡጡት የገዢው መደብ ባለስልጣናት እና ተከታዮቻቸው ለሕዝብ ደንታ የሌላቸው መሆኑን ከማሳየቱም በላይ የለውጡ ማኤበል ሳይውጠን በዝብዘን እንሰወር የሚለውን መንገድ ይዘው የሕዝብን ሃብት እየቦጠቦጡ ይገኛሉ::ከተለያዩ መስሪያ ቤቶች የሚገኙ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከባልና ሚስት ጀምሮ እስክ እናትና አባት እህት እና ወንድም እስከ ሰባት ቤተሰብ ድረስ ለዘረፋ ተደራጅተው በሙስና ተዘፍቀዋል::በጸረ ሙስና ኮሚሽን ተብሎ በሚጠራው ዬያኔው መስሪያ ቤት ቢያንስ በቀን እስከ 25 ጥቆማዎች የሚመጡ ሲሆን ለኮሚሽኑ ከመድረሳቸው በፍጥነት ወደ ደህንነት ቢሮ የመዝገብ ምርመራ ከተላኩ በኋላ የደህንነት ቢሮው አስፈላጊ የተባሉ መዝገቦችን ለኮሚሽኑ ሲልክ ጥብቅ ሚስጥር በሚል ደሞ ለኮሚሽኑ የማይላኩ መዝገቦች እንዳሉ ቀርብ የሆኑ ምንጮች ይናገራሉ::
በተለያዩ የሃገር ቤት ሚዲያዎች ይህ ጉዳይ ይፋ እንዲደረግ ጠቋሚዎች ማስረጃዎቻቸውን ይዘው ቢቀርቡም ሚዲያዎቹ ከመንግስት ፈቃድ ማግኘት አለብ በማለት ያለባቸውን ፍራቻ ቢገልጹም በየጽሁፎቻቸው ግን በደፈናው::ሳይዳሥሱ አላለፉትም::በቅርቡ አንድ የሃገር ቤት ጋዜጣ እንዳለው በሀገራችን ሌባው በጣም በዝቷል፡፡ ሁሉም ስለኮርቻው እንጂ ስለ በቅሎዋ አያወራም!የሀብት ዘረፋው ሳያንስ በሥልጣን የሚባልገው ሥፍር ቁጥር የለውም፡፡ ሥልጣን ወደ ኃላፊነት ሳይሆን ወደ ሀብት፣ ወደ መሬት መከፋፈል፣ ወደ ዘመድ መጠቃቀሚያ፣ ወደ ፍትሕ ማዛቢያ፣ ወደ ምዝበራ መረብ ማስፋፊያ፣ ወደ ህገ ወጥ ፎቅ መገንቢያ ካመራ፤ ወደ ልማት ሳይሆን ወደ ጥፋት እየሄድን ነው ማለት ነው፡፡ የተለያዩ ወገኖች ገብተውበት የዘረፋ መረቡ እንዲሰፋ፣ ማድረጉን ይያያዘዋል፡፡ አንዱ ህገ ወጥ ተብሎ ሲታሰር ግን መረቡ አይነካም፡፡ ሀገራችን የተወሳሰበ ሙስና እያስተናገደች መሆኑ ይነገራል፡፡ይህንኑ ሙስና ምሁሩም መሀይሙም፣ ህገ አስፈፃሚውም አላዋቂውም አድናቆቱን እየገለፀና ወሬውን በመንዛት እየተባበረ ሀገራችን ወደ አሳዛኝ ፈተና እየገባች ነው!
የብዝበዛው መረብ እስካልተበጣጠሰ ድረስ! በመሬት ስፋት የማይለካ፣ በፎቅ ርዝመት የማይወሰን፣ በቀረጥ ነፃ ብቻ የማይቆም የህሊና መቆሸሽና ተዛማች የሌብነት በሽታ እንደ ዘር – ደዌ መናኘቱ፤ የዲሞክራሲ፣ የመልካም አስተዳደር፣ የፍትሕ – ርትዕ፣ የዕድገት ሀገር ትሆናለች እየተባለች ፕሮፓጋንዳ የሚነፋላት ሀገራችንን፤ ህልውናዋን ጭምር የሚፈታተኑ ከተላላኪ እስከ መመሪያ አስፈፃሚ የሌብነት ባለድርሻ አካላት የሆኑባት የዘረፋ መናኸሪያ ሆናለች ሃገራችን::አይን ያወጣ ብዝበዛ ተንሰራፍቷል አንድ አሃገር ሕግ እና መንግስት ካለ ከምን ተነስቶ ነው በቃል እና ስልክ ቴዛዝ ትንሽ ይሁን ትልቅ ግዢ የሚፈጸመው?? ራሳቸው ላቋቋሙት የጸረ ሙስና ኮሚሽን መረጃ እና ማስረጃ የሚከለክሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተበራክተዋል::ጠያቂ እና ሃላፊነት የሚሰማው ስላሌለ የሃገር እና ሕዝብ ሃብት እየተበዘበዘ ስለሆነ ሃገር ከመራቆቷ በፊት የለውጥ ሃይሎች በዘረኝነት እና አጥንት ቆጠራ ላይ ከማተኮር ይልቅ የትግል አንድነቱን አጠናክሮ በመቀጠል ድሉን ማረጋገጥ ይጠበቅብናል:

Advertisements